የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/05 ገጽ 4
  • አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተባለውን ብሮሹር ለማበርከት የሚረዱ መግቢያዎች
  • አንድ አሳዛኝ ዜና ከጠቀስክ በኋላ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-
  • ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-
  • አንድ ወጣት አስፋፊ እንዲህ ሊል ይችላል:-
  • ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-
  • በዕድሜ ትልቅ የሆነ አንድ አስፋፊ ከትንሽ ልጅ ጋር ሲያገለግል ራሱንና ልጁን ካስተዋወቀ በኋላ እንዲህ ሊል ይችላል:-
  • ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርጉ ትልቁ አስፋፊ እንዲህ ሊል ይችላል:-
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 6/05 ገጽ 4

አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?

ተባለውን ብሮሹር ለማበርከት የሚረዱ መግቢያዎች

አንድ አሳዛኝ ዜና ከጠቀስክ በኋላ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-

“አምላክ በእርግጥ የሚያስብልን ከሆነ በሰው ልጆች ላይ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] ይህ ብሮሹር ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ከመስጠቱም በተጨማሪ አምላክ በቅርቡ ምን እርምጃ እንደሚወስድ ይገልጻል። [በገጽ 27 ላይ ያሉትን ሥዕሎች ካሳየኸው በኋላ አንቀጽ 22 ላይ የተጠቀሰውን መዝሙር 145:​16ን አንብብ።] ታዲያ አምላክ የሰው ልጆች የሚደርስባቸውን መከራ የሚያስወግደው እንዴት ነው? ሌላ ቀን መጥቼ ይህን ጥያቄ በተመለከተ ብንወያይ ደስ ይለኛል።” ብሮሹሩን አበርክትና ሌላ ጊዜ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዝ።

ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-

“ባለፈው ጊዜ ይህን ጥቅስ አንብበን ነበር። [መዝሙር 145:​16ን አውጥተህ አንብብ ወይም ሐሳቡን ጥቀስ።] በኋላም አምላክ የሰው ልጆች የሚደርስባቸውን መከራ የሚያስወግደው እንዴት ነው? የሚለውን ጥያቄ አንስቼ ነበር።” የሰጠኸውን ብሮሹር እንዲያመጣ ጠይቀው። ከዚያም ገጽ 27 እና 28ን ገልጠህ ከአንቀጽ 23-25 ባሉት ሐሳቦች ላይ ተወያዩ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ግብዣ አቅርብለት፤ ወይም በአንቀጽ 26 እና 27 ላይ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ያዝ።

አንድ ወጣት አስፋፊ እንዲህ ሊል ይችላል:-

“በእኔ ዕድሜ የሚገኙ ብዙ ወጣቶች ከዛሬ አሥር፣ አሥራ አምስት ዓመት በኋላ የዓለማችን ሁኔታ ምን ሊመስል እንደሚችል ያሳስባቸዋል። እርስዎስ በዚያ ጊዜ የዓለም ሁኔታ ምን የሚሆን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] በዛሬው ጊዜ የሚታዩት ችግሮች የምንኖረው በመጨረሻው ዘመን ውስጥ እንደሆነ ይጠቁማሉ። [2 ጢ⁠ሞቴዎስ 3:​1-3ን አንብብ።] ይህ ብሮሹር ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። [በብሮሹሩ ሽፋን ላይ ያሉትን ጥያቄዎች አንብብና እንዲወስደው ግብዣ አቅርብለት።] ተመልሼ ስመጣ በሽታና እርጅና እንደሚወገዱ የሚናገረውን አስደሳች ተስፋ ለጥቂት ደቂቃ ባወያይዎት ደስ ይለኛል።” እንደገና ለመገናኘት ቀጠሮ ያዝ።

ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-

“ባለፈው ጊዜ ባደረግነው ውይይት ላይ በሽታና እርጅና እንደሚወገዱ የሚናገር ሐሳብ ላካፍልዎ እንደምፈልግ ነግሬዎት ነበር። ይህን ነጥብ እዚህ ላይ ማግኘት እንችላለን።” የሰጠኸውን ብሮሹር እንዲያመጣ ንገረው። ከዚያም ከገጽ 23-24 አንቀጽ 6 እና 7ን አንብባችሁ ተወያዩባቸው። በሌላ ጊዜ ተገናኝታችሁ አንቀጽ 8 እና 9ን ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።

በዕድሜ ትልቅ የሆነ አንድ አስፋፊ ከትንሽ ልጅ ጋር ሲያገለግል ራሱንና ልጁን ካስተዋወቀ በኋላ እንዲህ ሊል ይችላል:-

“ፈቃድዎ ከሆነ፣ እገሌ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሊያነብልዎት ይፈልጋል። [ልጁ መዝሙር 37:​29ን ካነበበ በኋላ አጠር ያለ ገለጻ ይሰጣል።] ይህ ብሮሹር አምላክ ለሰው ልጆችና ለምድር ያለውን ዓላማ እንዴት እንደሚፈጽም ያብራራል። [ከገጽ 24-27 ያሉትን ሥዕሎች አሳየው።] በሌላ ጊዜ መጥተን መጽሐፍ ቅዱስ አስደሳች ስለሆነው የትንሣኤ ተስፋ የሚናገረውን ሐሳብ ባሳይዎት ደስ ይለኛል።” ብሮሹሩን አበርክትለትና ሌላ ቀን ለመገናኘት ቀጠሮ ያዝ።

ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርጉ ትልቁ አስፋፊ እንዲህ ሊል ይችላል:-

“ከዚህ በፊት ባደረግነው ውይይት ላይ መዝሙር 37:​29ን አንብበን ነበር፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ትንሣኤን በሚመለከት ምን እንደሚል ላሳይዎት እንደምፈልግ ነግሬዎት ነበር። እዚህ ላይ ምን እንደሚል ይመልከቱ።” የራሱን ብሮሹር እንዲያመጣ ንገረው። ከዚያም ገጽ 24 እና 25ን አውጥተህ ከአንቀጽ 12-14 ባሉት ሐሳቦች ላይ ተወያዩ። መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንዲጀምር ጠይቀው፤ ወይም ከአንቀጽ 15-16 ባለው ላይ እንድትወያዩ ሌላ ቀጠሮ ያዝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ