የ2006 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያ
የ2006 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ክፍሎቹ የሚቀርቡባቸው ጽሑፎች፦ መጽሐፍ ቅዱስ [አ.መ.ት]፣ መጠበቂያ ግንብ [w-AM]፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም [be-AM]፣ “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው (2 ዜና መዋዕል—ኢሳይያስ) [bsi] እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rs-AM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ከተከፈተ በኋላ ከዚህ በታች በሰፈረው መመሪያ መሠረት ይከናወናል። እያንዳንዱ ክፍል ሲያበቃ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ቀጣዩን ክፍል ያስተዋውቃል።
የንግግር ባሕርይ፦ 5 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች፣ ረዳት ምክር ሰጪው ወይም ጥሩ ችሎታ ያለው ሌላ ሽማግሌ ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ በአንድ የንግግር ባሕርይ ላይ የተመሠረተ ክፍል ያቀርባል። (በቂ ሽማግሌዎች በሌሉባቸው ጉባኤዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያላቸው የጉባኤ አገልጋዮች ይህን ክፍል ሊያቀርቡ ይችላሉ።)
ክፍል ቁ. 1፦ 10 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ብቃት ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም በተባለው መጽሐፍ ወይም “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው በተባለው ብሮሹር ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ለአሥር ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር የሚቀርብ ሲሆን የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። ዓላማው በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር ለጉባኤው ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ ማጉላት እንጂ የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ አይደለም። በፕሮግራሙ ላይ የተሰጠውን ጭብጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን ንግግር እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች ክፍላቸውን በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አቅርበው መጨረስ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይችላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 10 ደቂቃ። በመጀመሪያዎቹ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር እያዛመደ ያቀርበዋል። ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርበው ወንድም ለሳምንቱ ከተመደበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ በፈለገው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ሐሳብ መስጠት ይችላል። ክፍሉ ለሳምንቱ የተመደቡትን ምዕራፎች በመከለስ ብቻ መቅረብ አይኖርበትም። ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት እንደሚጠቅም እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ተናጋሪው ለእርሱ የተመደበለትን አምስት ደቂቃ ብቻ በመጠቀም አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አምስት ደቂቃ ላለመንካት መጠንቀቅ ይኖርበታል። ቀጥሎ አድማጮች ከሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ልባቸውን የነካውንና ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን ሐሳብ በአጭሩ (በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ) እንዲናገሩ ይጋብዛል። ከዚያም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በሁለተኛው አዳራሽ ውስጥ ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች መሄድ እንደሚችሉ ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ 4 ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ የሚቀርብ። ይህን ክፍል አንድ ወንድም በንባብ ያቀርበዋል። ተማሪው መግቢያ እና መደምደሚያ ማዘጋጀት ሳያስፈልገው ክፍሉን በንባብ ብቻ ያቀርበዋል። ከመዝሙር መጽሐፍ የተወሰደ ክፍል ሲያቀርብ መዝሙሩ አናት ላይ የሰፈረውን ሐሳብ ማንበብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዎቹ ክፍሉን በሚገባ ተረድተው፣ በቅልጥፍና፣ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ በማጥበቅ፣ ድምፅን በመለዋወጥ፣ በተገቢው ቦታ ቆም በማለትና የራሳቸውን ተፈጥሯዊ አነጋገር በመጠቀም እንዲያነብቡ ለመርዳት ጥረት ያደርጋል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። ይህን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡ ተማሪዎች በአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ ከተዘረዘሩት መቼቶች መካከል አንዱ ይመደብላቸዋል አሊያም ራሳቸው እንዲመርጡ ይደረጋል። ተማሪዋ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኘውን ጭብጥ መጠቀምና ክፍሉን ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል በሚስማማ መንገድ ማቅረብ ይኖርባታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪዋ በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ማሰባሰብ ይኖርባታል። አዳዲስ ተማሪዎች ጭብጡ ብቻ የተሰጠባቸውን ክፍሎች ማቅረብ አይኖርባቸውም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ እንዴት እንደምታዳብር እንዲሁም የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉምና የክፍሉን ዋና ዋና ነጥቦች እንድትገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። ተማሪው የተሰጠውን ጭብጥ ማዳበር ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪው በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ያሰባስባል። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ አድማጮቹን ግምት ውስጥ በማስገባት በንግግር መልክ ያቀርበዋል። ሆኖም ክፍሉን አንዲት እህት የምታቀርበው ከሆነ ለክፍል ቁጥር 3 በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተገቢ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ክፍል ቁጥር 4ን ለአንድ ወንድም ሊሰጥ ይችላል። የኮከብ ምልክት ያለባቸው ክፍሎች በንግግር መልክ መቅረብ ያለባቸው ስለሆኑ ለወንድሞች ብቻ መሰጠት ይኖርባቸዋል።
ጊዜ መጠበቅ፦ ክፍል የሚያቀርቡትም ሆኑ ምክር ሰጪው የተመደበላቸውን ጊዜ ማሳለፍ አይኖርባቸውም። ከቁጥር 2 እስከ 4 ያሉትን ክፍሎች የሚያቀርቡት ወንድሞች የተመደበላቸው ጊዜ ሲሞላ በዘዴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለ ንግግር ባሕርይ የሚናገረው የመክፈቻ ንግግር፣ ክፍል ቁጥር 1 ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርቡ ወንድሞች ሰዓት ካሳለፉ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይገባል። ሁሉም ሰዓታቸውን በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ጸሎትንና መዝሙርን ሳይጨምር ጠቅላላው ፕሮግራም 45 ደቂቃ ይፈጃል።
ምክር፦ 1 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ክፍል ቁ. 2፣ ቁ. 3 እና ቁ. 4 ከቀረቡ በኋላ የንግግሮቹን ገንቢ ጎኖች አንስቶ ለማመስገን ከአንድ ደቂቃ የበለጠ ጊዜ መውሰድ አይኖርበትም። ዓላማው “ጥሩ ነው” ብሎ ለማለፍ ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ የተማሪው አቀራረብ ጥሩ የሆነበትን ምክንያት ለይቶ መጥቀስ ያስፈልገዋል። የእያንዳንዱን ተማሪ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከስብሰባው በኋላ ወይም በሌላ ጊዜ ገንቢ የሆነ ተጨማሪ ምክር በግል መስጠት ይችላል።
ረዳት ምክር ሰጪ፦ የሽማግሌዎች አካል ከትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተጨማሪ ረዳት ምክር ሰጪ ሆኖ የሚያገለግል ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ሊመርጥ ይችላል። በጉባኤው ውስጥ በርካታ ሽማግሌዎች ካሉ በየዓመቱ ብቃት ያላቸው ሽማግሌዎች እየተቀያየሩ ይህን ኃላፊነት ሊይዙ ይችላሉ። የዚህ ወንድም ኃላፊነት ንግግር ቁጥር 1ን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ለሚያቀርቡ ወንድሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግል ምክር መስጠት ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እነዚህን ክፍሎች የሚያቀርቡ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ንግግራቸውን ባቀረቡ ቁጥር ምክር ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም።
ምክር መስጫ ቅጽ፦ በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
የቃል ክለሳ፦ 30 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በየሁለት ወሩ የሚደረገውን የቃል ክለሳ ይመራል። ክለሳው የሚደረገው የንግግር ባሕርይና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረቡ በኋላ ይሆናል። ክለሳው የሚሸፍነው፣ የክለሳውን ሳምንት ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የቀረቡትን ትምህርቶች ይሆናል። የቃል ክለሳ በሚቀርብበት ሳምንት ጉባኤያችሁ የወረዳ ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነ ክለሳው (እና በሳምንታዊ ፕሮግራሙ ላይ ያሉት ሌሎች ክፍሎች) አንድ ሳምንት ዘግይቶ የሚቀርብ ሲሆን የቀጣዩ ሳምንት ፕሮግራም ደግሞ አንድ ሳምንት አስቀድሞ መቅረብ አለበት። የቃል ክለሳውና የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት በሚገጣጠሙበት ጊዜ በፕሮግራሙ ላይ የሰፈረው መዝሙር፣ የንግግር ባሕርይና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች መቅረብ አለባቸው። የማስተማሪያ ንግግሩ (ከንግግር ባሕርይ ቀጥሎ ይቀርባል) ለሚቀጥለው ሳምንት ከወጣው ፕሮግራም ላይ ይወሰዳል። በቀጣዩ ሳምንት፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ የወጣው የንግግር ባሕርይ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ የቃል ክለሳው ይቀጥላል።
ፕሮግራም
ጥር 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 29-32መዝ. 34 (77)
የንግግር ባሕርይ፦ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ሙሉ ጥቅም አግኝ (be ገጽ 5 አን. 1–ገጽ 8 አን. 1)
ቁ. 1፦ የአምላክን ቃል በማንበብ ተደሰት (be ገጽ 9 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 30:1-12
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ጸያፍ ንግግርን ማስወገድ ያለባቸው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ኃጢአት ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና የሚነካው እንዴት ነው? (rs ገጽ 373 አን. 1-4)
ጥር 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 33-36መዝ. 61 (144)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥርት ያለ ንባብ (be ገጽ 83 አን. 1–ገጽ 84 አን. 1)
ቁ. 1፦ 2 ዜና መዋዕል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi አን. 34-36)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 34:1-11
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነፍስ ምን ይላል? (rs ገጽ 374 አን. 1–ገጽ 375 አን. 1)
ቁ. 4፦ የመጽሐፍ ቅዱስን የሥነ ምግባር መሥፈርት በመከተልህ ፈጽሞ ልታፍር አይገባም
ጥር 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕዝራ 1-5መዝ. 87 (195)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥርት አድርጎ ማንበብ የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 84 አን. 2–ገጽ 85 አን. 3)
ቁ. 1፦ የዕዝራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi አን. 1-7)
ቁ. 2፦ ዕዝራ 1:1-11
ቁ. 3፦ ንጹሕ ሕሊና የሚያስገኛቸው ጥቅሞች
ቁ. 4፦ እንስሳት ነፍሳት ናቸው (rs ገጽ 375 አን. 2–ገጽ 376 አን. 2)
ጥር 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕዝራ 6-10መዝ. 45 (106)
የንግግር ባሕርይ፦ ቃላትን አጥርቶ መናገር (be ገጽ 86 አን. 1-6)
ቁ. 1፦ ዕዝራ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi አን. 14-18)
ቁ. 2፦ ዕዝራ 6:1-12
ቁ. 3፦ ሰው ሲሞት ነፍሱም ሆነ መንፈሱ በሕይወት አይቀጥልም (rs ገጽ 376 አን. 3–ገጽ 378 አን. 4)
ቁ. 4፦ a አምላክ ስለ ጋብቻ ምን አመለካከት አለው?
ጥር 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህምያ 1-4መዝ. 94 (212)
የንግግር ባሕርይ፦ አጥርቶ መናገር የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 87 አን. 1–ገጽ 88 አን. 3)
ቁ. 1፦ የነህምያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi አን. 1-5)
ቁ. 2፦ ነህምያ 2:1-10
ቁ. 3፦ ከሁሉ የላቀው መተማመኛ
ቁ. 4፦ መንፈስ ቅዱስ ምንድን ነው? (rs ገጽ 379 አን. 1–3)
የካ. 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህምያ 5-8መዝ. 18 (42)
የንግግር ባሕርይ፦ የቃላት ትክክለኛ አጠራር—ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ጉዳይ (be ገጽ 89 አን. 1–ገጽ 90 አን. 2)
ቁ. 1፦ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብብ (be ገጽ 10 አን. 1–ገጽ 12 አን. 3)
ቁ. 2፦ ነህምያ 5:1-13
ቁ. 3፦ አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ (rs ገጽ 380 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ “ልብህን ጠብቅ” (ምሳሌ 4:23)
የካ. 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህምያ 9-11መዝ. 71 (163)
የንግግር ባሕርይ፦ የቃላትን ትክክለኛ አጠራር ማሻሻል የሚቻልባቸው መንገዶች (be ገጽ 90 አን. 3–ገጽ 91 አን. 4)
ቁ. 1፦ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን መማር (w04 1/1 ገጽ 6 አን. 8–ገጽ 7 አን. 5)
ቁ. 2፦ ነህምያ 10:28-37
ቁ. 3፦ ይሖዋ እንደሚወደን የሚያሳይ ማስረጃ
ቁ. 4፦ ሰው ከሞት በኋላ በሕይወት የሚቀጥል መንፈስ የለውም (rs ገጽ 381 አን. 4–ገጽ 382 አን. 1)
የካ. 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህምያ 12-13መዝ. 76 (172)
የንግግር ባሕርይ፦ ቅልጥፍና (be ገጽ 93 አን. 1–ገጽ 94 አን. 3)
ቁ. 1፦ ነህምያ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi አን. 16-19)
ቁ. 2፦ ነህምያ 13:1-14
ቁ. 3፦ ከሞቱ ሰዎች ጋር መነጋገር የማይቻለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 383 አን. 1-5)
ቁ. 4፦ b ዓመጽ የሚንጸባረቅባቸው የቪዲዮ ጨዋታዎች ለክርስቲያኖች አይሆኑም
የካ. 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ አስቴር 1-5መዝ. 96 (215)
የንግግር ባሕርይ፦ ቅልጥፍናን ማሻሻል የሚቻልበት መንገድ (be ገጽ 94 አን. 4–ገጽ 96 አን. 2, በገጽ 95 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ሳይጨምር)
የቃል ክለሳ
መጋ. 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ አስቴር 6-10መዝ. 56 (135)
የንግግር ባሕርይ፦ የመንተባተብን ችግር መቋቋም (be ገጽ 95 ሣጥኑ)
ቁ. 1፦ የአስቴር መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi አን. 1-6, 16-18)
ቁ. 2፦ አስቴር 6:1-10
ቁ. 3፦ የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል
ቁ. 4፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከማንኛውም ዓይነት መናፍስታዊ ተግባር የሚርቁት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 384 አን. 1–ገጽ 385 አን. 6)
መጋ. 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 1-5መዝ. 69 (160)
የንግግር ባሕርይ፦ ሐሳቡን በትክክል ለማስተላለፍና የሐሳብ ለውጥ ለማድረግ ቆም ማለት (be ገጽ 97 አን. 1–ገጽ 98 አን. 6)
ቁ. 1፦ የኢዮብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi አን. 1-6)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 2:1-13
ቁ. 3፦ ስለ አጋንንታዊ ኃይሎች ለማወቅ አትጓጉ (rs ገጽ 385 አን. 7–ገጽ 387 አን. 1)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከአጉረምራሚነት የሚርቁት ለምንድን ነው?
መጋ. 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 6-10መዝ. 43 (98)
የንግግር ባሕርይ፦ ለማጥበቅ እንዲሁም የሌሎችን ሐሳብ ለመስማት ቆም ማለት (be ገጽ 99 አን. 1–ገጽ 100 አን. 3)
ቁ. 1፦ መንፈሳዊ እሴቶች ያላቸው ብልጫ (w04 10/15 ገጽ 4 አን. 2–ገጽ 5 አን. 3)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 7:1-21
ቁ. 3፦ ልበ ንጹሕ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?
ቁ. 4፦ ከመናፍስት ተጽዕኖ መላቀቅ የሚቻለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 387 አን. 2-6)
መጋ. 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 11-15መዝ. 4 (8)
የንግግር ባሕርይ፦ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ ማጥበቅ (be ገጽ 101 አን. 1–ገጽ 102 አን. 3)
ቁ. 1፦ “እንዴት እንደምታዳምጡ በጥንቃቄ አስቡ” (be ገጽ 13 አን. 1–ገጽ 14 አን. 4)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 12:1-25
ቁ. 3፦ በራስ የመመራት መንፈስ እንዳይጠናወታችሁ ተጠንቀቁ (rs ገጽ 388 አን. 1–ገጽ 389 አን. 1)
ቁ. 4፦ አገልግሎት ደስታ የሚያስገኝልን ለምንድን ነው?
ሚያ. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 16-20መዝ. 24 (50)
የንግግር ባሕርይ፦ ቁልፍ ቃላትን በማጥበቅ ረገድ ማሻሻል (be ገጽ 102 አን. 4–ገጽ 104 አን. 3)
ቁ. 1፦ ለአምላክ ያለንን ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (w04 3/1 ገጽ 19-21)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 16:1-22
ቁ. 3፦ ይሖዋ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ ሰዎችን ወደ ራሱ የሚስበው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ c ኩራትና የዓመጸኝነት ዝንባሌ የሚያስከትሉት አደጋ (rs ገጽ 389 አን. 2-3)
ሚያ. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 21-27መዝ. 53 (130)
የንግግር ባሕርይ፦ ዋና ዋና ነጥቦችን አጽንዖት ሰጥቶ ማንበብ (be ገጽ 105 አን. 1–ገጽ 106 አን. 1)
ቁ. 1፦ መንፈሳዊ እሴቶች በረከት ያስገኛሉ (w04 10/15 ገጽ 5 አን. 4–ገጽ 7 አን. 2)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 24:1-20
ቁ. 3፦ ይሖዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ይሰጣል
ቁ. 4፦ d የሥጋ ፍላጎቶች እንዳያሸንፉን መጠንቀቅ (rs ገጽ 390 አን. 1)
ሚያ. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 28-32መዝ. 84 (190)
የንግግር ባሕርይ፦ ለአድማጮች ተስማሚ የሆነ የድምፅ መጠን (be ገጽ 107 አን. 1–ገጽ 108 አን. 4)
ቁ. 1፦ በጉባኤና በትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ማዳመጥ (be ገጽ 15 አን. 1–ገጽ 16 አን. 5)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 29:1-25
ቁ. 3፦ የዓይን አምሮት እንዲቆጣጠራችሁ አትፍቀዱ (rs ገጽ 390 አን. 2-3)
ቁ. 4፦ ሕዝቡ በኢየሱስ ትምህርት የተገረሙት ለምን ነበር?
ሚያ. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 33-37መዝ. 49 (114)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅህን መጠን ማሻሻል የምትችለው እንዴት ነው? (be ገጽ 108 አን. 5–ገጽ 110 አን. 2)
የቃል ክለሳ
ግን. 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዮብ 38-42መዝ. 35 (79)
የንግግር ባሕርይ፦ ድምፅን መለዋወጥ—የድምፅህን መጠን እንደ ሁኔታው አስተካክል (be ገጽ 111 አን. 1–ገጽ 112 አን. 2)
ቁ. 1፦ ኢዮብ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi አን. 39-43)
ቁ. 2፦ ኢዮብ 38:1-24
ቁ. 3፦ ኢሳይያስ 60:22 በዛሬው ጊዜ እየተፈጸመ ያለው አንዴት ነው?
ቁ. 4፦ e ቁጣና ስድብ የሥጋ ሥራዎች ናቸው (rs ገጽ 391 አን. 1)
ግን. 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 1-10መዝ. 74 (168)
የንግግር ባሕርይ፦ ድምፅን መለዋወጥ—ፍጥነትህን መለዋወጥ (be ገጽ 112 አን. 3–ገጽ 113 አን. 1)
ቁ. 1፦ የመዝሙር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 1 (bsi አን. 1-5)
ቁ. 2፦ መዝሙር 4:1 እስከ 5:12
ቁ. 3፦ በሰው ሳይሆን በአምላክ ታመን (rs ገጽ 391 አን. 2-3)
ቁ. 4፦ የጤናማውን ትምህርት ምሳሌ መያዝ
ግን. 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 11-18መዝ. 97 (217)
የንግግር ባሕርይ፦ ድምፅን መለዋወጥ—የድምፅህን ቃና መለዋወጥ (be ገጽ 113 አን. 2–ገጽ 114 አን. 2)
ቁ. 1፦ የመዝሙር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 2 (bsi አን. 6-11)
ቁ. 2፦ መዝሙር 14:1 እስከ 16:6
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች የዓለም ክፍል የማይሆኑት በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ቁ. 4፦ በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሰው መከራ ተጠያቂው ማን ነው? (rs ገጽ 392 አን. 1-2)
ግን. 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 19-25መዝ. 2 (4)
የንግግር ባሕርይ፦ በስሜት ተናገር (be ገጽ 115 አን. 1–ገጽ 116 አን. 4)
ቁ. 1፦ መልካም ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል (w04 7/15 ገጽ 27 አን. 4–ገጽ 28 አን. 4)
ቁ. 2፦ መዝሙር 22:1-22
ቁ. 3፦ መከራ የመጣው እንዴት ነው? (rs ገጽ 392 አን. 3–ገጽ 393 አን. 1)
ቁ. 4፦ f የአምላክ ማሳሰቢያዎች ምንድን ናቸው? ማሳሰቢያዎቹን መታዘዝ የሚኖርብንስ ለምንድን ነው?
ግን. 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 26-33መዝ. 21 (46)
የንግግር ባሕርይ፦ ለትምህርቱ የሚስማማ ግለት (be ገጽ 116 አን. 5–ገጽ 117 አን. 3)
ቁ. 1፦ የማስታወስ ችሎታህን ማሻሻል ትችላለህ (be ገጽ 17 አን. 1–ገጽ 18 አን. 5)
ቁ. 2፦ መዝሙር 30:1 እስከ 31:8
ቁ. 3፦ እውነት አንድን ሰው ነፃ የሚያወጣው በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ቁ. 4፦ ከሥቃይ መገላገል የምንችለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 393 አን. 2-3)
ሰኔ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 34-37መዝ. 94 (212)
የንግግር ባሕርይ፦ ወዳጃዊ ስሜት ማሳየት (be ገጽ 118 አን. 1–ገጽ 119 አን. 5)
ቁ. 1፦ ጸሎት ያለው ኃይል (w04 8/15 ገጽ 18 አን. 6–ገጽ 19 አን. 10)
ቁ. 2፦ መዝሙር 34:1-22
ቁ. 3፦ የፍቅር አምላክ ይህን ለሚያህል ጊዜ መከራ እንዲቀጥል የፈቀደው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 394 አን. 2)
ቁ. 4፦ ልንርቃቸው የሚገቡ የጣዖት አምልኮ ገጽታዎች የትኞቹ ናቸው?
ሰኔ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 38-44መዝ. 66 (155)
የንግግር ባሕርይ፦ ስሜትን ማንጸባረቅ (be ገጽ 119 አን. 6–ገጽ 120 አን. 5)
ቁ. 1፦ የአምላክ መንፈስ እንድናስታውስ በመርዳት ረገድ የሚጫወተው ሚና (be ገጽ 19 አን. 1–ገጽ 20 አን. 2)
ቁ. 2፦ መዝሙር 40:1-17
ቁ. 3፦ እውነተኛ ሳይንስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አይጋጭም
ቁ. 4፦ አምላክ በአገልጋዮቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ሁሉ ያስወግዳል (rs ገጽ 394 አን. 3–ገጽ 395 አን. 3)
ሰኔ 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 45-51መዝ. 23 (48)
የንግግር ባሕርይ፦ የአካላዊ መግለጫዎች አስፈላጊነት (be ገጽ 121 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ኢየሱስ የመጣው መቼ ነው? (w04 3/1 ገጽ 16፣ ሣጥን)
ቁ. 2፦ መዝሙር 46:1 እስከ 47:9
ቁ. 3፦ አምላክ የአዳምን ኃጢአት በይቅርታ ያላለፈው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 395 አን. 4-5)
ቁ. 4፦ አንድ ክርስቲያን እየደከመውም ብርቱ መሆን የሚችለው እንዴት ነው? (2 ቆሮ. 12:10)
ሰኔ 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 52-59መዝ. 58 (138)
የንግግር ባሕርይ፦ በአካላዊ እንቅስቃሴና ፊት ላይ በሚነበብ ስሜት ሐሳብን መግለጽ (be ገጽ 121 አን. 5–ገጽ 123 አን. 2)
የቃል ክለሳ
ሐምሌ 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 60-68መዝ. 20 (45)
የንግግር ባሕርይ፦ በአገልግሎት ላይ አድማጮችን ማየት (be ገጽ 124 አን. 1–ገጽ 125 አን. 4)
ቁ. 1፦ የይሖዋ ትሕትና ለእኛ ምን ትርጉም አለው? (w04 11/1 ገጽ 29-30)
ቁ. 2፦ መዝሙር 60:1 እስከ 61:8
ቁ. 3፦ በክርስቲያናዊ እንቅስቃሴዎች መካፈል የአምላክን ሕግጋት ለመጣስ ሰበብ ይሆነናል?
ቁ. 4፦ አካላዊና አእምሯዊ እክል እንዲኖር የሚያደርገው አምላክ አይደለም (rs ገጽ 395 አን. 6–ገጽ 396 አን. 2)
ሐምሌ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 69-73መዝ. 97 (217)
የንግግር ባሕርይ፦ ንግግር ስታቀርብ አድማጮችን ማየት (be ገጽ 125 አን. 5–ገጽ 127 አን. 1)
ቁ. 1፦ ለማንበብ መትጋት የሚያስፈልግህ ለምንድን ነው? (be ገጽ 21 አን. 1–ገጽ 23 አን. 3)
ቁ. 2፦ መዝሙር 71:1-18
ቁ. 3፦ ይሖዋ በፍቅር ተነሣሥቶ ልጆች የክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ አድርጓል (rs ገጽ 396 አን. 3)
ቁ. 4፦ g ክርስቲያኖች አድሎአዊ መሆን የሌለባቸው ለምንድን ነው?
ሐምሌ 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 74-78መዝ. 95 (213)
የንግግር ባሕርይ፦ በመስክ አገልግሎት ላይ የራስን ተፈጥሯዊ አነጋገር መጠቀም (be ገጽ 128 አን. 1–ገጽ 129 አን. 1)
ቁ. 1፦ ስታነብብ ተገቢው የልብ ዝንባሌ ይኑርህ (be ገጽ 23 አን. 4-ገጽ 26 አን. 4)
ቁ. 2፦ መዝሙር 75:1 እስከ 76:12
ቁ. 3፦ ይሖዋን መፈለግ ምን ነገሮችን ይጨምራል? (ሶፎ. 2:3)
ቁ. 4፦ አምላክ በተፈጥሮ አደጋዎች በመጠቀም ሰዎችን አይቀጣም (rs ገጽ 396 አን. 4–ገጽ 397 አን. 2)
ሐምሌ 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 79-86መዝ. 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ ከመድረክ ስትናገር የራስህን ተፈጥሯዊ አነጋገር መጠቀም (be ገጽ 129 አን. 2–ገጽ 130 አን. 1)
ቁ. 1፦ ‘የቅኖች ድንኳን ይስፋፋል’ (w04 11/15 ገጽ 26 አን. 1–ገጽ 28 አን. 1)
ቁ. 2፦ መዝሙር 82:1 እስከ 83:18
ቁ. 3፦ መከራና ሥቃይ የአምላክ ቁጣ ምልክት ተደርጎ መታየት የለበትም (rs ገጽ 397 አን. 3-4)
ቁ. 4፦ ፍጽምና የጎደላቸው ሰዎች በእርግጥ አምላክን ማስደሰት ይችላሉ?
ሐምሌ 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 87-91መዝ. 27 (57)
የንግግር ባሕርይ፦ ለሌሎች ስታነብብ የራስህን ተፈጥሯዊ አነጋገር መጠቀም (be ገጽ 130 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ ‘ዕውቀት በቀላሉ ስትገኝና’ ጥበብ ሲመራን (w04 11/15 ገጽ 28 አን. 2–ገጽ 29 አን. 7)
ቁ. 2፦ መዝሙር 89:1-21
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የአምልኳችን ክፍል ነው
ቁ. 4፦ ቁሳዊ ብልጽግና ከአምላክ የተገኘ በረከት ተደርጎ መቆጠር የለበትም (rs ገጽ 398 አን. 1-2)
ነሐሴ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 92-101መዝ. 84 (190)
የንግግር ባሕርይ፦ ንጹሕ መሆን መልእክቱን ያስከብረዋል (be ገጽ 131 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የአጠናን ዘዴ (be ገጽ 27 አን. 1–ገጽ 31 አን. 2)
ቁ. 2፦ መዝሙር 92:1 እስከ 93:5
ቁ. 3፦ አንድ ሰው በልሳን መናገሩ የአምላክ መንፈስ እንዳለው ያረጋግጣል? (rs ገጽ 399 አን. 1–ገጽ 400 አን. 1)
ቁ. 4፦ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናን የመጠበቅ አስፈላጊነት
ነሐሴ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 102-105መዝ. 57 (136)
የንግግር ባሕርይ፦ ጨዋነትና ጤናማ አስተሳሰብ በአለባበስና በአጋጌጥ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ (be ገጽ 131 አን. 4–ገጽ 132 አን. 3)
ቁ. 1፦ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው!” (w04 11/15 ገጽ 8-9)
ቁ. 2፦ መዝሙር 104:1-24
ቁ. 3፦ ነቅተን መጠበቅ ያለብን ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ በዛሬው ጊዜ ያለው በልሳን መናገር በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች ያደርጉት ከነበረው የተለየ የሆነው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 400 አን. 2-5)
ነሐሴ 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 106-109መዝ. 89 (201)
የንግግር ባሕርይ፦ ሥርዓታማ አለባበስ ያለው ጥቅም (be ገጽ 132 አን. 4–ገጽ 133 አን. 1)
ቁ. 1፦ ወጣቶች—እኩዮቻችሁን በጭፍን አትከተሉ (w04 10/15 ገጽ 22 አን. 4–ገጽ 24 አን. 5)
ቁ. 2፦ መዝሙር 107:20-43
ቁ. 3፦ የአምላክ ቃል፣ መንፈስ ቅዱስ አለን ለሚሉ ሰዎች ማስረጃ ለማቅረብ ይረዳናል (rs ገጽ 401 አን. 2-5)
ቁ. 4፦ አምላክን መምሰል የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ነሐሴ 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 110-118መዝ. 38 (85)
የንግግር ባሕርይ፦ ንጹሕና ሥርዓታማ አለባበስ ማሰናከያ እንዳንሆን ይጠብቀናል (be ገጽ 133 አን. 2-4)
የቃል ክለሳ
መስ. 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 119መዝ. 21 (46)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ አቋቋምና በሥርዓት የተያዙ ጽሑፎች (be ገጽ 134 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ጥናት በረከት ያስገኛል (be ገጽ 31 አን. 3–ገጽ 32 አን. 3)
ቁ. 2፦ መዝሙር 119:25-48
ቁ. 3፦ ለመንግሥት ባለ ሥልጣናት አክብሮት ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች ተለይተው የሚታወቁት በልሳናት በመናገር ችሎታቸው አይደለም (rs ገጽ 401 አን. 6–ገጽ 402 አን. 2)
መስ. 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 120-134መዝ. 95 (213)
የንግግር ባሕርይ፦ ንግግር ስትሰጥ የሚሰማህን ፍርሃት መቀነስ የሚቻልበት መንገድ (be ገጽ 135 አን. 1–ገጽ 137 አን. 2)
ቁ. 1፦ ምርምር ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 33 አን. 1-ገጽ 35 አን. 2)
ቁ. 2፦ መዝሙር 121:1 እስከ 123:4
ቁ. 3፦ በልሳናት የመናገር ስጦታ የቀጠለው እስከ መቼ ነበር? (rs ገጽ 402 አን. 3-4)
ቁ. 4፦ ግነት ምንድን ነው? ኢየሱስ የተጠቀመበትስ እንዴት ነው?
መስ. 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 135-141መዝ. 36 (81)
የንግግር ባሕርይ፦ ተረጋግቶ መናገር የሚቻልበት መንገድ (be ገጽ 137 አን. 3–ገጽ 138 አን. 3)
ቁ. 1፦ መዝሙር—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 1 (bsi አን. 23-27)
ቁ. 2፦ መዝሙር 136:1-26
ቁ. 3፦ የመታሰቢያው በዓል የሕብረት ማዕድ የሆነው በምን መንገድ ነው?
ቁ. 4፦ h የሥላሴ እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ አይደለም (rs ገጽ 404 አን. 1–ገጽ 410 አን. 3)
መስ. 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 142-150መዝ. 22 (47)
የንግግር ባሕርይ፦ ድምፅን ማጉላት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (be ገጽ 139 አን. 1–ገጽ 140 አን. 1)
ቁ. 1፦ መዝሙር—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 2 (bsi አን. 28-32)
ቁ. 2፦ መዝሙር 142:1 እስከ 143:12
ቁ. 3፦ i አንድ ሰው ‘በሥላሴ ታምናላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቅስ? (rs ገጽ 425 አን. 3–ገጽ 427 አን. 1)
ቁ. 4፦ ከራሳችን ይልቅ የሌሎችን ጥቅም ማስቀደም የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ጥቅ. 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 1-6መዝ. 85 (191)
የንግግር ባሕርይ፦ በማይክሮፎን ጥሩ አድርጎ መጠቀም (be ገጽ 140 አን. 2–ገጽ 142 አን. 1)
ቁ. 1፦ የምሳሌ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 1 (bsi አን. 1-5)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 5:1-23
ቁ. 3፦ ክፋት ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 427 አን. 2–ገጽ 428 አን. 1)
ቁ. 4፦ j የሐሰት ወሬ አታባዙ (2 ጢሞ. 4:4)
ጥቅ. 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 7-11መዝ. 79 (177)
የንግግር ባሕርይ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሞ መልስ መስጠት (be ገጽ 143 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የምሳሌ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ—ክፍል 2 (bsi አን. 6-11)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 7:1-27
ቁ. 3፦ ክርስቲያናዊ የገለልተኝነት አቋማችን ከወንድሞቻችን ጋር አንድነት እንዲኖረን አስተዋጽኦ ያደርጋል
ቁ. 4፦ አምላክ ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 428 አን. 2–ገጽ 429 አን. 2)
ጥቅ. 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 12-16መዝ. 80 (180)
የንግግር ባሕርይ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀማችንን ማሻሻል (be ገጽ 144 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ለምርምር የሚረዱ ሌሎች ጽሑፎችን መጠቀም (be ገጽ 35 አን. 3–ገጽ 38 አን. 4)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 14:1-21
ቁ. 3፦ አምላክ ክፋት እንዲኖር መፍቀዱ ጥቅም ያስገኘልን እንዴት ነው? (rs ገጽ 430 አን. 1-2)
ቁ. 4፦ በስብሰባዎች ላይ በትኩረት መከታተል እንድንችል ምን ይረዳናል?
ጥቅ. 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 17-21መዝ. 28 (58)
የንግግር ባሕርይ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ገልጠው እንዲከታተሉ ማበረታታት (be ገጽ 145-146)
ቁ. 1፦ ምሳሌ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 1 (bsi አን. 19-28)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 17:1-20
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ለአረጋውያን ያላቸው አመለካከት
ቁ. 4፦ k መጽሐፍ ቅዱስ ለሴቶች ምን አመለካከት አለው? (rs ገጽ 431 አን. 3–ገጽ 432 አን. 1)
ጥቅ. 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 22-26መዝ. 33 (72)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (be ገጽ 147 አን. 1–ገጽ 148 አን. 2)
የቃል ክለሳ
ኅዳር 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ምሳሌ 27-31መዝ. 9 (26)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ለማስተዋወቅ ተስማሚ የሆነ ሐሳብ መምረጥ (be ገጽ 148 አን. 3–ገጽ 149 አን. 2)
ቁ. 1፦ ምሳሌ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት—ክፍል 2 (bsi አን. 29-38)
ቁ. 2፦ ምሳሌ 28:1-18
ቁ. 3፦ የራስነትን ቦታ ለወንዶች መስጠት ሴቶችን ዝቅ ያደርጋቸዋል? (rs ገጽ 432 አን. 2-4)
ቁ. 4፦ በአገልግሎት ላይ የምናገኛቸውን ሰዎች ውጫዊ ሁኔታቸውን ተመልክተን መፍረድ የሌለብን ለምንድን ነው?
ኅዳር 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መክብብ 1-6መዝ. 15 (35)
የንግግር ባሕርይ፦ ተፈላጊውን ነጥብ ማጉላት ስሜቱን ማንጸባረቅንም ይጨምራል (be ገጽ 150 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የመክብብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi አን. 1-8)
ቁ. 2፦ መክብብ 5:1-15
ቁ. 3፦ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች የተሰወረው እንዴት ነው? (ማቴ. 11:25)
ቁ. 4፦ ሴቶች የጉባኤ አገልጋዮች መሆን ይገባቸዋል? (rs ገጽ 433 አን. 1-2)
ኅዳር 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መክብብ 7-12መዝ. 16 (37)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛዎቹን ቃላት ማጉላት (be ገጽ 150 አን. 3–ገጽ 151 አን. 2)
ቁ. 1፦ መክብብ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi አን. 15-19)
ቁ. 2፦ መክብብ 9:1-12
ቁ. 3፦ ክርስቲያን ሴቶች በአንዳንድ ወቅቶች ራሳቸውን የሚሸፍኑት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 433 አን. 3–ገጽ 434 አን. 1)
ቁ. 4፦ መቅናት ምን ስሕተት አለው?
ኅዳር 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማሕልየ መሓልይ 1-8መዝ. 74 (168)
የንግግር ባሕርይ፦ ለማጉላት የሚረዱ ዘዴዎች (be ገጽ 151 አን. 3–ገጽ 152 አን. 5)
ቁ. 1፦ የማሕልየ መሓልይ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi አን. 1-4, 16-18)
ቁ. 2፦ ማሕልየ መሓልይ 7:1 እስከ 8:4
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች አለባበሳቸው ሥርዓታማ፣ ንጹሕና ልከኛ ሊሆን የሚገባው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ሴቶች መኳኳያ መጠቀማቸው ወይም ጌጣጌጥ ማድረጋቸው ተገቢ ነው? (rs ገጽ 435 አን. 1-3)
ታኅ. 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 1-5መዝ. 35 (79)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ከነጥቡ ጋር ማገናዘብ (be ገጽ 153 አን. 1–ገጽ 154 አን. 2)
ቁ. 1፦ የኢሳይያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi አን. 1-8)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 3:1-15
ቁ. 3፦ ዓለም በእሳት ይጠፋ ይሆን? (rs ገጽ 436 አን. 1-2)
ቁ. 4፦ l ክርስቲያኖች ‘ለቁጣ የዘገዩ’ መሆን ያለባቸው ለምንድን ነው? (ያዕ. 1:19)
ታኅ. 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 6-10መዝ. 90 (204)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሱ ከነጥቡ ጋር ያለውን ዝምድና ግልጽ ማድረግ (be ገጽ 154 አን. 3–ገጽ 155 አን. 4)
ቁ. 1፦ አስተዋጽኦ ማዘጋጀት (be ገጽ 39-42)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 10:1-14
ቁ. 3፦ ይቅር ማለት መቻል በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ይህን ዓለም የሚገዛው ማን ነው? አምላክ ወይስ ሰይጣን? (rs ገጽ 436 አን. 3–ገጽ 437 አን. 2)
ታኅ. 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 11-16መዝ. 22 (47)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ተጠቅሞ ማስረዳት (be ገጽ 155 አን. 5–ገጽ 156 አን. 4)
ቁ. 1፦ ወጣቶች ሆይ፣ ልባችሁን በመጠበቅ ረገድ ወላጆቻችሁ እንዲረዷችሁ ፍቀዱላቸው (w04 10/15 ገጽ 20 አን. 1–ገጽ 22 አን. 3)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 11:1-12
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ስለ ዓለምና የዓለም ክፍል ስለሆኑት ሰዎች ምን አመለካከት አላቸው? (rs ገጽ 437 አን. 3–ገጽ 438 አን. 3)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች በአርማጌዶን ጦርነት አይካፈሉም
ታኅ. 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 17-23መዝ. 25 (53)
የንግግር ባሕርይ፦ የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ (be ገጽ 157 አን. 1–ገጽ 158 አን. 1)
የቃል ክለሳ
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
a ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
b ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
c ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
d ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
e ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
f ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
g ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
h ከተመደበልህ ክፍል ውስጥ ለጉባኤው ክልል ይበልጥ ተስማሚ የሆኑ ጥቂት ቁልፍ ነጥቦች ምረጥ።
i ከተመደበልህ ክፍል ውስጥ ለጉባኤው ክልል ይበልጥ ተስማሚ የሆኑ ጥቂት ቁልፍ ነጥቦች ምረጥ።
j ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
k ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
l ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።