ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ፤ ሐምሌ እና ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ነቅተህ ጠብቅ!
◼ የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ የተባለው መጽሐፍ አንድ ቅጂ በመንግሥት አዳራሹ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ሊቀመጥ ይገባል። የመንግሥት አዳራሽ ቤተ መጻሕፍትን በተመለከተ በየካቲት 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 9 እና በሚያዝያ 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ካለው የጥያቄ ሣጥን ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
◼ የጉባኤው ጸሐፊ ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች የቀረበ መጠይቅ (S-82) የሚለውን ቅጽ የሞሉትን የተጠመቁ አስፋፊዎች ሁኔታ በሚመለከት የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ዴስክ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሰው ማድረግ አለበት። በፈቃደኛ ሠራተኛው ሁኔታ ላይ ለውጥ ካለ ማለትም ወደ ሌላ ጉባኤ ከሄደ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ወይም ሽማግሌ ሆኖ ከተሾመ ወዲያውኑ አዲስ ቅጽ ተሞልቶ መላክ ይኖርበታል። ፈቃደኛ ሠራተኛው የፖስታ ሣጥን ቁጥር ወይም ስልክ ቁጥር ከለወጠ ወይም በጉባኤ ውስጥ እንደ ቀድሞው በጥሩ አቋም ላይ የማይገኝ ከሆነ ሽማግሌዎች ወዲያውኑ ለቢሮው በደብዳቤ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። ተሞልቶ የተጠናቀቀው ቅጽ (S-82) በጉባኤው ፋይል ውስጥ መቀመጥ ይኖርበታል። ከዚያም የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን በሚጎበኝበት ጊዜ ያየዋል።
◼ ሕጋዊ ማኅበራትን የሚቆጣጠረው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በማኅበራችን መተዳደሪያ ደንብ ላይ አንዳንድ ለውጦች ተደርገዋል። ይህ ማስተካከያ ቲኦክራሲያዊ አደረጃጀታችንን የማይነካ ቢሆንም ከዚህ በኋላ ግን የማኅበሩ ስም በአማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ የይሖዋ ምሥክሮች (Yeyihowa Misikiroch) የሚል ይሆናል።
በመተዳደሪያ ደንባችን ውስጥ ከተካተቱት የማኅበሩ ዓላማዎች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል:- “ማኅበሩ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የይሖዋ ምሥክሮች የሚያራምዷቸውን ፍጹም ሃይማኖታዊ የሆኑ ዓላማዎች ለማከናወን ተቋቁሟል። ከቤት ወደ ቤትና ከቦታ ቦታ እየሄዱ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚመራውን የአምላክ ‘መንግሥት ምሥራች’ በመስበክ ስለ ይሖዋ አምላክ ስም፣ ስለ ቃሉ እና ስለ ሉዓላዊነቱ መመሥከር፤ ይህንንም ዓላማ ለማከናወን በቃል፣ በጽሑፍና የማኅበሩን ሃይማኖታዊ ዓላማ ለማራመድ በሚረዳ በማናቸውም ሕጋዊ ዘዴ በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች ማሰራጨት ያጠቃልላል፤ (ማቴዎስ 24:14፤ 28:19, 20፤ ሥራ 20:20)።”
ከዚህ በኋላ በምንልካቸው ደብዳቤዎች አናት ላይ በሚገኘው የድርጅቱ አድራሻና ማህተም ላይ ለውጥ ይደረጋል። ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ሕጋዊ ሰነዶቻችን ላይ የምንጠቀመው የይሖዋ ምሥክሮች የሚለውን ስም ይሆናል። ከዚህ በኋላ በባንክ ገንዘብ ስትልኩም ሆነ በፖስታ ቤት የአደራ ደብዳቤ ስትልኩ የምትጠቀሙት በዚህ ስም ይሆናል። ከዚህ ውጭ ግን በፖስታ አድራሻችንም ሆነ በባንክ የሂሳብ ቁጥራችን ላይ የተደረገ ለውጥ የለም። (ሕጋዊ ማኅበራትን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የጥር 15, 2001 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 28-31ን ተመልከቱ።)