የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/05 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 14 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 21 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 28 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 4 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 3/05 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

መጋቢት 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 54 (132)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙት የመግቢያ ሐሳቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ በእነዚህ መግቢያዎች በመጠቀም የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው ለመጽሔት ደንበኛው ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግ የሚያሳይ ይሁን። አስፋፊው በቅርቡ የመታሰቢያ በዓል እንደሚከበርም ያስታውሰዋል።

20 ደቂቃ:- “ይበልጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያተኮረ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

15 ደቂቃ:-እኛን ለማበረታታት የተደረገ ዝግጅት። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በ2005 የዓመት መጽሐፍ ላይ ከአድማጮች ጋር ተወያዩ። ይሖዋ በዘመናችን ባደረጋቸው አስደናቂ ነገሮች ላይ ማሰላሰላችን ከእርሱም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከሚኖሩ ወንድሞቻችን ጋር እንድንቀራረብ ያደርገናል። (መዝ. 77:12-14) እንዲሁም ዲያብሎስን ‘በእምነት ጸንተን’ መቃወም እንድንችል ያጠነክረናል። (1 ጴጥ. 5:8, 9) አዲሶች የይሖዋን ድርጅት እንዲያደንቁ ይረዳቸዋል። አድማጮች የ2005ን የዓመት መጽሐፍ ሲያነብቡ ጠቃሚ ሆነው ያገኟቸውን ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች በግላቸው የዓመት መጽሐፉን ለማንበብ የሚያስችላቸው ፕሮግራም እንዴት እንዳወጡ እንዲናገሩ አስቀድመህ አዘጋጅ።

መዝሙር 62 (146) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 84 (190)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 7።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ይህንን ክፍል ስትዘጋጅ የሐምሌ 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 27 አንቀጽ 5ና 6ን ተመልከት።

20 ደቂቃ:- አርማጌዶን ምንድን ነው? አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ገጽ 43-47 ላይ ያለውን ሐሳብ በጥያቄና መልስ አቅርብ። አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን እንዲሁም ሐሳባቸው በመጽሐፉ ላይ የቀረቡትን ጥቅሶች በመጠቀም ደመቅ ባሉ ፊደላት ለተጻፉት ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ ጋብዛቸው። ይህንን ሐሳብ በአገልግሎታችን እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል ተወያዩ።

መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 61 (144)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርቱንና ጉባኤው ላደረገው አስተዋጽኦ ከቅርንጫፍ ቢሮው የተላከውን ምስጋና ተናገር። ሚያዝያ 10 ለሚቀርበው ልዩ የሕዝብ ንግግር የጉባኤው አባላት በሙሉ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች እንዲጋብዙ አበረታታ። በሚያዝያና በግንቦት የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን አበርክቱ። በየካቲት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ የወጡትን ከበፊቱ የበለጠ መጽሔቶች ለማበርከት እንድንችል የሚረዱ ሐሳቦች ከልስ። በቅርብ የወጡ መጽሔቶች ላይ የሚገኙ የሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ነጥቦችን ጥቀስ። በገጽ 4 ላይ የሚገኘው የመግቢያ ሐሳብ ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆነ በዚያ በመጠቀም የጥር 15ን መጠበቂያ ግንብ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። በሠርቶ ማሳያው ላይ አስፋፊው ዓለም አቀፉ ሥራችን የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።—መጠበቂያ ግንብ ላይ ገጽ 2ን ወይም ንቁ! ላይ ገጽ 5ን ተመልከት።

መዝሙር 95 (213) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 81 (181)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። (ዮሐ. 13:15) አንድ ሽማግሌ በየካቲት 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 15-18 አንቀጽ 10-21 ላይ ተመሥርቶ በንግግር ያቀርበዋል። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ቢገኙም ወደ ጉባኤ ስብሰባዎች አዘውትረው ለማይመጡ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ልናደርግላቸው እንችላለን። እውቀት መጽሐፍንና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ያጠኑ ሰዎችን የአምልኮ አንድነት በተባለው መጽሐፍ በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት እናድርግ። አስፋፊዎች በመንፈሳዊ የደከሙትን ለመርዳት ከሽማግሌዎች ጋር እንዴት ተባብረው መሥራት እንደሚችሉ ግለጽ።

25 ደቂቃ:- በሀብታችን አመስጋኝነታችንን ማሳየት። በታኅሣሥ 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19 አንቀጽ 17-19 እንዲሁም ኅዳር 16, 2001 እና ታኅሣሥ 10, 2002 ለሁሉም ጉባኤዎች በተላኩት ደብዳቤዎች ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 29 (62) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ