ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 23, 2004 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 5 እስከ የካቲት 23, 2004 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርያት
1. የምናቀርበው ትምህርት ዋጋማነት ለአድማጮቻችን ግልጽ እንዲሆንላቸውና እንዲጠቅማቸው ምን ማድረግ እንችላለን? [be ገጽ 158 አን. 2-4]
2. የምንናገራቸውን ቃላት በጥንቃቄ መምረጥ የሚኖርብን ለምንድን ነው? [be ገጽ 160 አን. 1 እና ሁለተኛው ሣጥን]
3. በ1 ቆሮንቶስ 14:9 ላይ የጎላው ጥሩ ንግግር ለማቅረብ የሚያስችል መሠረታዊ ነገር ምንድን ነው? ንግግር በምናቀርብበት ጊዜ የጥቅሱን ሐሳብ ልንሠራበት የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 161 አን. 1-4]
4. ማቴዎስ 5:3-12 እና ማርቆስ 10:17-21 ላይ በተገለጸው መሠረት ከኢየሱስ ልንኮርጅ የምንችለው ግሩም የማስተማር ጥበብ የትኛው ነው? [be ገጽ 162 አን. 4]
5. ስናገለግልም ሆነ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ሐሳብ ስንሰጥ ኃይል ያላቸው፣ ስሜቱን የሚያስተላልፉና ገላጭ የሆኑ ቃላት ለመጠቀም ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? (ማቴ. 23:37, 38) [be ገጽ 163 አን. 3, 4]
ክፍል ቁጥር 1
6. የአንድ ንግግር ጭብጥ ምንድን ነው? በንግግራችን ውስጥ የምናካትታቸውን ሐሳቦች ስንመርጥና ስናደራጅ ጭብጡን በአእምሯችን መያዛችን ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 39 አን. 6–ገጽ 40 አን. 1]
7. (ሀ) በመንፈሳዊ ንጹሕ መሆን ምን ማለት ነው? ይህስ ከሁሉም የንጽሕና ዘርፎች የላቀ እንደሆነ ተደርጎ የሚታየው ለምንድን ነው? (ለ) ክርስቲያኖች በዓለም ላይ ተስፋፍቶ ከሚታየው የሥነ ምግባር ርኩሰት መራቅ የሚችሉት እንዴት ነው? [w02 2/1 ገጽ 5-6]
8. መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት መሠረታዊ ሥርዓቶች ሁሉ የላቀ ቦታ የሚይዙት የትኞቹ ናቸው? [w02 2/15 ገጽ 5 አን. 1, 4, 6]
9. የሌላውን ችግር እንደ ራስ መመልከት ምን ነገሮችን ይጨምራል? ኢየሱስ ይህን ባሕርይ ያሳየውስ እንዴት ነው? [w02 4/15 ገጽ 24 አን. 4 እና ገጽ 25 አን. 4, 5]
10. ምሳሌ 11:11 በይሖዋ ሕዝቦች ጉባኤ ውስጥ ምን ተፈጻሚነት አለው? [w02 5/15 ገጽ 27 አን. 1-3]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ዘፍጥረት 2:9 ላይ የተጠቀሰው ‘የሕይወት ዛፍ’ ምን ያመለክታል?
12. የሎጥ ሚስት ሕይወቷን እንድታጣ ያደረጋት ምንድን ነው? (ዘፍ. 19:26) [w90 4/15 ገጽ 18 አን. 10]
13. ዘፍጥረት ምዕራፍ 24 ላይ በሚገኘው ትንቢታዊ ድራማ (ሀ) አብርሃም፣ (ለ) ይስሐቅ፣ (ሐ) የአብርሃም አገልጋይ ኤሊዔዘር፣ (መ) አሥሩ ግመሎች እና (ሠ) ርብቃ ምን ያመለክታሉ?
14. አምላክ የያዕቆብንና የዔሣውን ዕጣ አስቀድሞ ወስኗል? (ዘፍ. 25:23)
15. ራሔል ልባዊ ጥረት ማድረጓና ይሖዋም ጥረቷን የባረከላት መሆኑ ለእኛ ምን ጥሩ ምሳሌ ይዟል? (ዘፍ. 30:1-8) [w02 8/1 ገጽ 29-30]