የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/02 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 10/02 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት በማድረግ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። ኅዳር:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ሌላ የቆየ ጽሑፍ ልናበረክትላቸው እንችላለን። በጉባኤያችሁ ውስጥ የቆዩ ጽሑፎች ከሌሉ ከአጎራባች ጉባኤዎች መጠየቅ ትችላላችሁ። ታኅሣሥ:- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። በአማራጭነት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባሉትን መጻሕፍት መጠቀም ትችላላችሁ። ጥር:- ጉባኤው ያለውን ማንኛውንም ከ1988 በፊት የታተመ ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። እነዚህ ጽሑፎች በጉባኤያችሁ ውስጥ ከሌሉ ከአጎራባች ጉባኤዎች ጠይቁ። የእንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በክልላቸው ውስጥ ባሉባቸው ጉባኤዎች የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን መጽሐፍ ሊያበረክቱ ይችላሉ።

◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ ያለው አባሪ “የ2003 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።

◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2003 ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 27 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ ወደፊት በማስታወቂያ ይነገራል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት፣ የወረዳ ወይም ልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት እሁድ ግንቦት 4 ማቅረብ ይችላሉ። ማንኛውም ጉባኤ ከሚያዝያ 27, 2003 በፊት ልዩ የሕዝብ ንግግሩን ማቅረብ አይኖርበትም።

◼ የኅዳር ንቁ! መጽሔት “የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለው ኤድስ የሚገታበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?” የሚል ርዕስ ይዞ ይወጣል። ይህ ርዕሰ ጉዳይ የብዙ ሰዎችን ትኩረት መሳቡ ስለማይቀር በርከት ያሉ ቅጂዎች እንዲታተሙ አዝዘናል። ስለዚህ ጉባኤዎች M-202 ቅጽ በመጠቀም አሁኑኑ ተጨማሪ ቅጂዎች እንድታዝዙ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን።

◼ የጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓት ከጥር 1 ጀምሮ የሚቀየር ከሆነ የጉባኤው ጸሐፊ የጉባኤ ስብሰባዎች መረጃ እና የመጋበዣ ወረቀት ማዘዣ ቅጽ (S-5) በመላክ ለውጡን ለቅርንጫፍ ቢሮው ማሳወቅ ይገባዋል። አስፈላጊ ከሆነ በዚያው ቅጽ ተጠቅሞ አዲስ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ማዘዝ ይቻላል። መጋበዣ ወረቀት ማዘዝ የሚገባችሁ እንዲደርሳችሁ ከምትፈልጉበት ጊዜ ቢያንስ ከስምንት ሳምንት በፊት መሆን አለበት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ