የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/06 ገጽ 5-6
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 4/06 ገጽ 5-6

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ወቅት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ሐምሌ:- ብሮሹሮች።

◼ ለአውራጃ ስብሰባ ደረት ላይ የሚለጠፈው ባጅ ካርድ ከጽሑፎች ጋር ስለሚላክላችሁ ማዘዝ አያስፈልጋችሁም። ይሁን እንጂ ጉባኤው ተጨማሪ ካርድ ካስፈለገው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14) ማዘዝ ይኖርበታል። በጉባኤያችሁ ውስጥ የባጅ መያዣ ፕላስቲክ የሚፈልጉ ካሉ ማዘዝ ይኖርባችኋል።

◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቁ ቅጾች ይኑሯችሁ። የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ ቅጾችን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላካችሁ በፊት በደንብ መሞላታቸውን ማረጋገጥ አለባችሁ።

◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሁሉንም ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችና ጸሐፊዎች ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘት ይፈልጋል። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) ሞልቶና ፈርሞ በፍጥነት ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት። የስልክ ቁጥር ለውጥ ሲኖርም እንደዚህ መደረግ ይኖርበታል።

◼ ታኅሣሥ 13, 2005 በላክንላችሁ ደብዳቤ ላይ የኦሮምኛ መጠበቂያ ግንብ ከጥናት ርዕሶች ሌላ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን አካትቶ እንደሚወጣ ገልጸንላችሁ ነበር። ለጊዜው ግን በወሩ ውስጥ የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ብቻ ይዞ እንደሚወጣ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። በዚህ ቋንቋ የተዘጋጀውን መጽሔት ማግኘት የምትፈልጉ ሁሉ በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ትችላላችሁ።

◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፣ አረብኛ፣ ቻይንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ሂንዲ፣ ኑዌር፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ ቻይንኛ:- T-75 (መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል!)፤ እንግሊዝኛ:- በሲዲ የተዘጋጀ የ2005 የመጠበቂያ ግንብ ቤተ መጻሕፍት፤ ኦሮምኛ:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፤ ሲዳምኛ:- T-26 (ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?)፤ ትግርኛ:- ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ፣ የይሖዋ ምሥክሮች እነማን ናቸው?፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው 2006።

◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- T-15 (አዲስ ዓለም)፣ T-19 (ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን?)፣ T-26 (ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?)፣ የውዳሴ መዝሙር፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ የወጣቶች ጥያቄ፤ አረብኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ T-26 (ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?)፤ ቻይንኛ:- T-26 (ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?)፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ ፒስ ኤንድ ሃፒነስ፤ እንግሊዝኛ:- ጂሆቫስ ዊትነስስ-ሁ አር ዘይ?፣ ፕሮክሌይመርስ፣ በደስታ ኑር፣ የ2002፣ የ1989፣ የ1990፣ የ1994፣ የ1995፣ የ1996፣ የ1997 የንቁ! ጥራዞች፣ የ2002፣ የ1994፣ የ1995፣ የ1996፣ የ1997 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች፤ ሂንዲ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፤ ኦሮምኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፤ ሲዳምኛ:- T-15 (አዲስ ዓለም)፤ ትግርኛ:- T-20 (ማጽናኛ)፣ T-21 (ቤተሰብ)፣ T-22 (ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?)፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ የወጣቶች ጥያቄ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ