የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/04 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 2 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 1/04 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥር 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 74 (168)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 2003 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የአቀራረቡን ጠቃሚ ጎኖች ተናገር።

15 ደቂቃ:- “መለኮታዊ ጥበብ በዋጋ ሊተመን የማይችል ጥቅም አለው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሰው ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- ያገኘናቸው አዳዲስ ጽሑፎች! ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። “ለአምላክ ክብር ስጡት” በተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ሁለት አዳዲስ ጽሑፎች በማግኘታችን ተደስተን ነበር። “መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” የተባለው ጽሑፍ እስከዛሬ ካገኘናቸው ጽሑፎች ሁሉ በዓይነቱ ለየት ያለ ነው። በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የተስፋይቱን ምድር ልዩ ገጽታዎች በጥልቀት የሚዳስስ ክፍል እናገኛለን። በተለያዩ ካርታዎች ላይ ከቀረቡት ዝርዝር ሐሳቦች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስ። ይህን ጽሑፍ መጠቀም የምንችልባቸውን ተግባራዊ መንገዶች ተናገር። ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተሰኘው መጽሐፍ ደግሞ የልጆቻችንን መንፈሳዊ ጤንነት ለማጎልበት ይረዳል። በመጽሐፉ ውስጥ ከቀረቡት ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስና ወላጆችም ሆኑ ልጆች እንዴት ጥቅም ማግኘት እንደሚችሉ ግለጽ። አድማጮች እነዚህን አዳዲስ ጽሑፎች እንዴት እየተጠቀሙባቸው እንዳሉ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 71 (163)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

10 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። አንድ ሽማግሌ በንግግር ያቀርበዋል።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

15 ደቂቃ:- “የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ የትዳር ጓደኞችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። እውነትን የተቀበለውን የትዳር ጓደኛቸውን መልካም ምሳሌ ተመልክተው የይሖዋ አገልጋዮች ለሆኑ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግላቸው።

መዝሙር 14 (34) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 95 (213)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የጥር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የኅዳር 15 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ለጎረቤት መጽሔት ሲበረከት የሚያሳይ ይሁን።

15 ደቂቃ:- በሕይወታችሁ ውስጥ የአምላክን ቃል በየዕለቱ በሥራ ላይ አውሉ። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሁሉም ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2004 የተባለውን ቡክሌት በሚገባ እንዲጠቀሙበት አበረታታ። በቡክሌቱ ገጽ 3-4 ላይ ከሚገኘው መቅድም አንዳንድ ሐሳቦችን ተናገር። አድማጮች የዕለት ጥቅሱን ለማንበብ በግላቸው አመቺ ሆኖ ያገኙት ሰዓት የትኛው እንደሆነ ጠይቅ። ለዚያ ዕለት የቀረበውን ጥቅስና ሐሳብ ከጉባኤው ጋር ተወያዩበት። አድማጮች ትምህርቱን ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁሉም የዕለት ጥቅሱን ካነበቡ በኋላ ትምህርቱን እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደሚችሉ ቆም ብለው እንዲያስቡበት አበረታታ።

18 ደቂቃ:- ከእምነት አጋሮቻችን ጋር ያለንን ወዳጅነት ማጠናከር። (ምሳሌ 18:24፤ 27:9) በታኅሣሥ 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-3 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። እውነተኛው አምልኮ ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል አንዱ እውነተኛ ወዳጆች ለማፍራት የሚያስችል አጋጣሚ ማግኘታችን ነው። በስብሰባዎች፣ በመስክ አገልግሎትና በሌሎች አጋጣሚዎች አብረን ጊዜ ስናሳልፍ እርስ በርስ እንበረታታለን። በጉባኤ ውስጥ ከሌሎች ጋር ያለንን ወዳጅነት ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው? “ዘላቂ ወዳጅነት ለመመሥረት የሚረዱ ስድስት ነጥቦች” የሚለውን ሣጥን ከልስና ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ረገድ እያንዳንዱን ነጥብ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል አድማጮች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 79 (177) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 90 (204)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በየካቲት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። ራዕይ​—⁠ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! የተ​ባለውን መጽሐፍ ለማበርከት የሚረዱ አቀራረቦችን ከየካቲት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 12 ላይ ተናገር።

20 ደቂቃ:- “በጊዜ አጠቃቀማችሁ ረገድ ጠንቃቆች ሁኑ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎች ለመንፈሳዊ ነገሮች የሚያውሉትን ጊዜ እንዳይሻሙባቸው የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።

15 ደቂቃ:- የክርስቶስን ፈለግ የተከተለውን የጳውሎስን ምሳሌ ኮርጁ። (1 ቆ⁠ሮ. 11:1) ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ጳውሎስ እንደ ኢየሱስ አጋጣሚዎችን በሚገባ በመጠቀም ‘ለሚያገኛቸው ሰዎች’ ይመሰክር ነበር። (ሥራ 17:17) እኛስ በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ የትኞቹን አጋጣሚዎች መጠቀም እንችላለን? ገበያ ስንወጣ፣ በሕዝብ መጓጓዣ ስንጠቀም፣ በሥራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት እነማንን ‘እናገኛለን?’ በቤትስ ለእነማን መመሥከር እንችላለን? አድማጮች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻቸው ወቅት ለሰዎች ምሥራቹን በመናገር ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ