መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
በመጽሔቱ ሽፋን ላይ ያለውን ጥያቄ አንብብለት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቀው:- “ይህ ርዕስ ስለ የትኛው ምልክት እንደሚናገር ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ማቴዎስ 24:3ን አንብብ።] ይህ መጠበቂያ ግንብ የዚህን ምልክት አምስት ጉልህ ገጽታዎች የሚመረምር ከመሆኑም በላይ ምልክቱን ማስተዋላችን አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ያብራራል።” በገጽ 6 ላይ ያለውን ሣጥን አሳየው።
ንቁ! ጥቅምት 2005
“ፉክክር በበዛበት በዛሬው የሥራ ዓለም ውስጥ ሥራ አጥነት ዋነኛ ችግር ሆኗል። ይህ መጽሔት ሥራ ለማግኘት የሚረዱ አምስት ቁልፍ ሐሳቦችን በዝርዝር አስቀምጧል። [“ሥራ ለማግኘት የሚረዱ አምስት ቁልፍ ሐሳቦች” በሚለው ርዕስ ሥር በጉልህ በተጻፉት ነጥቦች ላይ ሐሳብ ስጥ።] ከዚህም በላይ ከሥራ ላለመፈናቀል የሚረዱ ተግባራዊ ምክሮች ይዟል።” በገጽ 10 ላይ የተጠቀሰውን ምሳሌ 22:29ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15
“ብዙ ሰዎች የተሳካ ሕይወት ለመምራት ቁልፉ ትምህርት እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንድ ግለሰብ የተሻለ ሰው እንዲሆንና የሕይወትን ውጣ ውረድ እንዲቋቋም የሚያስችለው የትምህርት ዘርፍ ይኖራል ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ሮሜ 12:2ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ከሁሉም ከላቀው ትምህርት ጥቅም ማግኘት የምንችልበትን መንገድ ያብራራል።”