የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
መስከረም 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19 (43)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የነሐሴን የመንግሥት አገልግሎታችን እትም በሚቀጥለው ሳምንት ይዘው እንዲመጡ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ ያሉት አቀራረቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ እነርሱን ተጠቅመህ የሐምሌ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 2004 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሌሎች አቀራረቦችንም መጠቀም ይቻላል። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የአቀራረቡን መልካም ጎን በአጭሩ ጥቀስ።
15 ደቂቃ፦ አሠሪህን ፈቃድ ጠይቀኸዋል? አንድ ሽማግሌ በመስከረም 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 ላይ በወጣው “አንተስ በዚያ ትገኝ ይሆን?” በሚል ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 67 ላይ የተወሰኑ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
18 ደቂቃ፦ መልካም ሥራችንን ሰዎች ይመለከታሉ። (1 ጴጥ. 2:12) በኅዳር 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 12-14 አንቀጽ 14-20 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች በአካባቢያችን ያሉ ሰዎች መልካም ሥራችንን ተመልክተው እንዴት እንደተነኩ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 70 (162) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጥቅምት 4 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም ዘኍልቍ 16:1-35ን አንብበውና የይሖዋን ሥልጣን አክብሩ የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም ተመልክተው እንዲመጡ አበረታታቸው።
15 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስላል? አንድ ሽማግሌ በጉባኤው የ2004 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ላይ ተመሥርቶ በንግግር ያቀርበዋል። አበረታች በሆኑት ጎኖች ላይ በማተኮር ወንድሞችና እህቶችን ለመልካም ጥረታቸው አመስግናቸው። አቅኚዎች ያከናወኑትን ትጋት የታከለበት ሥራ ጎላ አድርገህ ግለጽ። በያዝነው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚችላቸውን አንድ ወይም ሁለት ዘርፎች ጥቀስ።
20 ደቂቃ፦ “የአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት—ታላቅ የሥራ በር።” በነሐሴ 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከ2004 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 239-40 ላይ አንዳንድ ነጥቦች ጨምረህ አቅርብ። በወረዳ ስብሰባ ላይ በአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለመሠልጠን ፍላጎት ላላቸው ወንድሞች ተብሎ ስለሚዘጋጀው ስብሰባ ተናገር። ብቃቱን የሚያሟሉ በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ አበረታታቸው።
መዝሙር 28 (58) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 99 (221)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የመስከረም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የሐምሌ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። “የወረዳና የልዩ ስብሰባዎችን ለመከለስ የተደረገ አዲስ ዝግጅት” የሚለውን ርዕስ በንግግር አቅርበው። የወረዳና የልዩ ስብሰባዎች የሚካሄዱባቸው ቀኖች የሚታወቁ ከሆነ ተናገር። ለመጠመቅ የሚፈልጉ ካሉ አስቀድመው ለሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
10 ደቂቃ፦ የይሖዋ ቃል ሕያው ነው። በንግግር የሚቀርብ። ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም የተሟላ ጥቅም ማግኘት እንድንችል በቅርቡ በአንዳንድ የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው” በሚል ጭብጥ ተከታታይ ትምህርቶች መውጣት ጀምረዋል። በመስከረም 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 24-7 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም የዚህን ርዕስ የተለያዩ ገጽታዎች አጉላ። አጠቃላይ የምዕራፎቹ ሐሳብ ከቀረበ በኋላ “ቅዱስ ጽሑፋዊ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው” የተባለው ክፍል ለመረዳት አስቸጋሪ በሆኑ አንዳንድ ጥቅሶች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል። “ምን ትምህርት እናገኛለን?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር የሚወጡት ሐሳቦች የምዕራፎቹን ተግባራዊ ጠቀሜታ እንድናስተውል ይረዱናል። “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው” በሚል ጭብጥ የሚወጣው ተከታታይ ትምህርት የአምላክን ቃል የበለጠ ለመረዳት የሚያስችለን እንዴት እንደሆነ ለማሳየት የተወሰኑ ምሳሌዎችን ጥቀስ። በቀጣዩ ሳምንት የዘዳግም መጽሐፍን ማንበብ ስለምንጀምር ሁሉም በዚህ ዝግጅት በሚገባ እንዲጠቀሙ አበረታታቸው።
20 ደቂቃ፦ “መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ተጠቀሙበት።” በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 145 አንቀጽ 2-3 ላይ ያለውን ርዕስ መሠረት አድርገህ አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። በርዕሱ ውስጥ የቀረቡትን የመግቢያ ሐሳቦች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ለማሳየት የመጀመሪያ ቀን ውይይትና ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 17 (38) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ጤናማ ዓይን ይኑራችሁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ለአንቀጾቹ በቀረቡት ጥያቄዎች በመጠቀም በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱት ጥቅሶች እንዲብራሩ አድርግ።
25 ደቂቃ፦ “የይሖዋን ሥልጣን ማክበር አለብን።” ሁለት ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ይሁዳ 11ን አንብብ። ከዚያም በርዕሱ ውስጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም በቀጥታ ከአድማጮች ጋር ውይይት ጀምር። የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት ቆሬ ከተከተለው የዓመጸኝነት አካሄድ መራቅና ለይሖዋ ያላቸውን ታማኝነት በአንደኛ ቦታ ያስቀመጡትን የልጆቹን ምሳሌ መኮረጅ እንዳለብን ጎላ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።