የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/03 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥቅምት 13 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 27 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 10/03 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥቅምት 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 96 (215)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 2003 ንቁ! መጽሔቶችን በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሕያው ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ የመጽሔት ደንበኛ ለሆነ ሰው ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግለት የሚያሳይ ይሁን። አስፋፊው በመጽሔቱ ላይ “በሚቀጥለው እትማችን” በሚለው ሣጥን ውስጥ የቀረቡትን ርዕሶች በማሳየት ለሚቀጥለው ቀጠሮ መሠረት ይጥላል።​—⁠የጥቅምት 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 12 አን. 7ና 8ን ተመልከት።

20 ደቂቃ:- “ይሖዋን በደስታ አገልግሉት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (ሁሉም ለዚህ ውይይት የጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ይዘው መምጣት አለባቸው።) በአንቀጽ 4 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ በኅዳር ወር የምናበረክተው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹርና እውቀት መጽሐፍን መሆኑን ተናገር። በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ከተጠቀሱት አቀራረቦች መካከል አንዱን በአጭሩ ተናገር። ከዚያም አስፋፊዎች ይህንን አቀራረብ ሲለማመዱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም አገልግሎት ከመውጣታቸው በፊት በደምብ እንዲዘጋጁ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ማስጠናት በረከት ያስገኛል። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆኑ ርዕሶች ላይ ደረጃ በደረጃ የሚደረገውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስመልክቶ ከጽሑፎቻችን ላይ የተወሰኑ ተሞክሮዎችን ተናገር። (የመጋቢት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 6፤ የ1998 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 55-​60) አድማጮች ከተሞክሮዎቹ ምን ጠቃሚ ሐሳቦችን እንዳገኙና ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ማስጠናት ያለውን ጥቅም እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 76 (172) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 39 (86)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ አዲሱ የአገልግሎት ዓመት ከጀመረ በኋላ ያለውን የጉባኤውን የአገልግሎት ሪፖርት ይከልሳል። የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን ስለተደረገው እንቅስቃሴ ተናገር፤ እንዲሁም ከቤት ወደ ቤት ማገልገልን አበረታታ።

10 ደቂቃ:- “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም” የሚለውን ተወያዩበት።

20 ደቂቃ:- “ስብሰባዎችን በሰዓቱ ጀምራችሁ በሰዓቱ ጨርሱ።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። ሁሉንም አንቀጾች አንብብ።

መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 61 (144)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የጥቅምት ወር የመስክ አገልገሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የነሐሴ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 8, 2003 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሕያው ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “ፍላጎት የለኝም” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 16ን ተመልከት።

20 ደቂቃ:- የመንፈስን ሰይፍ ተጠቀሙ። (ኤፌ. 6:17) በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 143-4 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። (1) ለሚቀርቡልን ጥያቄዎች መልስ ስንሰጥ በመጽሐፍ ቅዱስ የምንጠቀመው ለምንድን ነው? (2) የይሖዋ ምሥክሮች የሚለው ስም ስለ እኛ ምን ይናገራል? (3) ኢየሱስ ምን ምሳሌ ትቶልናል? እርሱን መኮረጅ የምንችለውስ እንዴት ነው? (4) በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦችን ለሰዎች ለማካፈል ውጤታማ ሆነው የተገኙት ዘዴዎች የትኞቹ ናቸው? (5) ሰዎችን ስናነጋግር አመቺ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ማንበቡ ተመራጭ የሆነው ለምንድን ነው? (6) ሽማግሌዎች በመጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ እንዲጠቀሙ ሌሎችን ማበረታታት የሚችሉት እንዴት ነው? ጥሩ ችሎታ ያለው አንድ አስፋፊ በገጽ 144 ላይ ባለው መልመጃ ተመሥርቶ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። አስፋፊው ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ቢያንስ አንድ ጥቅስ ያነብባል። ሁሉም ምሥክርነቱን በሚሰጡበት አጋጣሚ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን ለመጠቀም ግብ እንዲያደርጉ አበረታታ።

13 ደቂቃ:- ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎች። አድማጮች በአውራጃ ስብሰባ ሲገኙ ወይም በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት ወይም በሌሎች ቦታዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነቱን ሲሰጡ ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

25 ደቂቃ:- ደስተኛ ከሆነው አምላክ ጋር ደስ ይበላችሁ። በግንቦት 1, 2001 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8-13 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 80 (180) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ