ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 27, 2005 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 2 እስከ ሰኔ 27, 2005 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አነጻጻሪና ተለዋጭ ዘይቤዎች ጥሩ የማስተማሪያ መንገዶች ናቸው የምንለው ለምንድን ነው? (ዘፍ. 22:17፤ መዝ. 1:3፤ ያዕ. 3:6) [be ገጽ 240 አን. 2-4፣ ሣጥኑ]
2. በጣም ጠቃሚ ትምህርት የሚያስተላልፉ ምሳሌዎችን ከየት ማግኘት እንችላለን? ይሁን እንጂ በዚህ ረገድ ምን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል? [be ገጽ 242 አን. 1-2]
3. ጥሩ ውጤት ሊያስገኙ የሚችሉ ምሳሌዎችን በምንመርጥበት ጊዜ ምን ማስታወስ ይገባናል? [be ገጽ 244 አን. 1-2]
4. ስናስተምር፣ የሚታዩ ነገሮችን ተጠቅመን ማስረዳታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይሖዋ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ያስተማረው እንዴት ነው? [be ገጽ 247 አን. 1-2፣ ሣጥኑ]
5. በመስክ አገልግሎት ላይ፣ የሚታዩ ነገሮችን ተጠቅመን ማስተማር የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 248 አን. 1 እስከ ገጽ 249 አን. 2]
ክፍል ቁጥር 1
6. በአምላክ ቃል ውስጥ ልጆችን ስለ ማስተማር ምን መመሪያ ተሰጥቷል? [w03 3/15 ገጽ 12 አን. 2፤ ገጽ 14 አን. 4]
7. ይሖዋ ለወጣቱ ዳዊት አሳቢነት ያሳየው እንዴት ነበር? ዳዊትስ ከይሖዋ ጋር ለነበረው ዝምድና ያለውን ስሜት የገለጸው እንዴት ነው? [w03 4/15 ገጽ 29 አን. 3፤ ገጽ 30 አን. 3]
8. ይሖዋ አቤል ባቀረበው መሥዋዕት የተደሰተው ለምንድን ነው? ይህስ ለእኛ ምን ያረጋግጥልናል? (ዘፍ. 4:4) [w03 5/1 ገጽ 28 አን. 4 እስከ ገጽ 29 አን. 1]
9. በምሳሌ 3:11 ላይ እንዳንንቀው ጥብቅ ማሳሰቢያ የተሰጠን ‘የእግዚአብሔር ተግሣጽ’ ምንድን ነው? [w03 10/1 ገጽ 20 አን. 2-4]
10. በ1 ጢሞቴዎስ 6:6-8 ላይ የተጠቀሰው ያለኝ ይበቃኛል የሚለው አስተሳሰብ ምን ማለት ነው? [w03 6/1 ገጽ 9 አን. 1-2፤ ገጽ 10 አን. 1]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ዮናታንንና ዳዊትን ያስተሳሰረው ፍቅር ለምን ነገር ጥላ ነው? (2 ሳሙ. 1:26) [w89 1/1 ገጽ 26 አን. 13]
12. ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ ካደረገው የመጀመሪያ ሙከራ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (2 ሳሙ. 6:2-9)
13. ዘዳግም 24:16 እና ሕዝቅኤል 18:20 ላይ አባት በሠራው ስህተት ምክንያት ልጅ እንደማይሞት እየተናገረ ዳዊትና ቤርሳቤህ በፈጸሙት ኃጢአት ሕፃኑ የሞተው ለምንድን ነው? (2 ሳሙ. 12:14፤ 22:31)
14. ሲባ ስለ ሜምፊቦስቴ የተናገረው ነገር ሐሰት መሆኑን እንዴት ማወቅ እንችላለን? (2 ሳሙ. 16:1-4)
15. ሜምፊቦስቴ፣ በእርሱና በሲባ መካከል የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ የነበረው አመለካከት ለእኛ ግሩም ምሳሌ የሚሆነን እንዴት ነው? (2 ሳሙ. 19:24-30)