የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/04 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 2/04 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- ራእይ ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማግኘት ልዩ ጥረት ይደረጋል። የምናነጋግራቸው ሰዎች ይህ ጽሑፍ ካላቸው የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት ይበረከታሉ። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ለተገኙ ሆኖም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ አዘውትረው ለማይገኙ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍን እና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል።

◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት። ጉባኤው ለዓለም አቀፉ ሥራና በድርጅቱ ለሚካሄዱ ሌሎች ሥራዎች ያደረገውን መዋጮ አስመልክቶ የተላከ የምስጋና ደብዳቤ ካለ ይነበብ።

◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት የማኅበሩን ዓመታዊ S-201 ደብዳቤዎች ተመልከቱ።

◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2004 ልዩ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “ደፋሮች ሁኑ፣ በይሖዋ ታመኑ” የሚል ይሆናል። ከዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት በመስከረም 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን ማስታወቂያ ተመልከት።

◼ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ሁለተኛው የተማሪ ክፍል፣ የአገልግሎት ስብሰባ ክፍሎች፣ የልዩና የወረዳ እንዲሁም የአውራጃ ስብሰባ ንግግሮች የሚቀርቡት አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተባለው በ1993 የታተመ መጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል። ይህን መጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት የምትችሉ ከሆነ በእነዚህና በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ብትጠቀሙበት ጥሩ ይሆናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ