የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/05 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 3/05 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት:- ነቅተህ ጠብቅ! ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ሰኔ:- የቤተሰብ ደስታ።

◼ አዳዲስ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ወደ ጉባኤዎች እንደደረሱ አስፋፊዎች እንዲወስዱ ማድረግ ይገባል። እንደዚህ መደረጉ አስፋፊዎች መጽሔቶቹን በአገልግሎት ላይ ከማበርከታቸው በፊት ማንበብ እንዲችሉ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል። የመንግሥት አገልግሎታችንም ቢሆን ወደ ጉባኤው እንደደረሰ ለአስፋፊዎች ሊሰጥ የሚገባ ሲሆን ይህንንም በመጽሐፍ ጥናት ላይ ማድረግ ይቻላል።

◼ ወደ ሌላ አገር በምትጓዙበት ወቅት በዚያ በሚደረገው የጉባኤ፣ የወረዳና የልዩ ወይም የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ትፈልጉ ይሆናል። እነዚህ ስብሰባዎች የሚካሄዱበትን ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ለማወቅ በዚያ አገር ያለውን ሥራ ለሚቆጣጠረው ቅርንጫፍ ቢሮ መጻፍ ይኖርባችኋል። የተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ በቅርብ ከወጣው የዓመት መጽሐፍ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205-AM) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b-AM) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቁ ቅጾች ይኑሯችሁ።

◼ የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ሐሙስ መጋቢት 24, 2005 ነው። ጉባኤያችሁ ሐሙስ ዕለት ስብሰባ ያደርግ ከነበረ ይህን ስብሰባ የመንግሥት አዳራሹ ነጻ ወደሚሆንበት ሌላ ቀን ማዛወር ይኖርባችኋል። እንዲህ ማድረግ ካልተቻለና የአገልግሎት ስብሰባው ሳይቀርብ ከቀረ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑትን ክፍሎች በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ማካተት ይቻላል።

◼ በርከት ያሉ አስፋፊዎች በአሁኑ ወቅት በወንድሞች እጅ የሚገኙ ተወዳጅ በሆነ ዘመናዊ ስታይል የተዘጋጁ የመንግሥቱ መዝሙሮችን በተመለከተ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ስልክ በመደወል እነዚህ ቅጂዎች የድርጅቱን ፈቃድ ያገኙ መሆን አለመሆናቸውን ጠይቀዋል። እንዲህ ዓይነት ቅጂዎች መኖራቸውን የሰማን ቢሆንም እነዚህ መዝሙሮች በእኛ ፈቃድ የወጡ አለመሆናቸውን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። እባካችሁ እንደዚህ ያሉትን ቅጂዎች ለማሰራጨት ወይም ከኢንተርኔት ላይ ለመውሰድ አትሞክሩ። ይህ ማስታወቂያ ጉዳዩን ግልጽ እንደሚያደርገው ተስፋ እናደርጋለን።

◼ አዲስ የደረሱን:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር 2005 (አማርኛ፣ አረብኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስፓንኛና ትግርኛ)፤ ኑዌር:- T-16።

◼ በድጋሚ የደረሱን:- እንግሊዝኛ:- ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ፣ መለኮታዊው ስም፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፣ ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?፣ ጅሆቫስ ዊትነስስ ኤንድ ኤጁኬሽን፣ የኢሳይያስ ትንቢት-1፣ T-26፤ ጣልያንኛ:- Bi12፤ ትግርኛ:- ታላቅ ሰው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ