መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 15
“አብዛኞቻችን የምንወደውን ሰው በሞት በማጣታችን የተነሳ መሪር ሐዘን ደርሶብናል። እዚህ ጥቅስ ላይ ስላለው አጽናኝ የሆነ ተስፋ ሰምተው ያውቃሉ? [የሐዋርያት ሥራ 24:15ን አንብብና መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ያም ሆኖ ብዙ ሰዎች ‘ትንሣኤ የሚያገኙት እነማን ናቸው? የሞቱ ሰዎች የሚነሱት መቼ ነው? የሚነሱትስ የት ነው?’ የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳሉ። ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀው የሚከተለው አባባል ስለ አምላክ ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን ያጎላል። [ማቴዎስ 4:4ን አንብብ።] ሆኖም ብዙ ሰዎች የአምላክን ቃል መረዳት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። እርስዎንስ አስቸግሮት ያውቃል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የሚያስችሉ አንዳንድ ተግባራዊ ሐሳቦችን ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 15
“ሁሉም ሰው ለማለት ይቻላል ለቤተሰብ ደስታ ቁልፍ ከሆኑት ነገሮች አንዱ በግልጽ መነጋገር መሆኑን ይስማማል። ሆኖም ብዙ ሰዎች እንደዚያ ማድረግ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። እንዲህ ማድረጉ አስቸጋሪ የሆነባቸው ለምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት በግልጽ የመነጋገር ችሎታን ለማዳበር የሚረዱ አንዳንድ ሐሳቦችን ይዟል።” ያዕቆብ 1:19ን አንብብ።
ንቁ! ሚያዝያ 2006
“ብዙ ሰዎች መስቀልን ተጠቅመው ሲጸልዩ ከአምላክ ጋር ይበልጥ እንደተቀራረቡ እንደሚሰማቸው ይናገራሉ። ሆኖም አንዳንዶች ‘ኢየሱስ የተገደለበትን መሣሪያ ማምለክ ተገቢ ነው? በእርግጥ ኢየሱስ የተሰቀለው በመስቀል ላይ ነው?’ የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳሉ። በዚህ መጽሔት ገጽ 12 ላይ የሚገኘው ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች ምን መልስ እንደሚሰጥ ይናገራል።” የሐዋርያት ሥራ 5:30ን አንብብ።