ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሰኔ:- እውቀት መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር ይበረከታል። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው በጉባኤው ውስጥ የሚገኝ ሌላ ብሮሹር ማበርከት ይቻላል። ሐምሌ፣ ነሐሴ እና መስከረም:- ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ”፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት . . .፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ—ሃው ቱ አቴይን ኢት? እና የሙታን መናፍስት —ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም:- እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ:- ላይፍ —ሃው ዲድ ኢት ጌት ሂር? ባይ ኢቮሉሽን ኦር ባይ ክሪኤሽን?