ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 24, 2006 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 6 እስከ ሚያዝያ 24, 2006 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. በምናስተምርበት ወቅት ከአንዱ ሐሳብ ወደ ሌላው ስንሸጋገር ቆም ማለት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? ሆኖም ይህን እንዳናደርግ ምን ሊያግደን ይችላል? [be ገጽ 98 አን. 3-4]
2. ለሌሎች ሰዎች ስንመሠክር በንግግራችን መሃል ቆም ማለት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? [be ገጽ 99 አን. 5 እስከ ገጽ 100 አን. 3]
3. ንግግር በምንሰጥበት ጊዜ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ ማጥበቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንንስ ችሎታ እንዴት ልናዳብረው እንችላለን? [be ገጽ 101 አን. 1-5፣ ሣጥን]
4. ለሌሎች በምናነብበት ወቅት በምናነበው ጽሑፍ ውስጥ ላሉት ዋና ዋና ነጥቦች ለየት ያለ አጽንዖት መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 105 አን. 1-6]
5. በምናስተምርበት ጊዜ ተስማሚ የድምፅ መጠን መጠቀማችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የድምፃችን መጠን ምን ያህል መሆን እንዳለበት ለመወሰን ምን ሊረዳን ይችላል? [be ገጽ 107-108]
ክፍል ቁጥር 1
6. በዘመናችን የሚገኙት ክርስቲያኖች ያሉበት ሁኔታ መርዶክዮስና አስቴር ይኖሩበት ከነበረው ጊዜ ጋር ተመሳሳይ የሆነው በምን መልኩ ነው? ምሳሌነታቸውንስ እንዴት ልንኮርጅ እንችላለን? [bsi ገጽ 11 አን. 17]
7. ሰሎሞን “ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነበር” ሲል ስለ ምን መናገሩ ነበር? (መክ. 2:11) [w04 10/15 ገጽ 4 አን. 3-4]
8. ለይሖዋ ፍቅር ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው? (ማር. 12:30) [w04 3/1 ገጽ 19-21]
9. በመንፈሳዊ እሴቶችና ቁሳዊ ሀብትን በማሳደድ መካከል ምን ልዩነት አለ? [w04 10/15 ገጽ 5-7]
10. በጉባኤም ሆነ በትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ትኩረታችን ሳይከፋፈል በጥሞና ለማዳመጥ ምን ሊረዳን ይችላል? [be ገጽ 15-16]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. የሐማ ፊት የተሸፈነው ለምን ነበር? (አስቴር 7:8)
12. በኤልፋዝ አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ አድርጎ የነበረው ምን ዓይነት መንፈስ ነው? (ኢዮብ 4:15, 16) [w05 9/15 ገጽ 26 አን. 2]
13. በኢዮብ 7:9, 10 እንዲሁም ኢዮብ 10:21 ላይ የተመዘገቡት አገላለጾች ኢዮብ በትንሣኤ እንደማያምን ያመለክታሉ?
14. “የጥርሴ ቆዳ ብቻ ቀርቶ አመለጥሁ” የሚለው የኢዮብ አባባል ምን ያመለክታል? (ኢዮብ 19:20 NW)
15. ኢዮብ “ጨዋነቴንም [“ታማኝነቴን፣” NW] እስክሞት ድረስ አልጥልም” ሲል ምን ማለቱ ነበር? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (ኢዮብ 27:5)