ብሮሹሮችን ለማበርከት የሚረዱ መግቢያዎች
በቅርብ አስቀምጡት
በዚህ አባሪ ላይ ብሮሹሮችን ለማበርከት የሚያስችሉ መግቢያዎችን ለማዘጋጀት እንዲረዱ የተለያዩ ሐሳቦች ቀርበዋል። የቀረቡትን ሐሳቦች እንደ አካባቢው ሁኔታ ተስማሚ አድርጎ ማቅረብ ወይም ሌሎች መግቢያዎችን መጠቀም ይቻላል። በዚህ አባሪ ላይ ያልተካተቱ ሌሎች መግቢያዎችን ቀጥሎ በቀረቡት ናሙናዎች መልክ ማዘጋጀት ይቻላል።—የጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6ን ተመልከት
በዚህ ገጽ ላይ የቀረበው እያንዳንዱ መግቢያ (1) ውይይት ለመጀመር የሚያስችል ስሜት ቀስቃሽ ጥያቄ፣ (2) የመነጋገሪያ ነጥቦቹ በብሮሹሩ ውስጥ የት ቦታ ላይ እንደሚገኙ የሚጠቁም መረጃ እንዲሁም (3) በውይይቱ ላይ ሊነበብ የሚችል ተስማሚ ጥቅስ ይዟል። ያነጋገርከው ሰው በሚሰጥህ ምላሽ ላይ ተመርኩዘህ ቀሪውን የመግቢያ ሐሳብ በራስህ አባባል ልታሟላው ትችላለህ።
ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ
“መጽሐፍ ቅዱስ ለዘመናችን የሚሠራ ምክር ይዟል ብለው ያስባሉ?”—ገጽ 22 የመግቢያው ሐሳብ፤ ገጽ 23 ላይ ያለው ሣጥን አን. 3፤ ምሳሌ 25:11
እርካታ ያለው ሕይወት—እንዴት ማግኘት ይቻላል?
“በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የተሻለ ሕይወት መምራት ይፈልጋሉ። እውነተኛ እርካታ ያለው ሕይወት ማግኘት የሚቻል ይመስልዎታል?”—ገጽ 29 አን. 6፤ 2 ጴጥ. 3:13
በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!
“ብዙ ሰዎች ደስታ የሰፈነበት ዘላለማዊ ሕይወት አግኝተው ለመኖር ወደ ሰማይ መሄድ እንደሚኖርባቸው ይሰማቸዋል። ሆኖም በምድር ላይ ለዘላለም መኖር የሚቻል ይመስልዎታል?”—መጽሔቱ ሽፋን ላይ ያለው ሥዕል፤ ራእይ 21:4
በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?
“የአምላክን እውነተኛ ማንነት አስመልክቶ ሰዎች የተለያየ አስተሳሰብ አላቸው። ይህን በተመለከተ የምናምነው ነገር ለውጥ ያመጣል ብለው ያስባሉ?”—ገጽ 3 አን. 3, 7–8፤ ዮሐ. 17:3
ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም
“ብዙዎቻችን ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ’ በማለት የሚጀምረውን ጸሎት እናውቀዋለን። (ማቴ. 6:9) ሆኖም መዳናችን የተመካው ይህንን ስም በማወቃችን ላይ እንደሆነ ተገንዝበዋል?”—ገጽ 28 አን. 1፤ ሮሜ 10:13
የአምላክ መንግሥት
ገነትን ታመጣለች
“በርካታ ሰዎች አሁን ያሉት ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙበትን ጊዜ ለማየት ይናፍቃሉ። እነዚህን ችግሮች ሊያስወግድ የሚችል መንግሥት ይመጣ ይሆናል ብለው አስበው ያውቃሉ?”—ገጽ 3 አን. 1፤ ማቴ. 6:9, 10
ስንሞት ምን እንሆናለን?
“የምንወዳቸው ሰዎች በሞት ሲለዩን ‘ያሉት የት ነው? እንደገና እንገናኝ ይሆን?’ እያልን መጠየቃችን የተለመደ ነገር ነው። እርስዎስ እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎችን ጠይቀው ያውቃሉ?”—የመጽሔቱ የኋላ ሽፋን ላይ ያሉት ጥያቄዎች፤ ኢዮብ 14:14, 15
የምትወዱት ሰው ሲሞት
“ወዳጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን በሞት ያጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አንብበውት ትልቅ መጽናኛና ተስፋ ያገኙበትን አንድ ብሮሹር እያስተዋወቅን ነው። የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው ብለው ጠይቀው ያውቃሉ?”—ገጽ 27 አን. 3፤ ዮሐ. 5:28, 29
“ወዳጁ ወይም ዘመዱ የሞተበትን ሰው እንዴት ላጽናናው እችላለሁ ብለው አስበው ያውቃሉ?”—ገጽ 20 አን. 1፤ ምሳሌ 17:17