የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/05 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሰኔ 13 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 27 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 4 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 6/05 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሰኔ 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 79 (177)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስ​ማሚ ከሆኑ) የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ መደበኛ ባልሆነ መንገድ መጽሔት ሲበረከት የሚያሳይ ይሁን።

15 ደቂቃ:- ሌሎች ያልተጠመቁ አስፋፊዎች እንዲሆኑ እርዷቸው። አንድ ሽማግሌ የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 79-81 ላይ ባለው ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ከጉባኤው ጋር በአገልግሎት ለመካፈል ቅዱስ ጽሑፋዊ ብቃቶችን ያሟላ መሆን አለመሆኑ የሚወሰነው እንዴት እንደሆነ ተወያዩ። በሚቀጥለው ሳምንት፣ ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን ብቃቱን ያሟሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ከቤት ወደ ቤት ማገልገል እንዲጀምሩ እንዴት ማሠልጠን እንደምንችል እናያለን።

20 ደቂቃ:- “የስብከቱ ሥራ እንድንጸና ይረዳናል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሰው ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 7 (19)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከሐምሌ 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 ላይ ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ከልስ። አስፋፊዎች በውጭ አገር ቋንቋ የተዘጋጀ ጽሑፍ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ አስረዳ። ይህ ክፍል በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ እንዴት ሊሠራ እንደሚችል ተናገር። በውጭ አገር ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎችን (አንድም እንኳ ቢሆን) ለማግኘት ማንኛውም ትእዛዝ መላክ ያለበት በጽሑፍ አገልጋዩ በኩል ነው። እንዲህ ከተደረገ የተፈለገው ጽሑፍ ሳይዘገይ ሊደርስ ይችላል።

15 ደቂቃ:- የአምላክ ቃል ኃይል አለው። (ዕብ. 4:​12) በኅዳር 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11 ከአንቀጽ 13-17 ላይ የተመሠረተ ንግግር። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሰዎች በሕይወታቸው ላይ ለውጥ እንዲያደርጉ እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን አክለህ ተናገር። (w00 1/1 ከገጽ 3-5) ሁሉም በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች መጽሐፍ ቅዱስን በጥሩ ሁኔታ እንዲጠቀሙ አበረታታቸው።

20 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 10።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አስቀድመው ሲለማመዱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ተማሪው አቀራረቡን ሲለማመድ አስጠኚው እንደ ቤቱ ባለቤት በመሆን በአካባቢው የተለመደ አንድ የተቃውሞ ሐሳብ ይሰነዝራል፤ ከዚያም ተማሪው ምን ብሎ እንደሚመልስ ግራ መጋባቱን ሲያይ ነገሩን እንዴት መያዝ እንዳለበት ያብራራለታል። ከቤት ወደ ቤት ማገልገል በጀመሩበት ወቅት ሥልጠና አግኝተው የነበሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ሐሳብ እንዲሰጡ አስቀድመህ አዘጋጅ።

መዝሙር 87 (195) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 48 (113)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሰኔ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም (ለአገልግሎት ክልላችሁ የሚስማማ ከሆነ) የሚያዝያ 15ን መጠበቂያ ግንብ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ሌላ መግቢያ መጠቀም ይቻላል። ከሠርቶ ማሳያው በኋላ የቤቱን ባለቤት ፍላጎት ለመቀስቀስ የተጠቀመበትን የመግቢያ ሐሳብ ደግመህ ተናገር።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- በሐምሌና በነሐሴ ብሮሹሮችን አበርክቱ። በአባሪው ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በገጽ 3 ላይ ያለውን ሣጥንና ከጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 ላይ የሚገኙትን ቁልፍ ነጥቦች ጎላ አድርገህ በመግለጽ በአባሪው እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በአጭሩ አብራራ። በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ ከቤት ወደ ቤት ብሮሹሮችን ለማበርከት ተስማሚ የሆኑትን የመግቢያ ሐሳቦች ተናገር። ሁለት ወይም ሦስት አቀራረቦችን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ቢያንስ አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ወጣት አስፋፊ ሲያቀርበው የሚያሳይ ይሁን።

መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 32 (70)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- የቤተሰብ ፕሮግራማችሁ ምን ጥቅም አስገኝቶላችኋል? በግንቦት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የቀረበውን ሐሳብ ከልስ፤ በተጨማሪም አድማጮች የተሰጠውን ሐሳብ ለመተግበር ያደረጉትን ጥረትና እንደዚያ በማድረጋቸው ያገኙትን ጥቅም እንዲናገሩ ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- “ሕዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ መመሥከር።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ምን ማድረግ እንደሚቻል ተናገር። አስፋፊዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የሚለውን ቅጽ እንዲጠቀሙ አስታውሳቸው።​—⁠የየካቲት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6ን ተመልከት።

መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ