የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/03 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 13 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 27 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 1/03 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥር 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 97 (217)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የታኅሣሥ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 2002 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ቢሆንም ሁለተኛውንም መጽሔት አያይዞ ያበረክታል።

15 ደቂቃ:- የእውነትን አምላክ ምሰሉት። አንድ ሽማግሌ በየካቲት 2000 ንቁ! ገጽ 12ና 13 ላይ የሚገኘውን “መዋሸት-ስህተት የማይሆንበት ሁኔታ ሊኖር ይችላልን?” የሚለውን ርዕስ በንግግር ያቀርበዋል። በይበልጥ ከ3-6 እና ከ9-10 ባሉት አንቀጾች ላይ አተኩር፤ እንዲሁም አንዳንድ ቁልፍ የሆኑ ጥቅሶችን አንብብ። ቅጾችን ስንሞላ እንኳን መጠንቀቅ እንዳለብን ግለጽ። በመጨረሻም የሚከተሉትን የክለሳ ጥያቄዎች መጠየቅ ይቻላል:- ይሖዋን ሙሉ በሙሉ ልንታመንበት የምንችለው ለምንድን ነው? (ቲቶ 1:2)፤ ውሸትን የጀመረው ማን ነው? (ዮሐ. 8:44)፤ ይሖዋ መዋሸትን የሚመለከተው እንዴት ነው? (ምሳሌ 6:16, 19)፤ ንስሐ የማይገቡ ውሸታሞች ምን ይደርስባቸዋል? (መዝ. 5:6፤ ራእይ 22:15)፤ የእውነት አምላክ የተወልንን ምሳሌ ለመኮረጅ ስንጥር ቁርጥ ውሳኔያችን ምን መሆን አለበት? (ማቴ. 5:37፤ መዝ. 97:10፤ ዕብ. 13:18፤ ኤፌሶን 4:15, 25)።

20 ደቂቃ:- “ራሳችንን ስንወስን ከገባነው ቃል ጋር ተስማምቶ መኖር።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 3ን ከተወያያችሁ በኋላ ከአንድ የጎለመሰ ወጣት ወይም በአሥራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኝ የተጠመቀ ልጅ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። ከተጠመቀበት ጊዜ አንስቶ ምን ዓይነት ፈተናዎች ገጥመውታል? እነዚህን ፈተናዎች ለማሸነፍ የረዳው ምንድን ነው? ሕይወቱን ለይሖዋ በመወሰኑ ምን ጥቅም አግኝቷል?

መዝሙር 14 (34) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34 (77)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ እየመረመርክ ነውን? በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ሁሉም ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2003 የተባለውን ቡክሌት በሚገባ እንዲጠቀሙበት አበረታታቸው። በቡክሌቱ ላይ ከገጽ 3-4 ከሚገኘው መቅድም ውስጥ በአንዳንድ ሐሳቦች ላይ ተወያዩ። ቤተሰቦች በአንድነት በዕለቱ ጥቅስ ላይ እንዴት መወያየት እንደሚችሉ የሚያሳዩ ሐሳቦችን ጠቁም። በዕለቱ ጥቅስ ላይ በየዕለቱ መወያየት ያለውን ጥቅም ለማሳየት ለሚቀጥለው ወር ከተዘጋጁት ጥቅሶችና ሐሳቦች ውስጥ በሁለት ወይም በሦስቱ ላይ ተወያዩ። አንድ ባልና ሚስት በዕለቱ ጥቅስ ላይ ሲወያዩ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

22 ደቂቃ:- “ንጹሑን ልሳን ለሌሎች አስተምሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 6 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አንድ ጥሩ ችሎታ ያለው አስፋፊ በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ 4 ላይ ባሉት ሐሳቦች ተጠቅሞ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት በሩ ላይ እንደቆመ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲያስጀምር የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሠርቶ ማሳያው ላይ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ከተባለው ብሮሹር ውስጥ በአንድ አንቀጽ ላይ ይወያያሉ። አስፋፊው በቀጣዩ አንቀጽ ላይ የተመሠረተ ጥያቄ ከጠየቀ በኋላ በሚቀጥለው ጉብኝት ወቅት ለጥያቄው መልስ እንደሚሰጥ በመናገር ይደመድማል። ሁሉም ተመላልሶ መጠየቅ ከሚያደርጉላቸው ውስጥ በዚህ ዘዴ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሊጀምሩ የሚችሉ ይኖሩ እንደሆነ እንዲያስቡበት አበረታታቸው።

መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 42 (92)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን ለመጽሐፍ ጥናታቸው የበላይ ተመልካች እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የታኅሣሥ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 22 (የእንግሊዝኛ) ንቁ! ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ የቤቱ ባለቤት መጽሔት አልቀበልም የሚል ሲሆን በሁለተኛው ሠርቶ ማሳያ ግን ይቀበላል። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው ሲደመድም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት ለቤቱ ባለቤት ያበረክትለታል። መጽሔት ላበረከትንላቸው ሰዎች ይህን ትራክት ከሰጠናቸው እንዴት በቀላሉ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ እንደምንችል በአጭሩ አብራራ።​—⁠የኅዳር 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 አንቀጽ 10ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- የአመስጋኝነትን መንፈስ አዳብሩ። በየካቲት 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 3-7 ላይ ተመሥርቶ ዋና ዋና ሐሳቦችን በመከለስ የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 71 (163) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 33 (72)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በጥያቄ ሣጥኑ ላይ ተወያዩበት።

12 ደቂቃ:- እምነታቸውን ኮርጁ። ይሖዋን በትሕትናና በታማኝነት ለብዙ ዓመታት ላገለገለ አንድ የጉባኤ ሽማግሌ ቃለ ምልልስ አድርግ። (ዕብ. 13:7) እውነትን የሰማው እንዴት ነው? ከእውነት ጎን ለመቆም ሲል ምን ምን ፈተናዎችን መቋቋም ነበረበት? እድገት ለማድረግ የረዱት የትኞቹ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ወይም ማበረታቻዎች ናቸው? በጉባኤ ውስጥ የበላይ ተመልካች ሆኖ ለማገልገል የሚያስችለውን ብቃት ለማሟላት ምን አድርጓል? (1 ጢ⁠ሞ. 3:1) የጉባኤ ኃላፊነቶችን ከሰብዓዊ ሥራና ከቤተሰብ ኃላፊነቶች ጋር በሚዛናዊነት ለማስኬድ የረዳው ምንድን ነው? (1 ጢ⁠ሞ. 5:8) በጉባኤው ውስጥ ሌሎችን ለመርዳት ያገኘውን ልዩ መብት እንዴት ይመለከተዋል?

18 ደቂቃ:- “ትሕትና የሚጠይቅ ሥራ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ አንድ ሰው ቢያፌዝብን፣ ቢያመናጭቀን፣ ግብግብ ቢፈጥር ወይም ቢቆጣ ምን ዓይነት ምላሽ መስጠት እንዳለብን አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ከተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 1160 አንቀጽ 3 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ