የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
መጋቢት 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 22 (47)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አስፋፊው የቤቱን ባለቤት በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኝ በመጋበዝ ሠርቶ ማሳያዎቹን ይደመድማል።
15 ደቂቃ:- “ሌሎች ሰዎች ከቤዛው እንዲጠቀሙ እርዷቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 206-208 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም እንዴት ሰዎችን ለመታሰቢያው በዓል መጋበዝ እንደምንችል በሰፊው የሚያብራራ ነው።
20 ደቂቃ:- የጌታ እራት—አምላክን የሚያስከብር በዓል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 206-208 ላይ ተመሥርቶ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ከአንድ ደቂቃ በሚያንሰው የመግቢያ ሐሳብ ውስጥ የመጀመሪያውን አንቀጽ በማንበብ የቤቱን ባለቤት ለመታሰቢያው በዓል እንዴት መጋበዝ እንደሚቻል አሳይ። ከዚያም አድማጮች ከዚህ በታች በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ፤ አንቀጾቹን ማንበብ አያስፈልግም። (አን. 2) ኢየሱስ የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያቋቋመው መቼ ነበር? (አን. 3) የጌታ እራት በዓል መከበር ያለበት በዓመት ስንት ጊዜ ነው? (አን. 4) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መታሰቢያው በዓል ምን ይላል? (አን. 5) ኢየሱስ ቂጣውን ቃል በቃል ወደ ሥጋው ወይኑን ደግሞ ወደ ደሙ እንዳልቀየረው እንዴት ማወቅ እንችላለን? (አን. 6) እርሾ የሌለበት ቂጣ ምንን ይወክላል? (አን. 7) ቀዩ ወይንስ የሚወክለው ምንን ነው? (አን. 8) ከቂጣውና ከወይኑ መካፈል የሚችሉት እነማን ብቻ ናቸው? (አን. 9) የመታሰቢያው በዓል በየዓመቱ መቼ ይከበራል? እኛስ በበዓሉ ላይ መገኘት ያለብን ለምንድን ነው? ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ቁልፍ ጥቅሶችን አብራራ። ሁሉም አስፋፊዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸው እንዲሁም በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ከሚጋብዟቸው ሰዎች ጋር አንቀጾቹን በማንበብ፣ በቁልፍ ነጥቦች ላይ በማወያየትና ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት ቀላል ጥያቄዎች በመጠቀም ይህን ክፍል እንዲያጠኑ አበረታታ።
መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 51 (127)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ሣጥን ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስ።
23 ደቂቃ:- ክርስቶስ በአምላክ ዝግጅት ውስጥ ያለው ሚና። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 10-13 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። “የክርስቶስ ሚና ምንድን ነው?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያሉትን የመጀመሪያዎቹን ሁለት አንቀጾች በምትወያዩበት ወቅት ሦስት ወይም አራት ደቂቃ ተጠቅመህ የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ ወረቀት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ሐሳብ ከሰጠህ በኋላ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በየካቲት 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 አንቀጽ 3 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ከልስ።
12 ደቂቃ:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር ያበረታናል። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2006 በተባለው ቡክሌት መቅድም ላይ ተመሥርቶ በንግግርና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። አንድ ቤተሰብ የዕለቱን ጥቅስና ሐሳቡን አንድ ላይ ሲወያዩበት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 85 (191) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 (58)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥር 15 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። የመጋበዣ ወረቀቱን በመጠቀም ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ለመታሰቢያው በዓል እንዴት መጋበዝ እንደሚቻል ግለጽ።
15 ደቂቃ:- የማይናወጥ አንድነት ያለው የወንድማማች ማኅበር። በንቁ! መጽሔቶች ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በተጨማሪም በ31/1/06 የተላከውን ደብዳቤ መመልከት ትችላለህ። ከመጋቢት 22, 2002 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 9 አን. 1-3 ላይ አጠር ያለ መግቢያ አዘጋጅ። ቀጥሎ በዚሁ ንቁ! መጽሔት ገጽ 6 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተጠቅመህ አደገኛ በሆነ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ሊደርስ የሚችለውን የአካልም ሆነ የንብረት ጉዳት እንዴት መቀነስ እንደሚችሉ አስረዳ። [ከታኅሣሥ 22, 1987 ንቁ! መጽሔት (እንግሊዝኛ) ገጽ 26 አን. 1-4 ላይ በተለይ ደግሞ መደናገጥ እንደማያስፈልግ ከሚናገረው አንቀጽ አንዳንድ ሐሳቦችን ማከል ይቻላል።] በኅዳር 8, 1985 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 26ና 27 “ኸልፕ ኒድድ ፋስት!” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር እንዲሁም በመስከረም 2000 ንቁ! ገጽ 25 እና በኅዳር 2001 ንቁ! ገጽ 14-16 ላይ በተገለጸው መሠረት ክርስቲያን እረኞች (የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቾች፣ ሌሎች ሽማግሌዎች፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች፣ በቅርንጫፍ ቢሮው ውስጥ የሚሠሩ ወንድሞች) የወንድሞቻችንን ደኅንነት በመከታተል ረገድ የሚጫወቱትን ሚና አጉላ። ወንድሞች ከጉባኤ ሽማግሌዎቻቸው ብሎም ከቅርንጫፍ ቢሮው ጋር በተቻለ ፍጥነት ግንኙነት ባደረጉበት ወቅት ያሳዩትን ጥበብና ሥርዓታማነት ጎላ አድርገህ ግለጽ። በተጨማሪም ወንድሞችና እህቶች እንዲህ ባለው አሳዛኝ ወቅት ጭምር ምሥራቹን በመመሥከር ችግር ላይ የወደቁትን ማጽናናታቸው ምን ያህል ጠቃሚ እንደነበረ አስረዳ። አብዛኞቻችን የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞን የማያውቅ ቢሆንም እንኳ የተሰጠው ማብራሪያ በሌሎች አስቸጋሪ ወቅቶችም ሊረዳን እንደሚችል በመናገር ንግግርህን ደምድም።
18 ደቂቃ:- በየካቲት 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በሚገኘውና “ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
መዝሙር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 55 (133)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎች። አስፋፊዎች በመጋቢት ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ሲያበረክቱ ያገኙት ተሞክሮ ካለ በተለይ ጥናት ያስጀመሩ ካሉ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ:- “ትሑት የሆኑ ሰዎች በአምላክ መንገድ እንዲሄዱ አስተምሯቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከሐምሌ 1, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16 አንቀጽ 9 ላይ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ።
መዝሙር 18 (42) እና የመደምደሚያ ጸሎት።