የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/06 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሚያዝያ 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 24 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 1 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 4/06 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሚያዝያ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 47 (112)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ የቤቱ ባለቤት ለመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጥሩ ፍላጎት ስላሳየ አስፋፊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ሲያበረክት የሚያሳይ ይሁን።

15 ደቂቃ:- “ቅንዓታችን እንዳይቀዘቅዝ ምን ማድረግ እንችላለን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከሰኔ 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14 አን. 13 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦችን አክል።

20 ደቂቃ:- “ፕሮግራምህን ማስተካከል ትችላለህ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ክፍሉን ለጉባኤው እንደሚስማማ አድርገህ አቅርበው። ጉባኤው አመሻሹ ላይ አገልግሎት ለመውጣት የሚያስችል ዝግጅት ካለው ተናገር።

መዝሙር 6 (13) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጉባኤው ለልዩ የሕዝብ ንግግሩ ያደረገውን ዝግጅት ጎላ አድርገህ ግለጽ። ሁሉም የሚያዝያ 1ን መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ተጠቅመው በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙትን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻቸውንና ሌሎች ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ለንግግሩ መጋበዛቸውን እንዲቀጥሉ አበረታታቸው። መጠበቂያ ግንቡን ተጠቅመው ሰዎችን ወደ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ መጋበዝ የቻሉ ካሉ ሁለት ወይም ሦስት ተሞክሮዎችን በአጭሩ ተናገር።

12 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

18 ደቂቃ:- “በር ላይም ሆነ በስልክ የምናስጠናቸው ሰዎች እድገት እንዲያደርጉ መርዳት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ አስፋፊ በር ላይ እንደቆመ የሚመራው ጥናት ቤት ውስጥ የሚመራበትን መንገድ ለማመቻቸት ምን ማለት እንደሚችል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 70 (162) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 61 (144)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በግንቦት ወር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ማበርከታችንን እንቀጥላለን። በገጽ 6 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የየካቲት 15 እና የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከሠርቶ ማሳያው በመቀጠል ከእነዚህ መጽሔቶች ላይ በአገልግሎት ክልሉ የሚገኙ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ሌሎች ርዕሶችን ጥቀስ።

12 ደቂቃ:- አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው? በሚያዝያ 1, 2006 መጠበቂያ ግንብ ጀርባ ላይ በሚገኘው ሐሳብ ተመሥርቶ በንግግርና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ሰዎች በልዩ የሕዝብ ንግግሩ ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ የሚያስችሏችሁን አጋጣሚዎች በሙሉ ጥሩ አድርጋችሁ ተጠቀሙባቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን እንዲሁም በጥናቱ ወቅት የማይገኙ የቤተሰባቸውን አባላት መጋበዛችሁን አትዘንጉ። ፍላጎት ያላቸውና በመስክ አገልግሎት የምናገኛቸው ሌሎች ሰዎች በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ልንጋብዛቸው ይገባል። አንድን የቀዘቀዘ ወይም በስብሰባዎች ላይ መገኘት ያቆመን ሰው የሚያዝያ 1, 2006ን መጠበቂያ ግንብ በመጠቀም እንዴት መጋበዝ እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

23 ደቂቃ:- ምሥራቹን የምንሰብክባቸው መንገዶች። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 92-95 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ።

መዝሙር 85 (191) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 93 (211)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሚያዝያ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን “በጥናቶችህ አማካኝነት ጥናት ለማግኘት ሞክረሃል?” የሚለውን ሣጥን ተወያዩበት።

15 ደቂቃ:- “ዓይን ለዓይን ለመተያየት በመጣር ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ አስፋፊ ሕዝብ በሚበዛበት አካባቢ ካገኘው ሰው ጋር ዓይን ለዓይን በመተያየት ትኩረቱን ለመሳብ ጥረት አድርጎ ውይይት ከጀመረ በኋላ ምሥክርነት ሲሰጥ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

20 ደቂቃ:- በይሖዋ ሥራዎች ላይ አሰላስሉ። (መዝ. 77:12) በ2006 የዓመት መጽሐፍ አንዳንድ ገጽታዎች ላይ ተመሥርቶ በንግግርና በውይይት የሚቀርብ። ከበላይ አካሉ በተጻፈው ደብዳቤ ላይ ያሉትን የሚያበረታቱ ነጥቦች ተናገር። (ገጽ 3-5) “የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ከልስ። (ገጽ 10-11) ያለፈውን ዓመት ጎላ ያሉ እንቅስቃሴዎችና ተሞክሮዎች ተናገር። (ገጽ 6-64) አድማጮች የ2006ን የዓመት መጽሐፍ ሲያነብቡ ያገኟቸውን ጠቃሚ ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸው ለይሖዋ ድርጅት አድናቆት እንዲኖራቸው ለማድረግ በመጽሐፉ እንዲጠቀሙ ሁሉንም አበረታታ።

መዝሙር 37 (82) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ