የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/02 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥቅምት 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 28 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 4 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 10/02 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥቅምት 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ጥቅምት 28 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚቀርበው ውይይት ዘኍልቍ ምዕራፍ 25ንና ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ጥራዝ 2 ገጽ 419 ከአንቀጽ 3-5 እንዲያነቡና ከዚያም ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች የተባለውን የቪዲዮ ፊልም እንዲመለከቱ ሁሉንም አበረታታ። በገጽ 1 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ‘የእናንተን ሃይማኖት በሚገባ አውቀዋለሁ’ ለሚል ሰው በሁለት የተለያዩ መንገዶች መልስ ሲሰጥ የሚያሳዩ ይሁኑ።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 20ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቾች ለሌሎች በግል ትኩረት ይሰጣሉ።” አንድ የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካች ከአድማጮች ጋር በጥያቄና መልስ ያቀርበዋል። በመግቢያህ ላይ የመጽሐፍ ጥናት እንዴት እንደጀመረ በአጭሩ ተናገር። (አዋጅ ነጋሪዎች ገጽ 237 አንቀጽ 4) በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት በኩል በግል በተደረገላቸው እርዳታ ያገኙትን ጥቅም እንዲናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ።

መዝሙር 66 (155) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 89 (201)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

20 ደቂቃ:- አንድ ሽማግሌ በመጠበቂያ ግንብ 9-107 ከገጽ 1 እስከ 5 (በእንግሊዝኛው መስከረም 1, 1986 ከገጽ 17-22) ላይ በሚገኘው “ደም አፍሳሽ በሆነ ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ገለልተኛ ክርስቲያኖች” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ ንግግር ያቀርባል። ንዑስ ርዕሶቹንና ቁልፍ የሆኑትን ጥቅሶች አጉላ። (ለአዳዲስ ጉባኤዎች ክፍሉን ለሚያቀርበው ወንድም የሚሆን የዚህ ጥናት ክፍል ፎቶ ኮፒ ይላክላቸዋል።)

15 ደቂቃ:- “ትናንሽ ልጆችም መጠመቅ አለባቸውን?” ይህንን ክፍል በጥያቄና መልስ ተወያዩ። አንድ ልጅ ከመጠመቁ በፊት ትምህርቱን ማጠናቀቅ አለበት የሚለው አመለካከት ማቴዎስ 6:33 ላይ ከሠፈረው መሠረታዊ ሥርዓት ጋር እንደሚጋጭ ጎላ አድርገህ ተናገር። እንዲሁም ወላጆች ትናንሽ ልጆች በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ዕድሜያቸው ገና አልደረሰም የሚል የተሳሳተ አመለካከት እንዳይኖራቸው አሳስባቸው።​—⁠ማቴ. 21:16

መዝሙር 62 (146) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 29 (62)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ባለፈው በተካሄደው የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም ላይ የያዙትን ማስታወሻ ከልሰው እንዲመጡ አበረታታ። አስፋፊዎች የጥቅምት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በገጽ 1 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመጠቀም አንዲት እህት መጠበቂያ ግንብ ስታበረክት፣ አንድ ወንድም ደግሞ ንቁ! መጽሔት ሲያበረክት የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የአቀራረቡን ጥሩ ጎኖች በአጭሩ ተናገር።

12 ደቂቃ:- “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም።” በንግግር የሚቀርብ። የወረዳ ስብሰባ የሚደረግበትን ቀን ተናገር። ሁሉም በስብሰባው ላይ ተገኝተው በጥሞና እንዲያዳምጡ አሳስባቸው። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለጥምቀት እንዲዘጋጁ አበረታታቸው። ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸውን በስብሰባው ላይ እንዲገኙ እንዲጋብዟቸው አሳስባቸው።

25 ደቂቃ:- “ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎችን ልብ እንድንል የቀረበ ፍቅራዊ ማሳሰቢያ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በርዕሱ ውስጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም ከአድማጮች ጋር መወያየት ጀምር። በታኅሣሥ ወር ኖ ብለድ​—⁠ሜዲስን ሚትስ ዘ ቻሌንጅ የተባለውን የቪዲዮ ፊልም እንከልሳለን።

መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 67 (156)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይአምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹርና እውቀት መጽሐፍን ለማበርከት ይረዳሉ ተብለው ከወጡት አቀራረቦች ውስጥ ጥቂቶቹን በአጭሩ ከልስ። ከአቀራረቦቹ አንዱን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

13 ደቂቃ:- በወንጌል አናፍርም። (ሮሜ 1:16) አንድ ወጣት ልጅ ወደ አባቱ ቀርቦ ስለ አንድ ችግር ያወያየዋል። ወጣቱ ጓደኞቹ እንዳይሰድቡት ስለሚፈራ የይሖዋ ምሥክር መሆኑ በትምህርት ቤት እንዲታወቅ አይፈልግም። አባትዬው ልጁ ችግሩን በግልጽ ስለነገረው ያመሰግነዋል። ከዚያም በአንድ ወቅት ጴጥሮስ ሰዎችን በመፍራት ምን እንዳደረገ ይነግረዋል። (ማቴ. 26:69-74) በመቀጠልም አባትየው የሚከተለውን ምክር ይሰጠዋል:- ክርስቲያን በመሆናችን ፈጽሞ ማፈር የለብንም። (ማር. 8:38) የይሖዋ ምሥክር መሆንህን በትምህርት ቤት ማሳወቅህ ይጠቅምሃል። ብዙ አስተማሪዎች የይሖዋ ምሥክር መሆንህን ካወቁ እምነቶችህን የሚያከብሩልህ ከመሆኑም በላይ ከክርስቲያናዊ አቋምህ ጋር በሚጋጩ እንቅስቃሴዎች እንድትካፈል አያደርጉህም። ሥርዓት የጎደላቸው ወጣቶችም መጥፎ ድርጊት እንድትፈጽም አይገፋፉህም። ሌሎች የክፍል ጓደኞችህም ከተቃራኒ ጾታ ጋር ተቀጣጥረህ ለመጫወት እንዲሁም ከትምህርት ውጪ በሚካሄዱ ስፖርቶች ወይም ከትምህርት ሰዓት በኋላ በሚደረጉ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ለመካፈል የማትፈልግበትን ምክንያት በቀላሉ ይረዱልሃል። ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች በተባለው ብሮሹር ገጽ 16-19 ላይ የሰፈሩትን ከዚህ ጋር የሚያያዙ ሐሳቦች ተመልከት። ጊዜ የሚፈቅድላቸው ከሆነ አባትየውና ልጁ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በተባለው መጽሐፍ በገጽ 315-18 ላይ ካለው “ከአምላክ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት በሕዝብ ፊት ማሳወቅ” ከሚለው ንዑስ ርዕስ አንዳንድ ነጥቦችን ይወያያሉ። በመጨረሻም ወጣቱ ልጅ ጥሩ ምክር ስለሰጠው አባቱን ያመሰግነዋል።

22 ደቂቃ:- ለአምላክ ተገዙ​—⁠ዲያብሎስን ተቃወሙ። (ያዕ. 4:7) አንድ ሽማግሌ ከታች የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም ባለፈው የአገልግሎት ዓመት የተደረገውን የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም ከአድማጮች ጋር ሕያው በሆነ ውይይት ይከልሳል። አድማጮች የተማሩትን በሥራ ላይ ለማዋል የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። (ሐሳብ የሚሰጡባቸውን ነጥቦች አስቀድሞ ማከፋፈል ይቻላል።) የሚከተሉትን የፕሮግራሙን ክፍሎች አጉላ:- (1) “በባርነት በተያዘ ዓለም ውስጥ ለአምላክ መገዛት።” በዓለም ወጥመዶች እንዳንያዝ መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው? (2) “በቤተሰብ ውስጥ አምላካዊ ተገዢነትን ማንጸባረቅ።” በይሖዋ ድርጅት ውስጥ የቤተሰብ ትስስርን ማጠናከር በጣም አጣዳፊ ጉዳይ የሆነው ለምንድን ነው? እንዲህ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? (3) “አዳዲስ ደቀ መዛሙርት ከይሖዋ ጎን በጽናት እንዲቆሙ እርዷቸው።” አዲሶች እምነታቸውን የሚፈትኑ እንቅፋቶችን በጽናት እንዲወጡ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? (4) “ዲያብሎስን መቃወም ሲባል ምን ማለት ነው?” ዲያብሎስን በተሳካ ሁኔታ ለመቃወም የሚያስችለው ቁልፍ ምንድን ነው? በኤፌሶን 6:​11-18 ላይ የተዘረዘሩት መንፈሳዊ የጦር ትጥቆች መከላከያ ሊሆኑልን የሚችሉት እንዴት ነው? (መጠበቂያ ግንብ 92 5/15 21-23) (5) “ክፉውን ተቋቁመው ያሸነፉ ወጣቶች” እና “ከአምላካዊ ተገዥነት ጥቅም ያገኙ ወጣቶች።” ወጣቶች ከየትኞቹ የሰይጣን ወጥመዶች ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው? ወጣቶች ራሳቸውን ለይሖዋ በማስገዛታቸው የተባረኩት እንዴት ነው? (መጠበቂያ ግንብ 15-111 ገጽ 13-​14, አን. 15-​17) (6) “ከአምላካዊ ተገዢነት ጥቅም ማግኘት።” ክርስቲያኖች ለመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ ለዓለማዊ አሠሪዎች፣ በቤተሰብ ክልል ውስጥና በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ተገዢነታቸውን እንዴት ማሳየት እንደሚችሉ አብራራ። እንዲህ ለማድረግ የሚረዱን የትኞቹ ባሕርያት ናቸው?

መዝሙር 99 (221) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ