መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሰዎች ከከንቱነት ስሜት ጋር ይታገላሉ። እነዚህን ሰዎች ለመርዳት ምን ማድረግ የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት እነዚህ ሰዎች እውነተኛ ደስታ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ይናገራል።” “መጽሐፍ ቅዱስ ደስታ እንድታገኝ ሊረዳህ ይችላል” በሚለው ርዕስ ሥር በደማቅ በተጻፉት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ ስጥ።
ንቁ! ነሐሴ 2005
“ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያዩት የሚፈቅዱትን ፊልም በመምረጥ ረገድ በጣም ጠንቃቆች ናቸው። ለቤተሰብዎ ተስማሚ የሆኑ ፊልሞችን መምረጡ ፈታኝ አልሆነብዎትም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኤፌሶን 4:17ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወላጆች ጥሩ መዝናኛዎችን በመምረጥ ረገድ ልጆቻቸውን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ይናገራል።”
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 15
“ብዙዎች የሚወዱትን ሰው በሞት ከተነጠቁ በኋላ ሰው ሲሞት ምን ይሆናል ብለው ይጠይቃሉ። ስለ ሞት ማወቅ የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ሙታን ስላሉበት ሁኔታ ምን እንደሚል ያብራራል። በተጨማሪም አምላክ በሞት የተለዩንን የምንወዳቸውን ሰዎች በትንሣኤ ለማስነሳት የገባውን ቃል ያብራራል።” ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብ።