የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/03 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 3/03 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት:- እውቀት መጽሐፍ የሚበረከት ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ይበረከታሉ። የምናነጋግራቸው ሰዎች ለዓለም አቀፉ ሥራ ድጋፍ መስጠት ከፈለጉ የገንዘብ መዋጮ ማድረግ እንደሚችሉ ልንነግራቸው ይገባል። ፍላጎት ላላ​ቸው ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። ሰኔ:- እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር ይበረከታል። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ጉባኤው ያለውን ሌላ ብሮሹር ማበርከት ይቻላል።

◼ በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ሆነው ማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች ከአሁኑ እቅድ ማውጣትና ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው ማስገባት አለባቸው። ይህም ሽማግሌዎች አስፈላጊውን የመስክ አገልግሎት ዝግጅት እንዲያመቻቹ እንዲሁም የመጽሔቶችና የሌሎች ጽሑፎች በቂ አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ ያስችላቸዋል። በረዳት አቅኚነት እንዲያገለግሉ የተፈቀደላቸው ሁሉ ስማቸው ለጉባኤው መነበብ አለበት።

◼ በየሦስት ወሩ ይወጣ የነበረው የትግርኛ ንቁ! መጽሔት መታተም አቁሟል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ