የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
የካቲት 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 (4)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የካቲት 24 የሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም በሶቪዬት ሕብረት ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በፈተና ወቅት ያሳዩት ጽናት የተባለውን የቪዲዮ ፊልም ተመልክተው እንዲመጡ አበረታታ። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2003 ንቁ! መጽሔት ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ቢሆንም ሌላውንም መጽሔት አያይዞ ያበረክታል።
35 ደቂቃ:- “የተሟላ ምሥክርነት ስጡ” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚያቀርበው። ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ በመጋቢትና በሚያዝያ ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ አበረታታ። ባለፈው የመታሰቢያው በዓል ወቅት ረዳት አቅኚ የነበሩ አስፋፊዎች አንዳንድ ሐሳቦችን እንዲናገሩ ጋብዝ። በረዳት አቅኚነት ለማገልገል ፕሮግራማቸውን ያመቻቹት እንዴት ነው? ይህስ ምን ጥረትና ማስተካከያዎችን ማድረግ ጠይቆባቸዋል? ረዳት አቅኚ ሆነው በማገልገላቸው ምን ዓይነት ደስታና በረከቶች አግኝተዋል? በገጽ 4 ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ የቀረቡትን የናሙና ፕሮግራሞች ከልስ። የረዳት አቅኚነት ማመልከቻ ቅጽ ከስብሰባው በኋላ ማግኘት እንደሚቻል ተናገር።
መዝሙር 67 (156) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በመጋቢት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች በመጠቀም እውቀት መጽሐፍን ለማበርከት የሚያስችሉ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን ተናገር። ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ግብ እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ:- “ቤትህን በፈቃደኝነት ልታቀርብ ትችላለህ?” የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካች የሚያቀርበው ንግግር። በሚያዝያ 2001 እና በየካቲት 1990 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጡት የጥያቄ ሣጥኖች ውስጥ አንዳንድ ሐሳቦችን ተናገር። ጉባኤው ስንት መጽሐፍ ጥናቶች እንዳሉትና አማካይ ተሰብሳቢያቸው ስንት እንደሆነ ተናገር። በቤታቸው የመጽሐፍ ጥናት የሚደረግ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች እነርሱና ቤተሰባቸው እንዴት እንደተጠቀሙ እንዲናገሩ አድርግ። ቤታቸውን ለመጽሐፍ ጥናት መሰብሰቢያነት ማቅረብ የሚፈልጉ አስፋፊዎች ለሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ማሳወቃቸው ተገቢ ነው።
20 ደቂቃ:- “ቅድሚያ የምትሰጡት ለምን ነገሮች ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአገልግሎት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ሁኔታዎቻቸውን ማስተካከል የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አስቀድመህ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አዘጋጅ።
መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 34 (77)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የየካቲት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የጥር 15 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 22 (የእንግሊዝኛ) ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ቢሆንም ሌላውንም መጽሔት አያይዞ ያበረክታል።
10 ደቂቃ:- “በተገቢው ጊዜ የተሰጠ ማበረታቻ።” አንድ ሽማግሌ በንግግር ያቀርበዋል። አገልግሎት ያቆሙትን ለመርዳት የሚደረገው ልዩ ጥረት ይሖዋ ለሕዝቦቹ ያለውን ፍቅራዊ አሳቢነት እንደሚያሳይ ጎላ አድርገህ ተናገር።
25 ደቂቃ:- “በሶቪዬት ሕብረት የተፈጸመውን ሁኔታ የሚያሳይ ልብ የሚነካ ፊልም!” በርዕሱ ውስጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም በሶቪዬት ሕብረት ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በፈተና ወቅት ያሳዩት ጽናት በተባለው የቪዲዮ ፊልም በቀጥታ ከአድማጮች ጋር ውይይት ጀምር። አስፋፊዎች ለመጨረሻው ጥያቄ በርከት ያሉ ሐሳቦች መስጠት እንዲችሉ ጊዜህን በጥንቃቄ ከፋፍለህ ተጠቀምበት። ስትደመድም በ2002 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 192 ላይ ያለውን ሣጥን አንብብ።
መዝሙር 26 (56) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 8 (21)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የመንግሥት አዳራሽ ቤተ መጻሕፍትን በሚመለከት የተደረገ አዲስ ዝግጅት” የሚለውን ርዕስ በአጭሩ አቅርብ። የቤተ መጻሕፍቱ ኃላፊ ሆኖ የሚያገለግለው ማን እንደሆነ ተናገር።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- “መጨረሻው እየቀረበ በሄደ መጠን ጤናማ አስተሳሰብ ይኑራችሁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 3, 4ን ስትወያዩ አስፋፊዎች በአሁኑ ወቅት ያሏቸውን መንፈሳዊ ግቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። አምላክን አምልክ (የእንግሊዝኛ) ከተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 176 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ተናገር።
መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።