መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“መጽሐፍ ቅዱስና ሳይንስ እርስ በርስ ይጋጫሉ ሲባል ሰምተው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት በሳይንስና በሃይማኖት መካከል ስለነበረው ግጭት ይዘግባል። በሌላ በኩል ደግሞ እውነተኛ ሳይንስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚስማማ የሚያሳይ ማስረጃም ያቀርባል።” ገጽ 6ና 7ን አሳየው። ከዚያም መክብብ 1:7ን አንብብለት።
ንቁ! ሚያዝያ 2005
“በዛሬው ጊዜ ከሚያጋጥሙን ከበድ ያሉ ችግሮች መካከል አንዱ ውጥረት ነው ቢባል አይስማሙም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በዚህ ዘመን እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ እንደሚኖር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አስቀድሞ የተነገረ ሲሆን ይህም በትክክል እየተፈጸመ ነው። [2 ጢሞቴዎስ 3:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት እርስዎም ሆኑ ቤተሰብዎ ውጥረትን እንዴት መቋቋም እንደምትችሉ የሚገልጹ ጠቃሚ ሐሳቦች ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 15
“በዛሬው ጊዜ በጣም ብዙ መረጃ እየቀረበ መሆኑን ልብ ብለዋል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይሁን እንጂ በዮሐንስ 17:3 ላይ ከተገለጸው ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ እውቀት የለም። [ጥቅሱን አንብብለት።] ይህ መጽሔት ‘የዘላለም ሕይወት’ ሲባል ምን ማለት እንደሆነና እንዲህ ያለ ሕይወት ለማግኘት የሚያስችለውን እውቀት እንዴት ማግኘት እንደምንችል ያብራራል።”