የ2003 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያ
የ2003 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ክፍሎቹ የሚቀርቡባቸው ጽሑፎች:- መጽሐፍ ቅዱስ [1954 ]፣ መጠበቂያ ግንብ [w-AM]፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም [be-AM]፣ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [si]፣ እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rs-AM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ከተከፈተ በኋላ በሚከተለው መመሪያ መሠረት ይከናወናል:-
የንግግር ባሕርይ:- 5 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች፣ ረዳት ምክር ሰጪው ወይም ጥሩ ችሎታ ያለው ሌላ ሽማግሌ ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ላይ በአንድ የንግግር ባሕርይ ላይ የተመሠረተ ክፍል ያቀርባል። (በቂ ሽማግሌዎች በሌሉባቸው ጉባኤዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያለው የጉባኤ አገልጋይ ይህን ክፍል ሊያቀርብ ይችላል።) ተጨማሪ መግለጫ ካልተሰጠ በስተቀር ለሳምንቱ በተመደቡት ገጾች ውስጥ የሚገኙት ሣጥኖች በንግግሩ ውስጥ መካተት ይኖርባቸዋል። መልመጃዎቹ ተማሪው በግሉ እንዲጠቀምባቸውና በግል ምክር ለመስጠት ታስበው የተዘጋጁ ስለሆኑ በክፍሉ ውስጥ መካተት አይኖርባቸውም።
ክፍል ቁ. 1:- 10 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም ወይም “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” በተባሉት መጽሐፎች ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ክፍሉ ለአሥር ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር የሚቀርብ ሲሆን የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። ዓላማው የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ ሳይሆን ለጉባኤው ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ እያጎሉ በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ ማተኮር ሊሆን ይገባል። በፕሮግራሙ ላይ የተሰጠውን ጭብጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን ንግግር እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ክፍላቸውን አቅርበው መጨረስ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይችላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች:- 10 ደቂቃ። በመጀመሪያ ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ለስድስት ደቂቃ ያህል ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር በጥሩ ሁኔታ እያዛመደ ያቀርበዋል። ክፍል ቁ. 2ን የሚያቀርበው ተማሪ በሚያነብበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ማብራሪያ ስለማይሰጥ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርበው ወንድም ለሳምንቱ ከተመደበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ በፈለገው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ሐሳብ መስጠት ይችላል። ለሳምንቱ የተመደቡትን ምዕራፎች በመከለስ ብቻ ክፍሉ መቅረብ አይኖርበትም። ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት እንደሚጠቅም እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ከዚያም ተናጋሪው በቀረው አራት ደቂቃ አድማጮች አጭር (ለ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ላነሰ ጊዜ) መልሶችን በመስጠት እንዲካፈሉ የሚከተሉትን ሁለት ጥያቄዎች ያቀርብላቸዋል:- “ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለአገልግሎት ወይም ለግል ሕይወታችሁ የሚሆን ምን ጠቃሚ ትምህርት አግኝታችኋል?” እና “እምነታችሁን የሚያጠነክርና ለይሖዋ ያላችሁን አድናቆት ከፍ የሚያደርግ ምን ነጥብ አግኝታችኋል?” ከዚያም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በሁለተኛው አዳራሽ ውስጥ ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች መሄድ እንደሚችሉ ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2:- 4 ደቂቃ። ይህን ክፍል አንድ ወንድም በንባብ ያቀርበዋል። ንባቡ አብዛኛውን ጊዜ የሚቀርበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል። በወር አንድ ጊዜ ክፍሉ ከመጠበቂያ ግንብ ይቀርባል። ተማሪው መግቢያ እና መደምደሚያ ማዘጋጀት ሳያስፈልገው ክፍሉን እንዲሁ በንባብ ብቻ ያቀርበዋል። በየሳምንቱ የሚነበበው ክፍል ርዝመት የሚለያይ ቢሆንም በአራት ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሸፈን ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የተማሪውን ዕድሜና ችሎታ ግምት ውስጥ ማስገባት እንዲችል ክፍሉን ከመስጠቱ በፊት ትምህርቱን ማንበብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዎቹ ክፍሉን በሚገባ ተረድተው፣ በቅልጥፍና፣ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ በማጥበቅ፣ ድምፅን በመለዋወጥ፣ በተገቢው ቦታ ቆም በማለትና የራስን ተፈጥሮአዊ አነጋገር በመጠቀም እንዲያነብቡ መርዳት ይፈልጋል።
ክፍል ቁ. 3:- 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። ይህን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡ ተማሪዎች በአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ ከተዘረዘሩት መቼቶች መካከል አንዱን መምረጥ ይችላሉ፤ ወይም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ክፍላቸውን የሚያቀርቡበትን መቼት ይሰጣቸዋል። ተማሪዋ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኘውን ጭብጥ መጠቀምና ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል በሚስማማ መንገድ ማቅረብ ይኖርባታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪዋ ታማኝና ልባም ባሪያ ባዘጋጃቸው ጽሑፎች ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ማሰባሰብ ይኖርባታል። አዳዲስ ተማሪዎች ጭብጡ ብቻ የተሰጠባቸውን ክፍሎች ማቅረብ አይኖርባቸውም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ እንዴት እንደምታዳብርና የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉምና የክፍሉን ዋና ዋና ነጥቦች እንዲገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። ይህን ክፍል እንድታቀርብ የተመደበችው እህት ማንበብ የምትችል መሆን አለባት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል።
ክፍል ቁ. 4:- 5 ደቂቃ። ተማሪው የተሰጠውን ጭብጥ ማዳበር ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪው ታማኝና ልባም ባሪያ ባዘጋጃቸው ጽሑፎች ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ያሰባስባል። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ የጉባኤውን አድማጭ ግምት ውስጥ በማስገባት በንግግር መልክ ያቀርበዋል። ሆኖም ክፍሉ ለአንዲት እህት ከተሰጠ ለሦስተኛው ክፍል በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል። የኮከብ ምልክት ያለባቸው ክፍሎች በንግግር መልክ መቅረብ ያለባቸው ስለሆኑ ለወንድሞች ብቻ መሰጠት ይኖርባቸዋል።
ጊዜን መጠበቅ:- ክፍል የሚያቀርቡትም ሆኑ ምክር ሰጭው የተመደበላቸውን ጊዜ ማሳለፍ አይኖርባቸውም። ከቁጥር 2 እስከ 4 ያሉትን ክፍሎች የሚያቀርቡት ወንድሞች የተመደበላቸው ጊዜ ሲሞላ በዘዴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለ ንግግር ባሕርይ የሚናገረው የመክፈቻ ንግግር፣ ክፍል ቁጥር 1 ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርቡ ወንድሞች ሰዓት ካሳለፉ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይገባል። ሁሉም ሰዓታቸውን በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ጸሎትንና መዝሙርን ሳይጨምር ጠቅላላው ፕሮግራም 45 ደቂቃ ይፈጃል።
ምክር:- 1 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከእያንዳንዱ የተማሪ ንግግር በኋላ የንግግሩን ገንቢ ጎኖች አንስቶ አስተያየት ለመስጠት ከአንድ ደቂቃ የበለጠ ጊዜ መውሰድ አይኖርበትም። ዓላማው “ጥሩ ነው” ብሎ ለማለፍ ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ የተማሪው አቀራረብ ጥሩ የሆነበትን ምክንያት ለይቶ መጥቀስ ያስፈልገዋል። የእያንዳንዱን ተማሪ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከስብሰባው በኋላ ወይም በሌላ ጊዜ በግል ገንቢ የሆኑ ተጨማሪ ምክር መስጠት ይችላል።
ረዳት ምክር ሰጪ:- የሽማግሌዎች አካል ከትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተጨማሪ ረዳት ምክር ሰጭ ሆኖ የሚያገለግል ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ሊመርጥ ይችላል። የዚህ ወንድም ኃላፊነት ንግግር ቁጥር 1ን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ለሚያቀርቡ ወንድሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግል ምክር መስጠት ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እነዚህን ክፍሎች የሚያቀርቡ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ንግግራቸውን ባቀረቡ ቁጥር ምክር ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም። ይህ ዝግጅት ከ2003 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ማስተካከያ ሊደረግበት ይችላል።
ምክር መስጫ ነጥቦችን የያዘ ቅጽ:- በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
የቃል ክለሳ:- 30 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በየሁለት ወሩ የሚቀርበውን የቃል ክለሳ ይመራል። ክለሳው የሚደረገው የንግግር ባሕርይና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረቡ በኋላ ይሆናል። ክለሳው የሚደረገው፣ የክለሳውን ሳምንት ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት በቀረቡት ትምህርቶች ላይ ተመሥርቶ ነው።
ፕሮግራም
ጥር 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 1-6 መዝ. 34 (77)
የንግግር ባሕርይ፦ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ተማሪ አድርገን ስንቀበልህ ደስ ይለናል (be ገጽ 5 አን.1–ገጽ 8 አን. 1)
ቁ. 1፦ የአምላክን ቃል በማንበብ ተደሰት (be ገጽ 9 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 4:1-22
ቁ. 3፦ የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች እውነተኛ ክርስቲያኖችን የሚነኩት እንዴት ነው? (rs ገጽ 238 አን. 2, 3)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ አሁን ምን በማድረግ ላይ ይገኛል?
ጥር 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 7-11 መዝ. 93 (211)
የንግግር ባሕርይ፦ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብብ (be ገጽ 10 አን. 1–ገጽ 12 አን. 3)
ቁ. 1፦ “እናንተም እንዲሁ ሩጡ” (w01 1/1 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 9:9-31
ቁ. 3፦ ለሰዎች የምንሰብከው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የይሖዋ ምሥክሮች “የመጨረሻ ቀኖች” የጀመሩት በ1914 ነው የሚሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 239 አን. 1-4)
ጥር 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 12-15 መዝ. 55 (133)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥርት ያለ ንባብ (be ገጽ 83 አን. 1–ገጽ 84 አን. 1)
ቁ. 1፦ የተስፋ መቁረጥን ስሜት መቋቋም ትችላለህ! (w01 2/1 ገጽ 20-3)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 13:1-23
ቁ. 3፦ አሁን ያለንበት ሥርዓት ከጠፋ በኋላ በምድር ላይ የሚተርፍ ሰው ይኖር ይሆን? (rs ገጽ 240 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ አምላክ ይለወጣልን?
ጥር 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 16-21 መዝ. 52 (129)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥርት አድርጎ ማንበብ የሚቻልበት መንገድ (be ገጽ 84 አን. 2–ገጽ 85 አን. 3)
ቁ. 1፦ ጊዜ ይከንፋል (si ገጽ 278-9 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ w01 1/15 ገጽ 20 አን. 20–ገጽ 21 አን. 24
ቁ. 3፦ ዓለምን አንድ ሊያደርግ የሚችለው ምንድን ነው?
ቁ. 4፦ አምላክ ክፉዎችን ሳያጠፋ ይህን ያህል ጊዜ የቆየው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 240 አን. 5-7)
የካ. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 22-25 መዝ. 59 (139)
የንግግር ባሕርይ፦ ቃላትን አጥርቶ መናገር (be ገጽ 86 አን. 1-6)
ቁ. 1፦ “እንዴት እንደምታዳምጡ በጥንቃቄ አስቡ” (be ገጽ 13 አን. 1–ገጽ 14 አን. 4)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 22:15-40
ቁ. 3፦ በዘመናችን እያየናቸው ያሉት ነገሮች ስለ መጨረሻው ዘመን የተነገሩት ምልክቶች ስለመሆናቸው እንዴት እናውቃለን? (rs ገጽ 241 አን.2–ገጽ 242 አን. 1)
ቁ. 4፦ ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?
የካ. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 26-28 መዝ. 10 (27)
የንግግር ባሕርይ፦ አጥርቶ መናገር የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 87 አን. 1–ገጽ 88 አን. 3)
ቁ. 1፦ እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው? (w01 3/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 26:6-30
ቁ. 3፦ ዕፅ መውሰድ የማይኖርብኝ ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የሰብዓዊ ሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? (rs ገጽ 243 አን. 3–ገጽ 244 አን. 4)
የካ. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 1-4 መዝ. 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ የቃላት ትክክለኛ አጠራር—ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ጉዳይ (be ገጽ 89 አን. 1–ገጽ 90 አን. 2)
ቁ. 1፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የጊዜ መለኪያዎች (si ገጽ 279-80 አን. 7-13)
ቁ. 2፦ w01 2/15 ገጽ 25 አን. 10–ገጽ 26 አን. 14
ቁ. 3፦ ሰዎች የተፈጠሩት ጥቂት ዓመታት ከኖሩ በኋላ እንዲሞቱ ነበርን? (rs ገጽ 245 አን. 1-3)
ቁ. 4፦ ቁማር መጫወት ተገቢ ያልሆነው ለምንድን ነው?
የካ. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 5-8 መዝ. 33 (72)
የንግግር ባሕርይ፦ የቃላትን ትክክለኛ አጠራር ማሻሻል የሚቻልባቸው መንገዶች (be ገጽ 90 አን. 3–ገጽ 91)
የቃል ክለሳ
መጋ. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 9-12 መዝ. 87 (195)
የንግግር ባሕርይ፦ ቅልጥፍና (be ገጽ 93 አን. 1–ገጽ 94 አን. 3)
ቁ. 1፦ ንግግር ሲሰጥ፣ ውይይት ሲደረግና በትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ማዳመጥ (be ገጽ 15 አን. 1–ገጽ 16 አን. 5)
ቁ. 2፦ ማርቆስ 10:1-22
ቁ. 3፦ ከአምላክ ብርታት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ የዘላለም ሕይወት እናገኛለን ብለን ተስፋ ማድረግ የምንችለው በምን መሠረት ነው? (rs ገጽ 246 አን. 5-7)
መጋ. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 13-16 መዝ. 83 (187)
የንግግር ባሕርይ፦ ቅልጥፍናን ማሻሻል የሚቻልበት መንገድ (be ገጽ 94 አን. 4–ገጽ 96 አን. 2፣ በገጽ 95 ላይ የሚገኘውን ሣጥን አይጨምርም።)
ቁ. 1፦ መንፈሳዊ ገነት ምንድን ነው? (w01 3/1 ገጽ 8-11)
ቁ. 2፦ ማርቆስ 13:1-23
ቁ. 3፦ ወደፊት ሕይወት የማግኘቱ ተስፋ የሚፈጸመው እንዴት ነው? (rs ገጽ 246 አን. 8–ገጽ 247 አን. 2)
ቁ. 4፦ አምላክ ሰዎች በሚያደርጉት ጦርነት ለአንዱ ይወግናል?
መጋ. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 1-3 መዝ. 6 (13)
የንግግር ባሕርይ፦ የመንተባተብን ችግር መቋቋም (be በገጽ 95 ላይ ያለው ሣጥን)
ቁ. 1፦ “ጥበብን የሚያገኝ ሰው ደስተኛ ነው” (w01 3/15 ገጽ 25-8)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 3:1-22
ቁ. 3፦ ኢየሱስን ማምለክ ተገቢ ነውን?
ቁ. 4፦ * ከአገሩ ሕግ ጋር የሚስማማ ጋብቻ መመሥረት አስፈላጊ ነውን? (rs ገጽ 248 አን. 3–ገጽ 249 አን. 2)
መጋ. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 4-6 መዝ. 67 (156)
የንግግር ባሕርይ፦ ሐሳቡን በትክክል ለማስተላለፍና የሐሳብ ለውጥ ለማድረግ ቆም ማለት (be ገጽ 97 አን. 1–ገጽ 98 አን. 6)
ቁ. 1፦ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚረዱህ ይሰማሃልን? (w01 4/1 ገጽ 20-3)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 6:1-23
ቁ. 3፦ የመታሰቢያው በዓል ትርጉም ምንድን ነው? (rs ገጽ 265 አን.3–ገጽ 266 አን. 2)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች መለኮታዊ ጥበቃ ይደረግልናል ብለው መጠበቅ ይችላሉ?
መጋ. 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 7-9 መዝ. 22 (47)
የንግግር ባሕርይ፦ ለማጥበቅና የሌሎችን ሐሳብ ለመስማት ሲባል ቆም ማለት (be ገጽ 99 አን. 1–ገጽ 100 አን. 3)
ቁ. 1፦ “እግዚአብሔርን ፍራ፣ ትእዛዙንም ጠብቅ” (be ገጽ 272 አን. 1–ገጽ 275 አን. 3)
ቁ. 2፦ w01 3/15 ገጽ 18 አን. 17–ገጽ 19 አን. 20
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ እንደሆነ እንዴት እናውቃለን?
ቁ. 4፦ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚቀርበው ቂጣና ወይን ትርጉሙ ምንድን ነው? (rs ገጽ 266 አን. 3, 4)
ሚያ. 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 10-12 መዝ. 65 (152)
የንግግር ባሕርይ፦ ቁልፍ ቃላትን ወይም ሐረጎችን በተገቢው ሁኔታ ማጥበቅ (be ገጽ 101 አን. 1–ገጽ 102 አን. 3)
ቁ. 1፦ ‘ስለ ኢየሱስ መመሥከር’ (be ገጽ 275 አን. 4–ገጽ 278 አን. 4)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 10:1-22
ቁ. 3፦ ከጌታ ራት መካፈል የሚኖርባቸው እነማን ናቸው? (rs ገጽ 267 አን. 2, 3)
ቁ. 4፦ የመጀመሪያው ጋብቻ የተፈጸመው በየትኞቹ ሥርዓቶች መሠረት ነው? (rs ገጽ 249 አን. 3, 4)
ሚያ. 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 13-17 መዝ. 62 (146)
የንግግር ባሕርይ፦ ቁልፍ ቃላትን ወይም ሐረጎችን በተገቢው ቦታ የማጥበቅ ችሎታን ማሻሻል የሚቻልበት መንገድ (be ገጽ 102 አን. 4–ገጽ 104 አን. 3)
ቁ. 1፦ ‘ይህ የመንግሥት ምሥራች’ (be ገጽ 279 አን. 1–ገጽ 281 አን. 4)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 15:11-32
ቁ. 3፦ ራሳችንን ከአጋንንት ተጽእኖ መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ የመታሰቢያው በዓል መከበር የሚኖርበት በየስንት ጊዜው ነው? የሚከበረውስ መቼ ነው? (rs ገጽ 268 አን. 2, 3)
ሚያ. 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 18-21 መዝ. 80 (180)
የንግግር ባሕርይ፦ ዋና ዋና ነጥቦችን አጽንዖት ሰጥቶ ማንበብ (be ገጽ 105 አን. 1–ገጽ 106 አን. 1)
ቁ. 1፦ የወቅቶች መፈራረቅ የይሖዋ ጥበብ የተንጸባረቀበት ፍቅራዊ ዝግጅት ነው (si ገጽ 280 አን. 14-17)
ቁ. 2፦ w01 4/15 ገጽ 6 አን. 19–ገጽ 7 አን. 22
ቁ. 3፦ የትንሣኤ ተስፋ ሕይወታችንን የሚነካው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ * መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ በላይ ማግባትን ያወግዛልን? (rs ገጽ 249 አን. 5–ገጽ 250 አን. 5)
ሚያ. 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 22-24 መዝ. 2 (4)
የንግግር ባሕርይ፦ ተስማሚ የድምፅ መጠን—አድማጮችህን ግምት ውስጥ አስገባ (be ገጽ 107 አን. 1–ገጽ 108 አን. 4)
የቃል ክለሳ
ግን. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 1-4 መዝ. 32 (70)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅህን መጠን ማሻሻል የምትችለው እንዴት ነው? (be ገጽ 108 አን. 5–ገጽ 110 አን. 2)
ቁ. 1፦ የማስታወስ ችሎታህን ማሻሻል ትችላለህ (be ገጽ 17 አን. 1–ገጽ 18 አን. 5)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 2:1-25
ቁ. 3፦ አምላክ የአልኮል መጠጥ መጠጣትን ያወግዛልን?
ቁ. 4፦ * አምላክ ከትዳር ጓደኛ ተለያይቶ መኖርን ይፈቅዳልን? (rs ገጽ 251 አን. 1)
ግን. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 5-7 መዝ. 74 (168)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅህን መጠን እንደ ሁኔታው አስተካክል (be ገጽ 111 አን. 1–ገጽ 112 አን. 2)
ቁ. 1፦ ምንም ዓይነት አስተዳደግ ይኑርህ ስኬታማ መሆን ትችላለህ (w01 4/15 ገጽ 25-8)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 5:1-24
ቁ. 3፦ የሰው ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል የሚለው ትምህርት ምክንያታዊ ያልሆነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ * መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍቺና እንደገና ስለማግባት ያለው አመለካከት ምንድን ነው? (rs ገጽ 251 አን. 2-ገጽ 252 አን. 2)
ግን. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 8-11 መዝ. 25 (53)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅህን ፍጥነት መለዋወጥ (be ገጽ 112 አን. 3–ገጽ 113 አን. 1)
ቁ. 1፦ ‘ጥበብ ረጅም ዘመን ታኖረናለች’ (w01 5/15 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 10:16-42
ቁ. 3፦ በድሮ ጊዜ በወንድምና በእህት መካከል ይደረግ የነበረውን ጋብቻ አምላክ ለምን ፈቀደ? (rs ገጽ 252 አን. 3, 4)
ቁ. 4፦ ውጥረትን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ
ግን. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 12-16 መዝ. 1 (3)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅህን ቃና መለዋወጥ (be ገጽ 113 አን. 2–ገጽ 114 አን. 2)
ቁ. 1፦ ዓመት እና ቅዱሳን ጽሑፎች (si ገጽ 280-2 አን. 18-23)
ቁ. 2፦ w01 5/1 ገጽ 14 አን. 4–ገጽ 15 አን. 7
ቁ. 3፦ ‘የዓለም ክፍል አለመሆን’ ሲባል ምን ማለት ነው?
ቁ. 4፦ ትዳርን ለማሻሻል ምን ነገሮች ሊረዱ ይችላሉ? (rs ገጽ 253 አን. 1-4)
ሰኔ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 17-21 መዝ. 38 (85)
የንግግር ባሕርይ፦ በጋለ ስሜት መናገር (be ገጽ 115 አን. 1–ገጽ 116 አን. 4)
ቁ. 1፦ የማስታወስ ችሎታን ለማሻሻል የአምላክ መንፈስ የሚጫወተው ሚና (be ገጽ 19 አን. 1–ገጽ 20 አን. 2)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 20:1-23
ቁ. 3፦ ትዳርን ለማሻሻል ምን ነገሮች ሊረዱ ይችላሉ? (rs ገጽ 253 አን. 5-8)
ቁ. 4፦ በሃይማኖት መደራጀት አስፈላጊ ነውን?
ሰኔ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 1-4 መዝ. 42 (92)
የንግግር ባሕርይ፦ ለትምህርቱ የሚስማማ ግለት (be ገጽ 116 አን. 5–ገጽ 117 አን. 3)
ቁ. 1፦ በይሖዋ ላይ ያለህን እምነት አጠናክር (w01 6/1 ገጽ 7-10)
ቁ. 2፦ ሥራ 4:1-22
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ማርያም ከሚናገረው ምን ልንማር እንችላለን? (rs ገጽ 254 አን. 1-6)
ቁ. 4፦ አምላክ ማንኛውንም ዓይነት አምልኮ ይቀበላልን?
ሰኔ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 5-7 መዝ. 69 (160)
የንግግር ባሕርይ፦ ወዳጃዊ ስሜት ማንጸባረቅ (be ገጽ 118 አን. 1–ገጽ 119 አን. 5)
ቁ. 1፦ መናዘዝ ፈውስ ያስገኛል (w01 6/1 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ ሥራ 7:1-22
ቁ. 3፦ የይሖዋ ምሥክሮች ከሌሎች ሃይማኖቶች የሚለዩት በምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ማርያም ኢየሱስን ስትወልድ በእውነት ድንግል ነበረችን? (rs ገጽ 254 አን. 7–ገጽ 255 አን. 1)
ሰኔ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 8-10 መዝ. 73 (166)
የንግግር ባሕርይ፦ ስሜትን መግለጽ (be ገጽ 119 አን. 6–ገጽ 120 አን. 5)
ቁ. 1፦ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች እና መበለቶችን በመከራቸው መጠየቅ (w01 6/15 ገጽ 9-12)
ቁ. 2፦ w01 6/1 ገጽ. 12 አን. 1–ገጽ 13 አን. 5
ቁ. 3፦ ማርያም ዕድሜዋን በሙሉ ድንግል ሆና ኖራለችን? (rs ገጽ 255 አን. 2-ገጽ 256 አን. 1)
ቁ. 4፦ * በስብሰባዎች ላይ መገኘት ለመንፈሳዊ እድገት ወሳኝ የሆነው ለምንድን ነው?
ሰኔ 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 11-14 መዝ. 18 (42)
የንግግር ባሕርይ፦ አካላዊ መግለጫዎችን መጠቀም አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት (be ገጽ 121 አን. 1-4)
የቃል ክለሳ
ሐምሌ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 15-17 መዝ. 17 (38)
የንግግር ባሕርይ፦ አካላዊ መግለጫዎችን መጠቀም (be ገጽ 121 አን. 5–ገጽ 123 አን. 2)
ቁ. 1፦ ለማንበብ መትጋት የሚኖርብህ ለምንድን ነው? (be ገጽ 21 አን. 1–ገጽ 23 አን. 3)
ቁ. 2፦ ሥራ 15:1-21
ቁ. 3፦ የይሖዋን ሉዓላዊነት መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ ማርያም የእግዚአብሔር እናት ነበረችን? (rs ገጽ 256 አን. 2-4)
ሐምሌ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 18-21 መዝ. 12 (32)
የንግግር ባሕርይ፦ በአገልግሎት ላይ አድማጮችን ማየት (be ገጽ 124 አን. 1–ገጽ 125 አን. 4)
ቁ. 1፦ ጥርጣሬ እምነትህን እንዲያጠፋ አትፍቀድ (w01 7/1 ገጽ 18-21)
ቁ. 2፦ ሥራ 19:1-22
ቁ. 3፦ # ማርያም በተፀነሰችበት ጊዜ ንጽሕት ነበረችን? (rs ገጽ 257 አን. 1, 2)
ቁ. 4፦ ‘መንግሥቱን ማስቀደም’ ሲባል ምን ማለት ነው?
ሐምሌ 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 22-25 መዝ. 100 (222)
የንግግር ባሕርይ፦ ንግግር በምታቀርብበት ጊዜ አድማጮችህን ማየት (be ገጽ 125 አን. 5–ገጽ 127 አን. 1)
ቁ. 1፦ በእርግጥ ታጋሽ ነህን? (w01 7/15 ገጽ 21-3)
ቁ. 2፦ ሥራ 24:1-23
ቁ. 3፦ ዲያብሎስ ዕውን አካል ነውን?
ቁ. 4፦ # ማርያም ከነሥጋዊ አካሏ ወደ ሰማይ አርጋለችን? (rs ገጽ 257 አን. 3–ገጽ 258 አን. 1)
ሐምሌ 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 26-28 መዝ. 7 (19)
የንግግር ባሕርይ፦ በመስክ አገልግሎት ላይ የራስን ተፈጥሮአዊ አነጋገር መጠቀም (be ገጽ 128 አን. 1–ገጽ 129 አን. 1)
ቁ. 1፦ ዜሮ የሚባል ዓመት የለም (si ገጽ 282 አን. 24-6)
ቁ. 2፦ w01 7/1 ገጽ 14 አን. 5-8
ቁ. 3፦ ‘አማላጃችን ማርያም ሆይ’ ብሎ መጸለይ ተገቢ ነውን? (rs ገጽ 258 አን. 2-4)
ቁ. 4፦ ለሕይወት ስጦታ አክብሮት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ነሐሴ 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 1-4 መዝ. 45 (106)
የንግግር ባሕርይ፦ ከመድረክ ስትናገር የራስን ተፈጥሮአዊ አነጋገር መጠቀም (be ገጽ 129 አን. 2–ገጽ 130 አን. 1)
ቁ. 1፦ ትጉህ አንባቢ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? (be ገጽ 23 አን. 4–ገጽ 26 አን. 4)
ቁ. 2፦ ሮሜ 2:1-24
ቁ. 3፦ ከዚህ ቀደም በሕይወት ኖረህ ታውቃለህን?
ቁ. 4፦ በአንደኛው መቶ ዘመን የክርስቲያን ጉባኤ ለማርያም ልዩ አክብሮት ሰጥቷት ነበርን? (rs ገጽ 259 አን. 2–ገጽ 260 አን. 1)
ነሐሴ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 5-8 መዝ. 11 (29)
የንግግር ባሕርይ፦ ለሌሎች ስታነብብ የራስን ተፈጥሯዊ አነጋገር መጠቀም (be ገጽ 130 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ ‘ጻድቅ በረከት ያገኛል’ (w01 7/15 ገጽ 24-7)
ቁ. 2፦ ሮሜ 5:6-21
ቁ. 3፦ # በድንግል ማርያም ታምናላችሁ? (rs ገጽ 260 አን. 2-4)
ቁ. 4፦ በሪኢንካርኔሽን ማመን ይገባሃልን?
ነሐሴ 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 9-12 መዝ. 66 (155)
የንግግር ባሕርይ፦ የግል ንጽሕና ለመልእክታችን ውበት ይጨምርለታል (be ገጽ 131 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ ልማድ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለበጎ ተጠቀሙበት (w01 8/1 ገጽ 19-22)
ቁ. 2፦ w01 8/15 ገጽ 21 አን. 10–ገጽ 22 አን. 13
ቁ. 3፦ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በርዘውታልን?
ቁ. 4፦ ቂጣውና ወይኑ በምሥጢራዊ ሁኔታ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደምነት ይለወጣልን? (rs ገጽ 261 አን. 1–ገጽ 262 አን 3)
ነሐሴ 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 13-16 መዝ. 19 (43)
የንግግር ባሕርይ፦ የአንድ ሰው ጨዋነትና ጤናማ አስተሳሰብ በአለባበሱና በአጋጌጡ የሚንጸባረቀው እንዴት ነው? (be ገጽ 131 አን. 4–ገጽ 132 አን. 3)
የቃል ክለሳ
መስ. 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ቆሮንቶስ 1-9 መዝ. 23 (48)
የንግግር ባሕርይ፦ ሥርዓታማ አለባበስ ምን ጥቅም አለው? (be ገጽ 132 አን. 4–ገጽ 133 አን. 1)
ቁ. 1፦ የአጠናን ዘዴ (be ገጽ 27 አን. 1–ገጽ 31 አን. 2)
ቁ. 2፦ 1 ቆሮንቶስ 3:1-23
ቁ. 3፦ የዮሐንስ 6:53-57 ትርጉም ምንድን ነው? (rs ገጽ 262 አን. 4–ገጽ 263 አን. 1)
ቁ. 4፦ ድህነት ለስርቆት ማሳበቢያ ሊሆን ይችላልን?
መስ. 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ቆሮንቶስ 10-16 መዝ. 50 (123)
የንግግር ባሕርይ፦ አለባበሳችንና አበጣጠራችን ጥሩ ከሆነ ለሌሎች መሰናክል አንሆንም (be ገጽ 133 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ ለእድገትህ እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን አሸንፍ! (w01 8/1 ገጽ 28-30)
ቁ. 2፦ 1 ቆሮንቶስ 12:1-26
ቁ. 3፦ አምላክ በሰዎች ላይ ክፉ ነገር እንዲደርስ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የቁርባንን ሥርዓት ያቋቋመው ኢየሱስ ነውን? (rs ገጽ 263 አን. 2–ገጽ 265 አን. 2)
መስ. 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ቆሮንቶስ 1-7 መዝ. 77 (174)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ አቋቋምና በሥርዓት የተያዙ ጽሑፎች (be ገጽ 134 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ የወጣትነት ሕይወትህን የተሳካ አድርገው (w01 8/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ 2 ቆሮንቶስ 6:1–7:1
ቁ. 3፦ አንድ ክርስቲያን ለበላይ ባለ ሥልጣኖች ሊኖረው የሚገባው አመለካከት (rs ገጽ 269 አን. 1–ገጽ 270 አን. 2)
ቁ. 4፦ አምላክ በምድር ላይ እየደረሰ ያለው ብክለት ያሳስበዋልን?
መስ. 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ቆሮንቶስ 8-13 መዝ. 91 (207)
የንግግር ባሕርይ፦ ንግግር ስናቀርብ የሚሰማንን ፍርሃት መቀነስ የሚቻልበት መንገድ (be ገጽ 135 አን. 1–ገጽ 137 አን. 2)
ቁ. 1፦ ጥበብ ያለበት ውሳኔ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? (w01 9/1 ገጽ 27-30)
ቁ. 2፦ 2 ቆሮንቶስ 8:1-21
ቁ. 3፦ ሰው ሲሞት ነፍስ ምን ትሆናለች?
ቁ. 4፦ አንድ ክርስቲያን በጦርነት በመካፈል ረገድ ሊኖረው ስለሚገባው አቋም መመሪያ ሆነው የሚያገለግሉት የትኞቹ ጥቅሶች ናቸው? (rs ገጽ 270 አን. 3–ገጽ 271 አን. 2)
መስ. 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ገላትያ 1-6 መዝ. 71 (163)
የንግግር ባሕርይ፦ መረጋጋት የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 137 አን. 3–ገጽ 138 አን. 3)
ቁ. 1፦ በታሪክ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ዓመታት ያላቸው ጥቅም (si ገጽ 282-3 አን. 27-30)
ቁ. 2፦ w01 9/1 ገጽ 15 አን. 8–ገጽ 17 አን. 11
ቁ. 3፦ የጥንቶቹ እስራኤላውያን ጦርነት እንዲያደርጉ አምላክ የፈቀደላቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 271 አን. 3–ገጽ 272 አን. 3)
ቁ. 4፦ የአምላክ መንግሥት እየገዛ እንዳለ ማወቅ የምንችልበት መንገድ
ጥቅ. 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤፌሶን 1-6 መዝ. 92 (209)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅ ማጉያ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት (be ገጽ 139 አን. 1–ገጽ 140 አን. 1)
ቁ. 1፦ ጥናት የሚያስገኘው በረከት (be ገጽ 31 አን. 3–ገጽ 32 አን. 3)
ቁ. 2፦ ኤፌሶን 2:1-22
ቁ. 3፦ በአምላክ ለማመን የሚያስችል በቂ ምክንያት አለ
ቁ. 4፦ አንድ ክርስቲያን በፖለቲካ ጉዳዮች በመካፈል ረገድ ሊኖረው ስለሚገባው አመለካከት መመሪያ ሆነው የሚያገለግሉት የትኞቹ ጥቅሶች ናቸው? (rs ገጽ 272 አን. 4–ገጽ 273 አን. 3)
ጥቅ. 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ፊልጵ. 1–ቆላ. 4 መዝ. 44 (105)
የንግግር ባሕርይ፦ በማይክሮፎን በሚገባ ተጠቀሙ (be ገጽ 140 አን. 2–ገጽ 142 አን. 1)
ቁ. 1፦ ‘ቀና በሆነው መንገድ’ ሂድ (w01 9/15 ገጽ 24-8)
ቁ. 2፦ ፊልጵስዩስ 2:1-24
ቁ. 3፦ አንድ ክርስቲያን የብሔራዊ ስሜት መግለጫ በሆኑ ሥነ ሥርዓቶች ላይ መካፈልን በተመለከተ ሊኖረው ስለሚገባው አቋም መመሪያ ሊሆኑ የሚችሉት ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው? (rs ገጽ 273 አን. 4–ገጽ 275 አን. 1)
ቁ. 4፦ ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ጥቅ. 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ተሰ. 1–2 ተሰ. 3 መዝ. 94 (212)
የንግግር ባሕርይ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሞ መልስ መስጠት (be ገጽ 143 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ ይሖዋ ለጊዜ ያለው አመለካከት (si ገጽ 283-4 አን. 31-3)
ቁ. 2፦ w01 10/15 ገጽ 23 አን. 6–ገጽ 24 አን. 9
ቁ. 3፦ ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ገለልተኞች በመሆናቸው ለሌሎች ሰዎች ደኅንነት ደንታ ቢሶች ናቸው ማለት ነውን? (rs ገጽ 275 አን. 2)
ጥቅ. 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ:- 1 ጢሞ. 1–2 ጢሞ. 4 መዝ. 21 (46)
የንግግር ባሕርይ፦ መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ረገድ ማሻሻል የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 144 አን. 1-4)
የቃል ክለሳ
ኅዳር 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ቲቶ 1-ፊልሞና መዝ. 26 (56)
የንግግር ባሕርይ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጠው እንዲከታተሉ ማበረታታት (be ገጽ 145-6)
ቁ. 1፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ምርምር ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 33 አን. 1–ገጽ 35 አን. 2)
ቁ. 2፦ ፊልሞና 1-25
ቁ. 3፦ ፍጹም ሆኖ ለዘላለም መኖር አሰልቺ ነውን?
ቁ. 4፦ ይሖዋ የሚለው ስም በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ለምን ገባ? (rs ገጽ 277 አን. 5–ገጽ 278 አን. 2)
ኅዳር 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕብራውያን 1-8 መዝ. 99 (221)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ የማስተዋወቅ አስፈላጊነት (be ገጽ 147 አን. 1–ገጽ 148 አን. 2)
ቁ. 1፦ ሄኖክ ፈሪሃ አምላክ በሌለው ዓለም ውስጥ አካሄዱን ከአምላክ ጋር አድርጓል (w01 9/15 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ ዕብራውያን 2:1-18
ቁ. 3፦ # ‘እናንተ የራሳችሁ መጽሐፍ ቅዱስ አላችሁ’ ለሚሉ ሰዎች መልስ መስጠት (rs ገጽ 279 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ በትንሣኤ የሚነሱ ሰዎች እንደ ሥራቸው ፍርድ የሚሰጣቸው እንዴት ነው?
ኅዳር 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕብራውያን 9-13 መዝ. 61 (144)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ለማስተዋወቅ ተስማሚ የሆኑ ሐሳቦችን መምረጥ (be ገጽ 148 አን. 3–ገጽ 149 አን. 2)
ቁ. 1፦ ታማኝ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? (w01 10/1 ገጽ 20-3)
ቁ. 2፦ ዕብራውያን 9:11-28
ቁ. 3፦ የአምላክ ሰማያዊ ፍጥረታት የተደራጁ ናቸው? (rs ገጽ 280 አን. 2, 3)
ቁ. 4፦ አምላክን የሚያስከብሩ ባሕርያትን ማንጸባረቅ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
ኅዳር 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ያዕቆብ 1-5 መዝ. 79 (177)
የንግግር ባሕርይ፦ ተገቢውን ስሜት በሚያንጸባርቅ መንገድ ማንበብ (be ገጽ 150 አን. 1, 2)
ቁ. 1፦ በጊዜ ሒደት ውስጥ የተለያዩ ክስተቶች የተፈጸሙበትን ዘመን ማስላት (si ገጽ 284-5 አን. 1-4)
ቁ. 2፦ w01 11/1 ገጽ 12 አን. 15–ገጽ 13 አን. 19
ቁ. 3፦ ልክን ማወቅ የሚያስገኘው ጥቅም
ቁ. 4፦ አምላክ በድሮ ጊዜ በምድር ላይ ለነበሩት አገልጋዮቹ መመሪያዎችን ያስተላልፍ የነበረው እንዴት ነው? (rs ገጽ 280 አን. 4–ገጽ 281 አን. 1)
ታኅ. 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ጴጥ. 1–2 ጴጥ. 3 መዝ. 36 (81)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛዎቹን ቃላት ማጉላት (be ገጽ 150 አን. 3–ገጽ 151 አን. 2)
ቁ. 1፦ ለምርምር የሚረዱ ሌሎች ጽሑፎችን አጠቃቀም ማወቅ (be ገጽ 35 አን. 3–ገጽ 38 አን. 4)
ቁ. 2፦ 1 ጴጥሮስ 1:1-16
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች የተደራጀ ሕዝብ እንደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያልን? (rs ገጽ 282 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ የክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ሕይወታችንን ሊነካ የሚገባው እንዴት ነው?
ታኅ. 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዮሐንስ 1–ይሁዳ መዝ. 41 (89)
የንግግር ባሕርይ፦ ለማጉላት የሚረዱ ዘዴዎች (be ገጽ 151 አን. 3–ገጽ 152 አን. 5)
ቁ. 1፦ ሕሊናህን ጠብቅ (w01 11/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ 1 ዮሐንስ 3:1-18
ቁ. 3፦ በሴቶች ላይ ለሚደርሰው በደል መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ምክንያት ተደርጎ ሊጠቀስ የማይገባው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች በተለያዩ የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተሰበጣጥረው የሚገኙ ናቸውን? (rs ገጽ 282 አን. 5-ገጽ 283 አን. 2)
ታኅ. 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 1-6 መዝ. 97 (217)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ከነጥቡ ጋር ማገናዘብ (be ገጽ 153 አን. 1–ገጽ 154 አን. 2)
ቁ. 1፦ የኖኅ እምነት ዓለምን ይኮንናል (w01 11/15 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ ራእይ 2:1-17
ቁ. 3፦ የሚታየው የይሖዋ ድርጅት በዘመናችን እንዴት ተለይቶ ሊታወቅ ይችላል? (rs ገጽ 283 አን. 3-9)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ገናን ማክበር የማይኖርባቸው ለምንድን ነው?
ታኅ. 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 7-14 መዝ. 3 (6)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሱ ከነጥቡ ጋር ያለውን ዝምድና ግልጽ ማድረግ (be ገጽ 154 አን. 3–ገጽ 155 አን. 4)
ቁ. 1፦ መንፈሳዊ የልብ ድካም እንዳይዝህ መከላከል ትችላለህ (w01 12/1 ገጽ 9-13)
ቁ. 2፦ w01 12/15 ገጽ 17 አን. 10–ገጽ 18 አን. 13 (የግርጌ ማስታወሻውን ጨምሮ)
ቁ. 3፦ የእኩዮችን ተፅዕኖ መቋቋም የሚቻልበት መንገድ
ቁ. 4፦ ለይሖዋ ድርጅት እንዴት አክብሮት ልናሳይ እንችላለን? (rs ገጽ 284 አን. 1-5)
ታኅ. 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 15-22 መዝ. 8 (21)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ተጠቅሞ ማስረዳት (be ገጽ 155 አን. 5–ገጽ 156 አን. 4)
የቃል ክለሳ
ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
ጊዜ በፈቀደልህ መጠን የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የተሰጡ መልሶችን ስታቀርብ ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።