የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/04 ገጽ 2-3
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሐምሌ 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 26 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 2 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 7/04 ገጽ 2-3

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሐምሌ 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 80 (180)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን የመግቢያ ሐሳቦች በመጠቀም የግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 2004 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው የሚናገረውን ቋንቋ በደንብ መናገር ለማይችል ሰው በጎዳና ላይ መጽሔት ሲያበረክትለት የሚያሳይ ይሁን።

18 ደቂቃ፦ “የይሖዋን ፍትሕ ኮርጁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።

15 ደቂቃ፦ መጽሐፍ ቅዱስ​—⁠አስተማማኝ ትንቢቶችን የያዘ መጽሐፍ። ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ በተባለው ብሮሹር ገጽ 27-29 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አብዛኛውን ጊዜ በአገልግሎታችን ላይ የወደፊቱ ጊዜ የሚያሳስባቸው ሰዎች ያጋጥሙናል። መጽሐፍ ቅዱስ ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች አስደሳች የሆነ የወደፊት ሕይወት እንደሚጠብቃቸው አስተማማኝ መረጃ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ በሚናገራቸው ትንቢቶች ላይ ያለንን እምነት የሚያጠናክሩ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ተናገር። አንድ አስፋፊ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ታሪካዊ ክስተቶችን ተጠቅሞ አንድን ፍላጎት ያሳየ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን እምነት እንዲያሳድግ ሲረዳው የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 8 (21) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 83 (187)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብን አስፈላጊነት ተናገር። በነሐሴ 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ ያለውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት​—⁠ክፍል 1።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። አዋጅ ነጋሪዎች ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 572-4 ላይ በሚገኘው ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ የማስጠናቱ ሥራ በጊዜያችን እንዴት እንደጀመረ በሚናገረው ሐሳብ ላይ ተመሥርተው አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። አድማጮች በዚህ ርዕስ በተከታታይ ለሚወጡት ትምህርቶች ጉጉት እንዲያድርባቸው አድርግ። ወደፊት የሚወጡት ትምህርቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን ለመምራት ስለመዘጋጀት፣ ተማሪው ተዘጋጅቶ እንዲመጣ ስለመርዳት፣ በአንድ የጥናት ወቅት ምን ያህል ክፍሎችን መሸፈን እንደሚቻል፣ ጥቅሶችን በሚገባ ስለመጠቀም፣ ተማሪው ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች መልስ ስለመስጠት፣ ትምህርቱን በጸሎት ጀምሮ በጸሎት ስለመደምደም ለተማሪው እንዴት መንገር እንደሚቻል፣ ተማሪውን ወደ ድርጅቱ እንዴት መምራት እንደሚቻልና እነዚህን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ። ሁሉም የሚቀርቡትን ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርጉና የመንግሥት አገልግሎት እትሞቹን ወደፊት ሊጠቀሙባቸው በሚችሉበት ሁኔታ እንዲያስቀምጧቸው አሳስባቸው።

መዝሙር 5 (10) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 95 (213)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የሐምሌ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን የመግቢያ ሐሳቦች በመጠቀም የግንቦት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ውይይት ለማስቆም “አዘውትራችሁ የምትመጡት ለምንድን ነው?” ለሚል ሰው በተለያየ መንገድ እንዴት መመለስ እንደሚቻል የሚያሳዩ ይሁኑ።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 20ን ተመልከት።

8 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በአንድ ሽማግሌ የሚቀርብ። ሁሉንም አንቀጾች እያነበብክ ተወያዩባቸው።

25 ደቂቃ:- “በንግድ አካባቢዎች መስበክ የሚቻለው እንዴት ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በንግድ አካባቢዎች ለማገልገል ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅትና ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ጥቀስ። በአንቀጽ 4-5 ላይ የሚገኙትን ሁለት አቀራረቦች ወይም በአካባቢው ውጤታማ ሆኖ የተገኘ ሌላ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ጊዜ በፈቀደ መጠን አድማጮች በንግድ አካባቢዎች በማገልገል ያገኟቸውን አበረታች ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 39 (86) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 83 (187)

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናውን አዲስ መጽሐፍ ከተናገርክ በኋላ “ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለውን መጽሐፍ በማጥናት ተጠቀሙ” የሚለውን ርዕስ ተወያዩበት።

15 ደቂቃ፦ አሳማኝ ማስረጃ ታቀርባለህ? በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 254 አንቀጽ 1-2 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በመስክ አገልግሎት ላይም ሆነ ከመድረክ ንግግር በምናቀርብበት ወቅት ጥቅሶችን እየጠቀስን ስናብራራ እንዲያው ድርቅ ባለ ሁኔታ ሐሳባችንን ከመግለጽ ይልቅ አሳማኝ ማስረጃዎችን እያቀረብን ብናስረዳ በማስተማር ችሎታችን ይበልጥ ውጤታማ እንሆናለን። ከማመራመር መጽሐፍ ወይም ከሌሎች ጽሑፎች ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ምሳሌዎችን በመጠቀም (1) በአንድ ጥቅስ ላይ የሚገኙ ቁልፍ ሐሳቦችን ምረጥና አብራራ፣ (2) በጥቅሱ ዙሪያ ያሉትን ሐሳቦች ወይም ከጉዳዩ ጋር ተዛማጅነት ያለውን ሌላ ጥቅስ በመጠቀም ነጥቡን የሚደግፍ ተጨማሪ ማስረጃ አቅርብ፣ (3) ምሳሌ በመጠቀም የምትናገረውን ሐሳብ ትክክለኛነት አሳይ እንዲሁም (4) አድማጮች በጉዳዩ ላይ በጥሞና እንዲያስቡበት ለመርዳት ጥያቄዎችን ተጠቀም። አሳማኝ አቀራረብ መጠቀም ያለውን ጥቅም አጉላ።

15 ደቂቃ፦ ጸንተህ ቁም​—⁠አትደናቀፍ። በመጠበቂያ ግንብ 8-111 (ሚያዝያ 15, 1990) ገጽ 26-28 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ።

መዝሙር 12 (32) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ