የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/04 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሚያዝያ 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 26 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 4/04 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሚያዝያ 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 97 (217)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “ደፋሮች ሁኑ፣ በይሖዋ ታመኑ” በሚል ርዕስ ለሚቀርበው ልዩ የሕዝብ ንግግር ሁሉም ሌሎች ሰዎችን እንዲጋብዙ አበረታታ። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2004 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ውይይቱን ለማስቆም “ሥራ አለብኝ” ለሚል ሰው በተለያየ መንገድ መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳዩ ይሁኑ።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 19-20 ተመልከት

15 ደቂቃ:- “ለይሖዋ ምርጣችንን መስጠት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ በአገልግሎታችን ላይ ለሰዎች ፍቅር ማሳየት የምንችልባቸውን መንገዶች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- የተግሣጽን ዓላማ መረዳት። በጥቅምት 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20-23 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

መዝሙር 18 (42) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 58 (138)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

17 ደቂቃ:- “የኢየሱስን አስተሳሰብ ኮርጁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ በረዳት አቅኚነት እያገለገሉ ያሉ በዚህ የአገልግሎት ዘርፍ መካፈላቸው ያስገኘላቸውን በረከት እንዲናገሩ ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- አካላዊ ንጽሕና ያስመሰግነናል። በሰኔ 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20-21 አንቀጽ 9-13 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ጥር 30, 2004 ለሁሉም ጉባኤዎች ከተላከው ደብዳቤ ላይ እና በጥቅምት 2003 ንቁ! መጽሔት ገጽ 11-13 ላይ ከወጣው “ጤንነትህን ለመጠበቅ የሚረዱ ስድስት መንገዶች” ከሚለው ርዕስ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 92 (209) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 21 (46)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የሚያዝያ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በግንቦት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የየካቲት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ለሥራ ባልደረባ ወይም ለትምህርት ቤት ጓደኛ ምሥክርነት ሲሰጥ የሚያሳይ ይሁን።

13 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- በሀብታችን አመስጋኝነታችንን ማሳየት። በታኅሣሥ 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19 አንቀጽ 17-19 እንዲሁም በኅዳር 16, 2001 እና በታኅሣሥ 10, 2002 ለሁሉም ጉባኤዎች በተላኩት ደብዳቤዎች ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 17 (38) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 23 (48)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በጉባኤያችሁ ብዙም ያልተሠራባቸው ክልሎች ካሉ ልዩ የአገልግሎት ክልል የመሸፈን ዘመቻ ከመጠናቀቁ በፊት ክልሎቹን ሙሉ በሙሉ ለማዳረስ ምን ዝግጅት እንደተደረገ ተናገር። ሁሉም በጉባኤያቸው ክልል ውስጥ እያሉም ሆነ ርቀው ሲሄዱ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን በየወሩ መስጠት እንዳይረሱ አስታውሳቸው።

15 ደቂቃ:- “ወጣቶች​—⁠የአምላክን ቃል አንብቡ!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራማቸው ምን እንደሚመስል እና ምን ጥቅሞች እንዳገኙበት የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት ወጣቶች አስቀድመህ አዘጋጅ። ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን ከዳር እስከ ዳር አንብበው የመጨረስ ግብ እንዲኖራቸው አበረታታ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 10 አንቀጽ 4 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ:- ሁልጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ሕግ ያስፈልግሃል? በታኅሣሥ 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20-23 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ።

መዝሙር 72 (164) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ