ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 30, 2003 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 5 እስከ ሰኔ 30, 2003 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርያት
1. ድምፅን እየለዋወጡ መናገር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ድምፅን መለዋወጥ የሚቻለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 111 ሣጥን፤ ገጽ 112 ሣጥን]
2. አንድ ተናጋሪ የሚያቀርበውን ትምህርት ከልብ የሚያምንበትና ይሖዋን የሚወድ ቢሆንም እንኳ በጋለ ስሜት እንዳይናገር ሊያግደው የሚችለው ምንድን ነው? [be ገጽ 115 አን. 3-4፤ ገጽ 116 አን. 1]
3. አንድ ሰው ንግግር ሲያቀርብ ወዳጃዊ ስሜት እንዲያሳይ ምን ሊረዳው ይችላል? ይህስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 119 አን. 1-4]
4. በንግግር ላይ ተስማሚ የሆነ ግለት፣ ፍቅራዊ ስሜትና ሌሎች ስሜቶችን ማሳየት የተመካው በምን ላይ ነው? [be ገጽ 120 አን. 2-5]
5. እውነት ወይም ሐሰት:- አካላዊ መግለጫዎች ፋይዳ የሚኖራቸው አድማጮች ወደ አንተ የሚያዩ ከሆነ ብቻ ነው። አብራራ። [be ገጽ 121 አን. 3]
ንግግር ቁ. 1
6. ኢዮስያስ መጥፎ የልጅነት ሕይወት ያሳለፈ ቢሆንም ትክክለኛ ጎዳና እንዲከተል የረዳው ምንድን ነው? (2 ዜና 34:1, 2) [w 01 4/15 ገጽ 26 አን. 5 እስከ ገጽ 27 አን. 5፤ ገጽ 28 አን. 4]
7. የምሳሌ 9:7, 8ሀ ትርጉም ምንድን ነው? ይህስ በመስክ አገልግሎት ላይ በሥራ ሊውል የሚችለው እንዴት ነው? [w 01 5/15 ገጽ 29 አን. 4-5]
8. ይሖዋ እስራኤላውያንን “እንዳትረሳ ተጠንቀቅ” ሲላቸው ምን ማለቱ ነበር? እኛስ የመርሳትን ባሕርይ ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው? (ዘዳ. 4:9፤ 8:11) [be ገጽ 19 አን. 3 እስከ ገጽ 20 አን. 2]
9. መዝሙር 32:1, 5 እና መዝሙር 51:10, 15 ላይ ሠፍረው የሚገኙት የዳዊት ቃላት አንድ ሰው ለፈጸመው ከባድ ኃጢአት ልባዊ ንስሐ ከገባ በኋላ የከንቱነት ስሜት ሊሰማው እንደማይገባ የሚያሳዩት እንዴት ነው? [w 01 6/1 ገጽ 30 አን. 1-3]
10. ጳውሎስ በ1 ጢሞቴዎስ 5:3-16 ላይ ችግረኞችን ስለ መንከባከብ ከሰጠው መመሪያ ምን ትምህርት ማግኘት ይቻላል? [w 01 6/15 ገጽ 11 አን. 1]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ዮሐንስ 3:3 ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው መሠረት ኢየሱስ ስለ ‘ዳግመኛ መወለድ’ ሲናገር ምን ማመልከቱ ነበር? [w 95 7/1 ገጽ 9-10 አን. 4-5]
12. ኢየሱስ የቀሰመውን ትምህርት በምን መንገድ ተጠቅሞበታል? ከዚህስ ምን ጠቃሚ ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (ዮሐንስ 7:15-18) [w 96 2/1 ገጽ 9-10 አን. 4-7]
13. በአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ላይ ከዮሐንስ 7:53 እስከ 8:11 ጭማሪ እንደሆነ ተደርጎ የቀረበው ለምንድን ነው?
14. ኢየሱስ ወደ ሰማይ በወጣበት መንገድ ‘እንዲሁ የሚመጣው’ እንዴት ነው? (ሥራ 1:11) [w 90 6/1 ገጽ 11 አን. 5]
15. ሥራ 5:13 ላይ በተገለጸው መሠረት ‘ከሌሎች ማንም [ደቀ መዛሙርቱን] ሊተባበራቸው ያልደፈረው’ ለምንድን ነው?