የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ማሳሰቢያ፦ የመንግሥት አገልግሎታችን የአውራጃ ስብሰባ በምታደርጉበት ወር የሁሉንም ሳምንታት ፕሮግራም ይዞ ይወጣል። ጉባኤዎች “ከአምላክ ጋር መሄድ” በተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ ላይ በሚገኙበት ሳምንት የሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም እንዳያመልጣቸው እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ማድረግ ይችላሉ። የሚቻል ከሆነ ከአውራጃ ስብሰባው በፊት ባለው ሳምንት በምታደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ 15 ደቂቃ ወስዳችሁ በቅርብ ወራት በወጡ የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪዎች ላይ የአውራጃ ስብሰባውን በሚመለከት ከሰፈሩት ጠቃሚ ምክሮች ውስጥ ለጉባኤው ያስፈልጋሉ የምትሏቸውን ከልሱ። ሁሉም የአውራጃ ስብሰባዎች ሲጠናቀቁ የፕሮግራሙን ጎላ ያሉ ነጥቦች ለመከለስ አንድ ሙሉ የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ይመደባል። በዚህ የክለሳ ውይይት ላይ ጥሩ ተሳትፎ ለማድረግ ሁላችንም በስብሰባው ወቅት ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦችን እንዲሁም በግል ሕይወታችንና በመስክ አገልግሎት ላይ ልንሠራባቸው የምንፈልጋቸውን ዝርዝር ሐሳቦች በማስታወሻ መያዝ እንችላለን። ከዚያም በውይይቱ ላይ እነዚህን ምክሮች ከአውራጃ ስብሰባው በኋላ እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደቻልን በመናገር ሌሎችን ማበረታታት እንችላለን።
ጥቅምት 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 13 (33)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
22 ደቂቃ፦ “ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸውን ሥራዎች በፈቃደኝነት ትሠራለህ?” ከግንቦት 15, 1975 የመጠበቂያ ግንብ እትም አጠር ባለ መልክ የቀረበውን የዚህን ርዕስ የመጀመሪያ አምስት አንቀጾች አንድ ሽማግሌ በንግግር ያቀርባቸዋል። ቁልፍ ነጥቦችን አንብብ። እንዲሁም በቤቴል፣ በቤት ውስጥ፣ በመንግሥት አዳራሽ ወይም በየትኛውም ቦታ የሚከናወኑት የጉልበት ሥራዎች ዝቅ ተደርገው መታየት የሌለባቸው ለምን እንደሆነ ተናገር።
15 ደቂቃ፦ ሌሎችን በመርዳት ደስታ አግኙ። (ዮሐ. 4:34) ቃለ ምልልስ። አንድ ሰው በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን እውነት ሲማርና በዚህም የተነሳ ፊቱ በደስታ ሲፈካ መመልከት በጣም ያስደስታል። (w94 3/1 ገጽ 29 አን. 6-7) በአገልግሎታቸው ላይ መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመርና በማስጠናት ረገድ ለተዋጣላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ወይም አቅኚዎች ቃለ መጠይቅ አድርግላቸው። ለምሥራቹ አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ሲያገኙ ፍላጎታቸውን የሚኮተኩቱት እንዴት ነው? እንዲህ በማድረጋቸው ምን ደስታ አግኝተዋል? በአገልግሎታቸው ላይ ያጋጠሟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ወይም በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 51 (127)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ካሉት አቀራረቦች ውስጥ ለጉባኤህ ክልል ተስማሚ የሆኑትን በመጠቀም የነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 2004 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ በሽታ በተስፋፋበት በዚህ ዘመን ለሌሎች አሳቢነት ማሳየት። አንድ ሽማግሌ ከሚያዝያ-ሰኔ 1995 ንቁ! መጽሔት ገጽ 16 አንቀጽ 3-5, ገጽ 18 አንቀጽ 7ና ገጽ 19 አንቀጽ 6 ላይ የተወሰኑ ሐሳቦችን ያቀርባል። በበሽታ ለተጠቁ ሰዎች አዘኔታ ማሳየት የሚቻልባቸውን መንገዶች ስትጠቅስ ከጥር 1999 ንቁ! መጽሔት ገጽ 9 ላይ “በእርግጥ የሚደነቅ ጉባኤ ነው” በሚል ንዑስ ርዕስ ሥር የቀረበውን ሐሳብ ተናገር። ከዚያም ማቴዎስ 7:12ን እና ፊልጵስዩስ 2:4ን አንብብና የቫይረሱ ተሸካሚ የሆኑ ሰዎች ባሕላዊ በሆኑ የሰላምታ አሰጣጦች፣ በቤት ውስጥ ዕቃዎች አጠቃቀም ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ረገድ እንዴት አሳቢነት ማሳየት እንደሚችሉ ተናገር።
15 ደቂቃ፦ አምላክ ሀብት በመስጠት ይባርከናል? በጥቅምት 2003 ንቁ! መጽሔት ገጽ 14 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። ወደ ሌላ አገር ከመሄድ፣ የሥራ እድገት ከማግኘትና እነዚህን ከመሳሰሉ ነገሮች ጋር በተያያዘ በአካባቢያችን ካለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ጋር አያይዘህ አቅርብ።
መዝሙር 57 (136) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 (56)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በገጽ 8 ላይ ያለውን አቀራረብ በመጠቀም (ለጉባኤህ ክልል ተስማሚ ከሆነ) የነሐሴ 15 መጠበቂያ ግንብን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያው ውይይት ለማስቆም “የይሖዋ ምሥክሮችን አልፈልግም” ለሚል ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 17ና 18ን ተመልከት።
18 ደቂቃ፦ የአምላክን ቃል የሚደግፍ ማስረጃ አቅርቡ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 256-7 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ማስረጃዎችን ተጠቅመን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ እውነት መሆኑን ሰዎች እንዲያስተውሉ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? አድማጮች በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ:- የፈጣሪን መኖር በማስረጃ ለማሳየት ከግዑዙ አጽናፈ ዓለም ውስጥ ምን ምሳሌ መጥቀስ እንችላለን? (ማመራመር ገጽ 83-85) ሌሎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን እንዲቀበሉ ለመርዳት ምሑራን ወይም ባለሙያዎች የሰጡትን አስተያየት መጥቀስ የምንችለው እንዴት ነው? (ማመራመር ገጽ 61-62) አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደበትን ምክንያት ለሌሎች ለማስረዳት ምን ምሳሌ ወይም ንጽጽር መጠቀም እንችላለን? (ማመራመር ገጽ 429) የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር መከተል ያለውን ጥቅም ሌሎች እንዲያስተውሉ ለመርዳት እስካሁን በየትኞቹ ተሞክሮዎች ወይም ምሳሌዎች ተጠቅማችኋል?
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 29 (62) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 100 (222)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም አስፋፊዎች የጥቅምት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በኅዳር ወር አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር እናበረክታለን። በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 ላይ የወጡትን ብሮሹሩን ለማበርከት የሚያስችሉ አቀራረቦች በአጭሩ ከልስና አንዱ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸውን ሥራዎች በፈቃደኝነት ትሠራለህ?” ከግንቦት 15, 1975 የመጠበቂያ ግንብ እትም ላይ አጠር ባለ መልክ በቀረበው በዚህ ርዕስ ከአንቀጽ 6-9 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ዋና ዋና ሐሳቦችን አንብብ፤ የጉልበት ሥራ ይሠሩ የነበሩትን የዳዊትን፣ የጳውሎስንና የኢየሱስን ምሳሌ ጥቀስ። አንድ ክርስቲያን እንደ ዘበኝነት፣ አትክልተኛነት፣ የቤት ሠራተኛነት ወይም ጫማ መጥረግ ለመሳሰሉ ሥራዎች ሊኖረው የሚገባውን አመለካከት በምክንያት አስደግፈው እንዲናገሩ አድማጮችን ጠይቅ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በሚያዝያ 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28ና 29 ላይ ከወጣው “ይሖዋ ተራ ለሆኑ ሰዎች ያስባል” ከሚለው ርዕስ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 78 (175) እና የመደምደሚያ ጸሎት።