የ2004 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያ
#የ2004 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ክፍሎቹ የሚቀርቡባቸው ጽሑፎች፦ መጽሐፍ ቅዱስ [1954]፣ መጠበቂያ ግንብ [w-AM]፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም [be-AM]፣ “ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [si ] እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rs-AM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ከተከፈተ በኋላ በሚከተለው መመሪያ መሠረት ይከናወናል:-
የንግግር ባሕርይ፦ 5 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች፣ ረዳት ምክር ሰጪው ወይም ጥሩ ችሎታ ያለው ሌላ ሽማግሌ ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ላይ በአንድ የንግግር ባሕርይ ላይ የተመሠረተ ክፍል ያቀርባል። (በቂ ሽማግሌዎች በሌሉባቸው ጉባኤዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያለው የጉባኤ አገልጋይ ይህን ክፍል ሊያቀርብ ይችላል።) ተጨማሪ መግለጫ ካልተሰጠ በስተቀር ለሳምንቱ በተመደቡት ገጾች ውስጥ የሚገኙት ሣጥኖች በንግግሩ ውስጥ መካተት ይኖርባቸዋል። መልመጃዎቹ ተማሪው በግሉ እንዲጠቀምባቸውና በግል ምክር ለመስጠት ታስበው የተዘጋጁ ስለሆኑ በክፍሉ ውስጥ መካተት አይኖርባቸውም።
ክፍል ቁ. 1፦ 10 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም ወይም “ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” በተባሉት መጽሐፎች ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ለአሥር ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር የሚቀርብ ሲሆን የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። ዓላማው በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር ለጉባኤው ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ እያጎሉ የተመደበውን ክፍል መሸፈን ነው። በፕሮግራሙ ላይ የተሰጠውን ጭብጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን ንግግር እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች ክፍላቸውን በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አቅርበው መጨረስ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይችላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 10 ደቂቃ። በመጀመሪያ ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ለስድስት ደቂቃ ያህል ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር እያዛመደ ያቀርበዋል። ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርበው ወንድም ለሳምንቱ ከተመደበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ በፈለገው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ሐሳብ መስጠት ይችላል። ለሳምንቱ የተመደቡትን ምዕራፎች በመከለስ ብቻ ክፍሉ መቅረብ አይኖርበትም። ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት እንደሚጠቅም እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ተናጋሪው ለመጀመሪያው ክፍል የተመደበለትን ስድስት ደቂቃ ብቻ በመጠቀም አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አራት ደቂቃ ላለመንካት መጠንቀቅ ይኖርበታል። ቀጥሎ አድማጮች ከሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ልባቸውን የነካውንና ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን ሐሳብ በአጭሩ (በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ) እንዲናገሩ ይጋብዛል። ከዚያም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በሁለተኛው አዳራሽ ውስጥ ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች መሄድ እንደሚችሉ ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ 4 ደቂቃ። ይህን ክፍል አንድ ወንድም በንባብ ያቀርበዋል። ንባቡ አብዛኛውን ጊዜ የሚቀርበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል። በወር አንድ ጊዜ ክፍሉ ከመጠበቂያ ግንብ ይቀርባል። ተማሪው መግቢያ እና መደምደሚያ ማዘጋጀት ሳያስፈልገው ክፍሉን እንዲሁ በንባብ ብቻ ያቀርበዋል። በየሳምንቱ የሚነበበው ክፍል ርዝመት የሚለያይ ቢሆንም በአራት ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሸፈን ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የተማሪውን ዕድሜና ችሎታ ግምት ውስጥ ማስገባት እንዲችል ክፍሉን ከመስጠቱ በፊት ትምህርቱን ማንበብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዎቹ ክፍሉን በሚገባ ተረድተው፣ በቅልጥፍና፣ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ በማጥበቅ፣ ድምፅን በመለዋወጥ፣ በተገቢው ቦታ ቆም በማለትና የራስን ተፈጥሯዊ አነጋገር በመጠቀም እንዲያነብቡ መርዳት ይፈልጋል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። ይህን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡ ተማሪዎች በአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ ከተዘረዘሩት መቼቶች መካከል አንዱን መምረጥ ይችላሉ፤ ወይም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ክፍላቸውን የሚያቀርቡበትን መቼት ይሰጣቸዋል። ተማሪዋ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኘውን ጭብጥ መጠቀምና ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል በሚስማማ መንገድ ማቅረብ ይኖርባታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪዋ ታማኝና ልባም ባሪያ ባዘጋጃቸው ጽሑፎች ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ማሰባሰብ ይኖርባታል። አዳዲስ ተማሪዎች ጭብጡ ብቻ የተሰጠባቸውን ክፍሎች ማቅረብ አይኖርባቸውም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ እንዴት እንደምታዳብርና የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉምና የክፍሉን ዋና ዋና ነጥቦች እንዲገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። ይህን ክፍል እንድታቀርብ የተመደበችው እህት ማንበብ የምትችል መሆን አለባት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። ተማሪው የተሰጠውን ጭብጥ ማዳበር ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪው ታማኝና ልባም ባሪያ ባዘጋጃቸው ጽሑፎች ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ያሰባስባል። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ የጉባኤውን አድማጭ ግምት ውስጥ በማስገባት በንግግር መልክ ያቀርበዋል። ሆኖም ክፍሉ ለአንዲት እህት ከተሰጠ ለክፍል ቁጥር 3 በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተገቢ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ክፍል ቁጥር 4ን ለአንድ ወንድም ሊሰጥ ይችላል። የኮከብ ምልክት ያለባቸው ክፍሎች በንግግር መልክ መቅረብ ያለባቸው ስለሆኑ ለወንድሞች ብቻ መሰጠት ይኖርባቸዋል።
ጊዜን መጠበቅ፦ ክፍል የሚያቀርቡትም ሆኑ ምክር ሰጪው የተመደበላቸውን ጊዜ ማሳለፍ አይኖርባቸውም። ከቁጥር 2 እስከ 4 ያሉትን ክፍሎች የሚያቀርቡት ወንድሞች የተመደበላቸው ጊዜ ሲሞላ በዘዴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለ ንግግር ባሕርይ የሚናገረው የመክፈቻ ንግግር፣ ክፍል ቁጥር 1 ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርቡ ወንድሞች ሰዓት ካሳለፉ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይገባል። ሁሉም ሰዓታቸውን በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ጸሎትንና መዝሙርን ሳይጨምር ጠቅላላው ፕሮግራም 45 ደቂቃ ይፈጃል።
ምክር፦ 1 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከእያንዳንዱ የተማሪ ንግግር በኋላ የንግግሩን ገንቢ ጎኖች አንስቶ አስተያየት ለመስጠት ከአንድ ደቂቃ የበለጠ ጊዜ መውሰድ አይኖርበትም። ዓላማው “ጥሩ ነው” ብሎ ለማለፍ ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ የተማሪው አቀራረብ ጥሩ የሆነበትን ምክንያት ለይቶ መጥቀስ ያስፈልገዋል። የእያንዳንዱን ተማሪ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከስብሰባው በኋላ ወይም በሌላ ጊዜ ገንቢ የሆነ ተጨማሪ ምክር በግል መስጠት ይችላል።
ረዳት ምክር ሰጪ፦ የሽማግሌዎች አካል ከትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተጨማሪ ረዳት ምክር ሰጪ ሆኖ የሚያገለግል ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ሊመርጥ ይችላል። በጉባኤው ውስጥ በርካታ ሽማግሌዎች ካሉ በየዓመቱ ብቃት ያላቸው ሽማግሌዎች እየተቀያየሩ ይህን ኃላፊነት ሊይዙ ይችላሉ። የዚህ ወንድም ኃላፊነት ንግግር ቁጥር 1ን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ለሚያቀርቡ ወንድሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግል ምክር መስጠት ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እነዚህን ክፍሎች የሚያቀርቡ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ንግግራቸውን ባቀረቡ ቁጥር ምክር ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም። ይህ ዝግጅት በ2004ም ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከዚያ በኋላ ማስተካከያ ሊደረግበት ይችላል።
ምክር መስጫ ነጥቦችን የያዘ ቅጽ፦ በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
የቃል ክለሳ፦ 30 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በየሁለት ወሩ የሚቀርበውን የቃል ክለሳ ይመራል። ክለሳው የሚደረገው የንግግር ባሕርይና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረቡ በኋላ ይሆናል። ክለሳው የሚሸፍነው፣ የክለሳውን ሳምንት ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የቀረቡትን ትምህርቶች ይሆናል።
ፕሮግራም
ጥር 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 1-5 መዝ. 35 (79)
የንግግር ባሕርይ፦ የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ (be ገጽ 157 አን. 1-ገጽ 158 አን. 1)
ቁ. 1፦ አስተዋጽኦ ማዘጋጀት (be ገጽ 39-42)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 2:7-25
ቁ. 3፦ “አዲስ ኪዳን” ወደፊት ምድራዊት ገነት እንደምትቋቋም ይናገራል ወይስ ስለ ገነት የሚናገረው “ብሉይ ኪዳን” ብቻ ነው? (rs ገጽ 284 አን. 6–ገጽ 285 አን. 2)
ቁ. 4፦ a በጎ የሆነውን አለማድረግ ኃጢአት እንደሆነ ከሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ምን ትምህርት እናገኛለን?
ጥር 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 6-10 መዝ. 96 (215)
የንግግር ባሕርይ፦ ትምህርቱን ለአድማጮች በሚጠቅም መንገድ ማቅረብ (be ገጽ 158 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ ንጽሕና—ትክክለኛ ትርጉሙ ምንድን ነው? (w02 2/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 8:1-17
ቁ. 3፦ መዋሸት ስህተት የሆነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ በሉቃስ 23:43 ላይ የተጠቀሰው ‘ገነት’ የሚለው ቃል በሔድስ ወይም በሰማይ የሚገኝን ቦታ አያመለክትም የምንለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 286 አን. 1–ገጽ 287 አን. 1)
ጥር 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 11-16 መዝ. 98 (220)
የንግግር ባሕርይ፦ የትምህርቱን ጠቀሜታ እንዲያስተውሉ መርዳት (be ገጽ 158 አን. 5–ገጽ 159 አን. 3)
ቁ. 1፦ ከአምላካዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጥቅም ማግኘት ትችላለህ (w02 2/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 13:1-18
ቁ. 3፦ በሉቃስ 23:43 ላይ የተጠቀሰው ገነት ምድራዊ መሆኑን የሚያመለክተው ምንድን ነው? (rs ገጽ 287 አን. 2–ገጽ 288 አን. 2)
ቁ. 4፦ የይሖዋ ምሥክሮች ስለ እምነታቸው ለሌሎች የሚናገሩት ለምንድን ነው?
ጥር 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 17-20 መዝ. 45 (106)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ ቃላትን መምረጥ (be ገጽ 160 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የሌላውን ችግር እንደራስ መመልከት—ደግና ሩኅሩኅ ለመሆን የሚረዳ ባሕርይ (w02 4/15 ገጽ 24-7)
ቁ. 2፦ w02 1/1 ገጽ 10, 11 አን. 9-11
ቁ. 3፦ በሉቃስ 13:24 ላይ የሚገኙት የኢየሱስ ቃላት ምን ትርጉም አላቸው?
ቁ. 4፦ ማናችንም ብንሆን እውነተኛ እውቀትና ጥበብ ልናገኝ የምንችለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 288 አን. 3–ገጽ 289 አን. 2)
የካ. 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 21-24 መዝ. 61 (144)
የንግግር ባሕርይ፦ ለመረዳት የማያስቸግር አገላለጽ (be ገጽ 161 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡህን የተማሪ ክፍሎች መዘጋጀት (be ገጽ 43 አን. 1–ገጽ 44 አን. 3)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 21:1-21
ቁ. 3፦ የሰብዓዊ ፍልስፍናዎች ምንጭ ምንድን ነው? (rs ገጽ 289 አን. 3–ገጽ 290 አን. 2)
ቁ. 4፦ b ክርስቲያኖች ለጋብቻ መተጫጨትን አክብደው ሊመለከቱት የሚገባው ለምንድን ነው?
የካ. 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 25-28 መዝ. 33 (72)
የንግግር ባሕርይ፦ የተለያዩና ትክክለኛ ቃላት መጠቀም (be ገጽ 161 አን. 5–ገጽ 162 አን.4)
ቁ. 1፦ ከጭብጡና ከመቼቱ ጋር የሚስማማ ዝግጅት (be ገጽ 44 አን. 4–ገጽ 46 አን. 1)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 28:1-15
ቁ. 3፦ መከራ በሞላበት በዚህ ዓለም ውስጥ ውስጣዊ ሰላም ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ ከሰብዓዊ ፍልስፍና ይልቅ የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ማጥናት ትክክለኛ አስተሳሰብ እንዳለን የሚያሳየው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 290 አን. 3–ገጽ 291 አን. 3)
የካ. 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 29-31 መዝ. 69 (160)
የንግግር ባሕርይ፦ ኃይል ያላቸው፣ ስሜቱን የሚያስተላልፉና ገላጭ የሆኑ ቃላት (be ገጽ 163 አን. 1–ገጽ 164 አን. 1)
ቁ. 1፦ ጽኑ አቋም ቅኖችን ይመራቸዋል (w02 5/15 ገጽ 24-7)
ቁ. 2፦ w02 2/1 ገጽ 15-16 አን. 6-10
ቁ. 3፦ አምላክ የሚሰማው የእነማንን ጸሎት ነው? (rs ገጽ 292 አን. 1–ገጽ 293 አን. 1)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች በጎነትን ማዳበር የሚገባቸው ለምንድን ነው?
የካ. 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 32-35 መዝ. 23 (48)
የንግግር ባሕርይ፦ የሰዋስውን ሕግ የጠበቀ አነጋገር (be ገጽ 164 አን. 2–6)
የቃል ክለሳ
መጋ. 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 36-39 መዝ. 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ በአስተዋጽኦ መጠቀም (be ገጽ 166 አን. 1–ገጽ 167 አን. 1)
ቁ. 1፦ ለጉባኤ የሚቀርቡ ንግግሮችን መዘጋጀት (be ገጽ 47 አን. 1–ገጽ 49 አን. 1)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 37:12-28
ቁ. 3፦ እምነታችን ከጽናት ጋር የሚያያዘው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ c የአንድን ሰው ጸሎት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ሊያሳጡት የሚችሉ ነገሮች ምንድን ናቸው? (rs ገጽ 293 አን. 2-9)
መጋ. 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 40-42 መዝ. 67 (156)
የንግግር ባሕርይ፦ መናገር የምትፈልገውን ሐሳብ አቀናብር (be ገጽ 167 አን. 2–ገጽ 168 አን. 1)
ቁ. 1፦ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡ ክፍሎችንና ሌሎች ንግግሮችን መዘጋጀት (be ገጽ 49 አን. 2–ገጽ 51 አን. 1)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 42:1-20
ቁ. 3፦ ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ዝምድና መመሥረት የሚቻለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ d ልንጸልይባቸው የሚገቡ ትክክለኛ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? (rs ገጽ 294 አን. 1-8)
መጋ. 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 43-46 መዝ. 31 (67)
የንግግር ባሕርይ፦ አስተዋጽኦህ ቅልብጭ ያለ ይሁን (be ገጽ 168 አን. 2–ገጽ 169 አን. 6)
ቁ. 1፦ ይሖዋ ከልብ የምናደርገውን ጥረት ይባርካል (w02 8/1 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 43:1-18
ቁ. 3፦ #አንድ ሰው ‘መጀመሪያ አብረን እንጸልይና ከዚያ በኋላ መልእክትህን ታሰማኛለህ’ ቢልስ? (rs ገጽ 294 አን. 9-ገጽ 295 አን. 1)
ቁ. 4፦ በዓመፃ ገንዘብ ወዳጆችን ማፍራት የምንችለው እንዴት ነው?
መጋ. 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 47-50 መዝ. 83 (187)
የንግግር ባሕርይ፦ ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር (be ገጽ 170 አን. 1–ገጽ 171 አን. 2)
ቁ. 1፦ ይሖዋ የአቤልን መሥዋዕት ሲቀበል የቃየንን ያልተቀበለው ለምን ነበር? (w02 8/1 ገጽ 28)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 47:1-17
ቁ. 3፦ ገና ወደ ፊት የሚፈጸሙ ጎላ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ምንድን ናቸው? (rs ገጽ 295 አን. 3–ገጽ 296 አን. 6)
ቁ. 4፦ የጥበብ መጀመሪያ ይሖዋን መፍራት ነው የሚባለው ለምንድን ነው?
መጋ. 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 1-6 መዝ. 90 (204)
የንግግር ባሕርይ፦ ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ማቅረብ (be ገጽ 171 አን. 3–ገጽ 172 አን. 5)
ቁ. 1፦ የማመዛዘን ችሎታ ሊጠብቅህ የሚችለው እንዴት ነው? (w02 8/15 ገጽ 21-4)
ቁ. 2፦ w02 2/15 ገጽ 19-20 አን. 7-11
ቁ. 3፦ ይሖዋ ኩራትን የሚመለከተው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች በጉጉት መከታተል የሚገባቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 296 አን. 7-ገጽ 297 አን. 4)
ሚያ. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 7-10 መዝ. 63 (148)
የንግግር ባሕርይ፦ አግባብ ያላቸውን ነጥቦች ብቻ ምረጥ (be ገጽ 173 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ለሕዝብ የሚቀርብ ንግግር መዘጋጀት (be ገጽ 52 አን. 1–ገጽ 54 አን. 1)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 8:1-19
ቁ. 3፦ #አንድ ሰው ‘ለትንቢት ከሚገባ በላይ ብዙ ትኩረት ትሰጣላችሁ’ ቢልስ? (rs ገጽ 297 አን. 5-ገጽ 298 አን. 1)
ቁ. 4፦ ተስፋ ‘ለነፍስ መልሕቅ’ ነው የሚባለው ለምንድን ነው?
ሚያ. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 11-14 መዝ. 40 (87)
የንግግር ባሕርይ፦ በራስ አባባል መናገር (be ገጽ 174 አን. 1–ገጽ 175 አን. 5)
ቁ. 1፦ ለተናጋሪው የተተዉ ውሳኔዎች (be ገጽ 54 አን. 2-4፤ ገጽ 55 ላይ የሚገኘውን ሣጥን)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 12:1-16
ቁ. 3፦ የይሖዋን ተግሣጽ በደስታ መቀበል የሚኖርብን ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የመንጽሔ ትምህርት የተመሠረተው በምን ላይ ነው? (rs ገጽ 298 አን. 2-ገጽ 299 አን. 3)
ሚያ. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 15-18 መዝ. 75 (169)
የንግግር ባሕርይ፦ በራሳችን አባባል ስንናገር ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ ጉዳዮች (be ገጽ 175 አን. 6–ገጽ 177 አን. 1)
ቁ. 1፦ ለፈተናዎች ሊኖረን የሚገባው አመለካከት ምንድን ነው? (w02 9/1 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ w02 3/1 ገጽ 15-16 አን. 8-11
ቁ. 3፦ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ድሮ ለሠራቸው ኃጢአቶች ተጨማሪ ቅጣት ይቀበላልን? (rs ገጽ 299 አን. 5-ገጽ 300 አን. 3)
ቁ. 4፦ e ጋብቻ የዕድሜ ልክ ጥምረት መሆን የሚኖርበት ለምንድን ነው?
ሚያ. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 19-22 መዝ. 78 (175)
የንግግር ባሕርይ፦ ለሌሎች ማብራሪያ መስጠት ሲያስፈልግ (be ገጽ 177 አን. 2–ገጽ 178 አን. 2)
የቃል ክለሳ
ግን. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 23-26 መዝ. 6 (13)
የንግግር ባሕርይ፦ በጭውውት መልክ መናገር (be ገጽ 179-180)
ቁ. 1፦ የማስተማር ችሎታህን አዳብር (be ገጽ 56 አን. 1–ገጽ 57 አን. 2)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 23:1-17
ቁ. 3፦ ይሖዋ አንድን ሰው ከጎጂ ልማዶች እንዲላቀቅ ሊረዳው የሚችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ የተለያዩ ዘሮች ከየት መጡ? (rs ገጽ 300 አን.4-ገጽ 301 አን. 2)
ግን. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 27-29 መዝ. 51 (127)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅ ጥራት (be ገጽ 181 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ “ለዩ” (be ገጽ 57 አን. 3–ገጽ 58 አን. 2)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 28:29-43
ቁ. 3፦ በምድር ላይ የነበረው አንድ ቤተሰብ ብቻ ከሆነ ቃየን ሚስቱን ከየት አገኘ? (rs ገጽ 301 አን. 3-5)
ቁ. 4፦ የዘር መድሎ ተገቢ ያልሆነው ለምንድን ነው?
ግን. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 30-33 መዝ. 66 (155)
የንግግር ባሕርይ፦ አተነፋፈስህን መቆጣጠር (be ገጽ 181 አን. 5–ገጽ 184 አን. 1፤ ገጽ 182 ላይ የሚገኘው ሳጥን)
ቁ. 1፦ አድማጮች በጉዳዩ ላይ እንዲያስቡ ማድረግ (be ገጽ 58 አን. 3–ገጽ 59 አን. 3)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 30:1-21
ቁ. 3፦ የዋህ መሆን የሚኖርብን ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የተለያዩ ዘሮች የተለያየ መልክ የኖራቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 302 አን. 1–ገጽ 303 አን. 1)
ግን. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 34-37 መዝ. 39 (86)
የንግግር ባሕርይ፦ የተወጠሩ ጡንቻዎችን ማዝናናት (be ገጽ 184 አን. 2–ገጽ 185 አን. 2፤ ገጽ 184 ላይ የሚገኘው ሳጥን)
ቁ. 1፦ ተግባራዊ የሚሆንበትን መንገድ ማስረዳት እንዲሁም ጥሩ ምሳሌ መሆን (be ገጽ 60 አን. 1–ገጽ 61 አን. 3)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 36:1-18
ቁ. 3፦ የሰው ልጆች በሙሉ የአምላክ ልጆች ናቸውን? (rs ገጽ 303 አን. 2–ገጽ 304 አን. 1)
ቁ. 4፦ በትንንሽ ጉዳዮችም ታማኝ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?
ግን. 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 38-40 መዝ. 91 (207)
የንግግር ባሕርይ፦ ለሰዎች አሳቢነት ማሳየት (be ገጽ 186 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ከሰዎች ጋር የመወያየት ችሎታህን ማሻሻል (be ገጽ 62 አን. 1–ገጽ 64 አን. 1)
ቁ. 2፦ w02 5/1 ገጽ 19-20 አን. 3-6
ቁ. 3፦ 1 ዮሐንስ 3:19, 20ን መረዳታችን የሚያጽናናን እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ ወደፊት ሁሉም ዘሮች አንድ የወንድማማቾችና የእህትማማቾች ቤተሰብ ይሆናሉን? (rs ገጽ 304 አን. 2–ገጽ 305 አን. 1)
ሰኔ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 1-5 መዝ. 50 (123)
የንግግር ባሕርይ፦ በጥሞና ማዳመጥ (be ገጽ 187 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ውይይቱ እንዲቀጥል ማድረግ (be ገጽ 64 አን. 2–ገጽ 65 አን. 4)
ቁ. 2፦ ዘሌዋውያን 3:1-17
ቁ. 3፦ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በሰማዕትነት ከሞቱት ሌሎች ሰዎች ሞት የሚለየው በምንድን ነው? (rs ገጽ 305 አን.2-ገጽ 306 አን. 2)
ቁ. 4፦ ከአስማት ጋር ንክኪ ካላቸው ነገሮች መራቅ ያለብን ለምንድን ነው?
ሰኔ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 6-9 መዝ. 7 (19)
የንግግር ባሕርይ፦ ሌሎች እድገት እንዲያደርጉ መርዳት (be ገጽ 187 አን. 6–ገጽ 188 አን. 3)
ቁ. 1፦ የጠያቂውን አመለካከት መረዳት (be ገጽ 66 አን. 1–ገጽ 68 አን. 1)
ቁ. 2፦ ዘሌዋውያን 7:1-19
ቁ. 3፦ ክፋትን መጥላት መማር የምንችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ ቤዛው በዚህ መንገድ መቅረቡ አስፈላጊ የሆነው ለምን ነበር? (rs ገጽ 306 አን. 4-6)
ሰኔ 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 10-13 መዝ. 82 (183)
የንግግር ባሕርይ፦ እርዳታ መስጠት (be ገጽ 188 አን. 4–ገጽ 189 አን. 4)
ቁ. 1፦ እንዴት መልስ መስጠት እንዳለብህ ተማር (be ገጽ 68 አን. 2–ገጽ 70 አን. 3)
ቁ. 2፦ ዘሌዋውያን 11:1-25
ቁ. 3፦ አምላክ እርሱን ለመታዘዝ የሚመርጡ ሁሉ ለዘላለም እንዲኖሩ ፈቅጃለሁ ብሎ በቀላሉ ለምን አይናገርም ነበር? (rs ገጽ 307 አን. 1–4)
ቁ. 4፦ ይሖዋ መኮረጅን እንዴት ይመለከተዋል?
ሰኔ 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 14-16 መዝ. 39 (86)
የንግግር ባሕርይ፦ ሰዎችን ማክበር (be ገጽ 190 አን. 1-4)
የቃል ክለሳ
ሐምሌ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 17-20 መዝ. 4 (8)
የንግግር ባሕርይ፦ አክብሮት የሚገለጽባቸው የተለያዩ መንገዶች (be ገጽ 191 አን. 1–ገጽ 192 አን. 1)
ቁ. 1፦ ደብዳቤ መጻፍ (be ገጽ 71-73)
ቁ. 2፦ ዘሌዋውያን 17:1-16
ቁ. 3፦ በይሖዋ ድርጅት ተማመኑ
ቁ. 4፦ የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ መሥዋዕት ዋጋ ተጠቃሚዎች እነማን ነበሩ? ዓላማውስ ምን ነበር? (rs ገጽ 308 አን. 1, 2)
ሐምሌ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 21-24 መዝ. 58 (138)
የንግግር ባሕርይ፦ ለአድማጮች አክብሮት እንዳለን የሚያሳይ አነጋገር (be ገጽ 192 አን. 2–ገጽ 193 አን. 2)
ቁ. 1፦ እድገት አድርግ (be ገጽ 74 አን. 1–ገጽ 75 አን. 3)
ቁ. 2፦ ዘሌዋውያን 22:1-16
ቁ. 3፦ በዘመናችን ከኢየሱስ መሥዋዕት ተጠቃሚ የሆኑት ሌሎች ሰዎች እነማን ናቸው? (rs ገጽ 308 አን. 3-ገጽ 309 አን. 1)
ቁ. 4፦ ይሖዋ የአይሁዳውያን አምላክ ብቻ ነውን?
ሐምሌ 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 25-27 መዝ. 62 (146)
የንግግር ባሕርይ፦ በእርግጠኝነት መናገር (be ገጽ 194 አን. 1–ገጽ 195 አን. 2)
ቁ. 1፦ ተሰጥዎህን ተጠቀምበት (be ገጽ 75 አን. 4–ገጽ 77 አን. 2)
ቁ. 2፦ ዘሌዋውያን 25:1-19
ቁ. 3፦ ሽብርተኝነት መቋጫው ምንድን ነው?
ቁ. 4፦ በቤዛው ምክንያት ወደፊት ምን ዓይነት በረከቶች ይመጣሉ? (rs ገጽ 309 አን. 2-ገጽ 310 አን. 1)
ሐምሌ 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 1-3 መዝ. 29 (62)
የንግግር ባሕርይ፦ እርግጠኛ መሆናችን የሚንጸባረቅባቸው መንገዶች (be ገጽ 195 አን. 3–ገጽ 196 አን. 4)
ቁ. 1፦ ክርስቲያኖች መቅናት ይኖርባቸዋልን? (w02 10/15 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ w02 6/15 ገጽ 18-19 አን. 6-9
ቁ. 3፦ ፍጹም ከሆነው የኢየሱስ መሥዋዕት ዘላቂ ጥቅም እንድናገኝ ምን ይፈለግብናል? (rs ገጽ 310 አን. 2–5)
ቁ. 4፦ የምንወደው ሰው ሲሞት ማዘን ስህተት ነውን?
ነሐሴ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 4-6 መዝ. 88 (200)
የንግግር ባሕርይ፦ በአነጋገር ዘዴኛ መሆን (be ገጽ 197 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ ሕይወታችንን በይሖዋ ፊት ትርጉም ባለው መንገድ ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው? (w02 11/15 ገጽ 20-3)
ቁ. 2፦ ዘኍልቍ 6:1-17
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዳይጠላሉ ሊረዳቸው የሚችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ የቤዛው ዝግጅት በአኗኗራችን ላይ ምን ዓይነት ለውጥ ሊያስከትል ይገባል? (rs ገጽ 310 አን. 6-ገጽ 311 አን. 2)
ነሐሴ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 7-9 መዝ. 15 (35)
የንግግር ባሕርይ፦ ስንመሰክር በአነጋገራችን ዘዴኛ መሆን (be ገጽ 197 አን. 4–ገጽ 198 አን. 4)
ቁ. 1፦ የመደብ ልዩነት የሌለበት ኅብረተሰብ መፍጠር ይቻል ይሆን? (w02 1/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘኍልቍ 8:1-19
ቁ. 3፦ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች “ከክርስቶስ ጋር ለመሆን” ይነጠቃሉ ባለ ጊዜ እያብራራ የነበረው ርዕሰ ጉዳይ ምን ነበር? (rs ገጽ 311 አን. 3-ገጽ 312 አን. 1)
ቁ. 4፦ የክርስቶስ ተቃዋሚ ማን ነው?
ነሐሴ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 10-13 መዝ. 21 (46)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ ቃላትን በትክክለኛ ጊዜ ላይ መጠቀም (be ገጽ 199 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ እውን በሆነው አምላክ በይሖዋ ታመን (w02 1/15 ገጽ 5-7)
ቁ. 2፦ ዘኍልቍ 12:1-16
ቁ. 3፦ አምላክ የሚበቀል መሆኑ ከአፍቃሪነቱ ጋር አይጋጭም?
ቁ. 4፦ ክርስቶስ በደመና እየታየና ዓለም እየተመለከተው ታማኝ ክርስቲያኖችን ወደ ሰማይ ይወስዳቸዋልን? (rs ገጽ 312 አን. 2-ገጽ 313 አን. 1)
ነሐሴ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 14-16 መዝ. 91 (207)
የንግግር ባሕርይ፦ ከቤተሰባችንና ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ዘዴኛ መሆን (be ገጽ 200 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ የተለያየ አመለካከት ያዳበሩ ወንድማማቾች (w02 1/15 ገጽ 21-3)
ቁ. 2፦ w02 7/15 ገጽ 23-24 አን. 15-19
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ከነሥጋዊ አካላቸው ወደ ሰማይ ሊወሰዱ ይችላሉን? (rs ገጽ 313 አን. 2, 3)
ቁ. 4፦ f ክርስቲያኖች በዓመፅ ድርጊት የተሞሉ የቪዲዮ ጨዋታዎችን መጫወት የማይኖርባቸው ለምንድን ነው?
ነሐሴ 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 17-21 መዝ. 49 (114)
የንግግር ባሕርይ፦ አዎንታዊና የምታበረታታ ሁን (be ገጽ 202 አን. 1–ገጽ 203 አን. 1)
የቃል ክለሳ
መስ. 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 22-25 መዝ. 54 (132)
የንግግር ባሕርይ፦ አዎንታዊ አቀራረብ ይኑርህ (be ገጽ 203 አን. 2–ገጽ 204 አን. 1)
ቁ. 1፦ የጥንቱ ዓለም የጠፋው ለምንድን ነው? (w02 3/1 ገጽ 5-7)
ቁ. 2፦ ዘኍልቍ 22:1-19
ቁ. 3፦ ታማኝ ክርስቲያኖች ሳይሞቱ በምሥጢር ወደ ሰማይ ይወሰዳሉን? (rs ገጽ 313 አን. 4–ገጽ 314 አን. 3)
ቁ. 4፦ g ክርስቲያን ወላጆች ለልጆቻቸው ማንበብ የሚኖርባቸው ለምንድን ነው?
መስ. 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 26-29 መዝ. 32 (70)
የንግግር ባሕርይ፦ ከክርስቲያን ወንድሞችህ ጋር ስትጨዋወት (be ገጽ 204 አን. 2–ገጽ 205 አን. 4)
ቁ. 1፦ የአካል ጉዳተኝነት የሚወገደው እንዴት ነው? (w02 5/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘኍልቍ 29:1-19
ቁ. 3፦ በታላቁ መከራ ጊዜ ለእውነተኛ ክርስቲያኖች ምን ጥበቃ ይደረግላቸዋል? (rs ገጽ 314 አን. 4–ገጽ 315 አን. 3)
ቁ. 4፦ አምላክ የሰጣቸው ተስፋዎች በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት አዎን የሆኑት እንዴት ነው?
መስ. 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 30-32 መዝ. 14 (34)
የንግግር ባሕርይ፦ ነጥቡን ለማጉላት መደጋገም (be ገጽ 206 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ጽድቅን በመዝራት የአምላክን ፍቅራዊ ደግነት እጨዱ (w02 7/15 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ ዘኍልቍ 30:1-16
ቁ. 3፦ አንዳንድ ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር እንዲሆኑ ወደ ሰማይ የሚወሰዱት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 315 አን. 5-8)
ቁ. 4፦ h ወሲባዊ ሥዕሎችንና ጽሑፎችን መጥላት የሚኖርብን ለምንድን ነው?
መስ. 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 33-36 መዝ. 57 (136)
የንግግር ባሕርይ፦ በአገልግሎት ላይና ንግግር ስትሰጥ መደጋገም (be ገጽ 207 አን. 1–ገጽ 208 አን. 3)
ቁ. 1፦ እውነተኞቹ ቅዱሳን ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው? (w02 9/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ w02 8/1 ገጽ 18-19 አን. 15-19
ቁ. 3፦ #‘በአካል መነጠቅ እንዳለ ታምናለህ?’ (rs ገጽ 315 አን. 9–ገጽ 316 አን. 1)
ቁ. 4፦ አደገኛ በሆኑ ስፖርቶች መካፈል የሌለብን ለምንድን ነው?
ጥቅ. 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 1-3 መዝ. 85 (191)
የንግግር ባሕርይ፦ ጭብጡን ማዳበር (be ገጽ 209 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ አምላክን በትክክል በማወቅ የሚገኝ መጽናኛ (w02 10/1 ገጽ 5-7)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 1:1-18
ቁ. 3፦ እውነትን የራስህ አድርግ ሲባል ምን ማለት ነው?
ቁ. 4፦ ከዚህ በፊት የማናውቃቸውን ሰዎችና ቦታዎች እንደምናውቅ ሆኖ የሚሰማን መሆኑ ሪኢንካርኔሽን እውነት መሆኑን ያረጋግጣልን? (rs ገጽ 316 አን. 2–ገጽ 318 አን. 1)
ጥቅ. 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 4-6 መዝ. 81 (181)
የንግግር ባሕርይ፦ ተስማሚ ጭብጥ (be ገጽ 210 አን. 1–ገጽ 211 አን. 1 እና ሳጥኑን)
ቁ. 1፦ ከ537 ከዘአበ አንስቶ እስከ 997 ከዘአበ ወደኋላ መቁጠር (si ገጽ 285 አን. 5-7)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 4:1-14
ቁ. 3፦ በዮሐንስ 9:1, 2 ላይ የሚገኘው ዘገባ ሪኢንካርኔሽንን የማያመለክተው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 318 አን. 2-ገጽ 319 አን. 2)
ቁ. 4፦ ስለ ሥጋ ማሰብ ምን ነገሮችን ይጨምራል?
ጥቅ. 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 7-10 መዝ. 45 (106)
የንግግር ባሕርይ፦ ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ (be ገጽ 212 አን. 1–ገጽ 213 አን. 1)
ቁ. 1፦ ከ997 ከዘአበ አንስቶ እስከ 2370 ከዘአበ ወደኋላ መቁጠር (si ገጽ 285-6 አን. 8-11)
ቁ. 2፦ w02 8/15 ገጽ 15-16 አን. 3-6
ቁ. 3፦ በሪኢንካርኔሽንና መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው ተስፋ መካከል ምን ያህል ልዩነት አለ? (rs ገጽ 319 አን. 3, 4)
ቁ. 4፦ i ይሖዋ ከሃዲዎችን የሚመለከታቸው እንዴት ነው?
ጥቅ. 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 11-13 መዝ. 27 (57)
የንግግር ባሕርይ፦ ዋና ዋና ነጥቦች አይብዙ (be ገጽ 213 አን. 2–ገጽ 214 አን. 5)
የቃል ክለሳ
ኅዳር 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 14-18 መዝ. 9 (26)
የንግግር ባሕርይ፦ በጉጉት ለማዳመጥ የሚጋብዝ መግቢያ (be ገጽ 215 አን. 1–ገጽ 216 አን. 4)
ቁ. 1፦ ከ2370 ከዘአበ አንስቶ እስከ 4026 ከዘአበ ወደኋላ መቁጠር (si ገጽ 286-7 አን. 12-15)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 14:1-23
ቁ. 3፦ #አንድ ሰው ‘እኔ በሪኢንካርኔሽን አምናለሁ’ ቢልስ? (rs ገጽ 320 አን. 1-3)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች አኗኗራቸውን ቀላል ማድረግ የሚኖርባቸው ለምንድን ነው?
ኅዳር 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 19-22 መዝ. 28 (58)
የንግግር ባሕርይ፦ በመስክ አገልግሎት ላይ የምታገኛቸው ሰዎች በትኩረት እንዲከታተሉህ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? (be ገጽ 217 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት (si ገጽ 291 አን. 16-17)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 21:1-17
ቁ. 3፦ ይህን ያህል ብዙ ሃይማኖቶች የኖሩት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 321 አን. 1–ገጽ 322 አን. 2)
ቁ. 4፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ምሳሌዎች የተስፋ መቁረጥ ስሜትን እንድንቋቋም ሊረዱን የሚችሉት እንዴት ነው?
ኅዳር 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 23-27 መዝ. 70 (162)
የንግግር ባሕርይ፦ በመግቢያ ላይ ርዕሰ ጉዳዩን ግልጽ ማድረግ (be ገጽ 217 አን. 5–ገጽ 219 አን. 1)
ቁ. 1፦ ኢየሱስ በአገልግሎት ያሳለፋቸው ዓመታት (si ገጽ 291 አን. 18-19)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 24:1-16
ቁ. 3፦ የአምላክ ድጋፍ ያላቸውን ሰዎች ለይተን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ ሁሉም ሃይማኖት የራሱ ጥሩ ጎን አለው የሚባለው እውነት ነውን? (rs ገጽ 322 አን.3-ገጽ 323 አን. 1)
ኅዳር 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 28-31 መዝ. 12 (32)
የንግግር ባሕርይ፦ ግቡን የሚመታ መደምደሚያ (be ገጽ 220 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ዘመን (si ገጽ 291-2 አን. 20-3)
ቁ. 2፦ ዘዳግም 29:1-18
ቁ. 3፦ የወላጆችን ሃይማኖት መተው ትክክል ነውን? (rs ገጽ 323 አን. 2-4)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ልከኞች መሆን ያለባቸው ለምንድን ነው?
ኅዳር 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 32-34 መዝ. 34 (77)
የንግግር ባሕርይ፦ መደምደሚያን በተመለከተ ሊታስብባቸው የሚገቡ ነጥቦች (be ገጽ 220 አን. 4–ገጽ 221 አን. 4)
ቁ. 1፦ የጳውሎስ ሁለተኛው ሚስዮናዊ ጉዞ (si ገጽ 292-3 አን. 24-5)
ቁ. 2፦ w02 10/15 ገጽ 11 አን. 10-13
ቁ. 3፦ የአምላክን ስም መቀደስ የምንችልባቸው መንገዶች
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖቶችን ስለ መቀላቀል ምን አመለካከት አለው? (rs ገጽ 324 አን. 1–ገጽ 325 አን. 1)
ታኅ. 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 1-5 መዝ. 18 (42)
የንግግር ባሕርይ፦ በአገልግሎት (be ገጽ 221 አን. 5–ገጽ 222 አን. 6)
ቁ. 1፦ የጳውሎስ ሦስተኛው ሚስዮናዊ ጉዞ እንዲሁም የአገልግሎቱ የመጨረሻ ዓመታት፣ ከ56-100 እዘአ (si ገጽ 293 አን. 26-30)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 4:1-14
ቁ. 3፦ የአንድ የተደራጀ ሃይማኖት አባል መሆን አስፈላጊ ነውን? (rs ገጽ 325 አን. 2–ገጽ 326 አን. 1)
ቁ. 4፦ ገና የክርስቲያኖች ክብረ በዓል ነው?
ታኅ. 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 6-8 መዝ. 95 (213)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ መረጃ ማስተላለፍ (be ገጽ 223 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ይቅርታ መጠየቅ—እርቅ ለመፍጠር የሚያስችል ቁልፍ (w02 11/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 6:10-23
ቁ. 3፦ ከቤት ወደ ቤት እየሄድን መስበካችንን ማቋረጥ የሌለብን ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የሚያስፈልገው ሌላውን ሰው መውደድ ብቻ ነውን? (rs ገጽ 326 አን. 3)
ታኅ. 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 9-11 መዝ. 56 (135)
የንግግር ባሕርይ፦ ‘በታመነው ቃል መጽናት’ (be ገጽ 224 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ እጃችሁን አጽኑ (w02 12/1 ገጽ 30, 31)
ቁ. 2፦ w02 11/15 ገጽ 18-19 አን. 19-23
ቁ. 3፦ ከአምላክ ጋር የግል ዝምድና መመሥረት የግድ አስፈላጊ ነውን? (rs ገጽ 326 አን. 4–ገጽ 327 አን. 1)
ቁ. 4፦ j ሰላማዊ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?
ታኅ. 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 12-15 መዝ. 76 (172)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ መረጃ መሆኑን ማረጋገጥ (be ገጽ 225 አን. 1-3)
የቃል ክለሳ
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
a ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
b ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
c ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
d ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
e የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የተሰጡ መልሶችን ስታቀርብ ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።
f የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የተሰጡ መልሶችን ስታቀርብ ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።
g ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
h ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
i ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
j ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የተሰጡ መልሶችን ስታቀርብ ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።
ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የተሰጡ መልሶችን ስታቀርብ ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።
ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።