የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሰኔ 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 74 (168)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ መጽሔቱ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲበረከት የሚያሳይ ይሁን።
20 ደቂቃ:- “አገልግሎታችን ርኅራኄ የሚንጸባረቅበት ሥራ ነው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
15 ደቂቃ:- ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ መተማመን። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 8 (21)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ:- በወቅቱ የተነገረ ቃል ምንኛ መልካም ነው! በጥር 1, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-19 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በንግግሩ መግቢያ ላይ “የሚያስገኛቸው መልካም ውጤቶች” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያሉትን ሌሎችን ማመስገን የሚያስገኛቸውን አራት ጥቅሞች ጎላ አድርገህ ጥቀስ። ከዚያም አድማጮች ከዚህ በታች በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ:- ከሁሉ የላቀ ውዳሴ የሚገባው ማን ነው? የእምነት አጋሮቻችን ተገቢ የሆነ ምስጋና የሚገባቸው ለምንድን ነው? በጉባኤ ውስጥ ሌሎችን ለማመስገን የሚያስችሉ ምን አጋጣሚዎች አሉ? የቤተሰባችንን አባላት ማመስገናችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? እንዲህ ማድረግስ የምንችለው እንዴት ነው? ሌሎች ሲያመሰግኑህ የተበረታታህበት ወይም ጥንካሬ ያገኘህበት ጊዜ አለ?
15 ደቂቃ:- “ሰዎችን በማመስገን ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አስፋፊው፣ የቤቱ ባለቤት የሚሰጠውን አስተያየት በጥሞና ሲያዳምጥ፣ ከዚያም ስለሰጠው ሐሳብ ከልብ ሲያመሰግነውና ተገቢ የሆነ ጥቅስ በማንበብ የግለሰቡን አስተያየት ሲያጠናክር የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 94 (212) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 30 (63)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የግንቦት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ መደምደሚያ ላይ አስፋፊው በቀጣዩ ጉብኝት ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅሞ መልስ የሚሰጥበት አመራማሪ ጥያቄ ያቀርባል።
20 ደቂቃ:- ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተመልሳችሁ አነጋግሩ። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። በጥር 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 አንቀጽ 1 እና በመጋቢት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8-9 አንቀጽ 5-11, 16 እንዲሁም ገጽ 8 ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ የተጠቀሱትን ሐሳቦች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል በሚያሳይ መንገድ ክፍሉን አቅርበው።
15 ደቂቃ:- በሐምሌ ወር ምሥራቹን መስበክ። በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ይበልጥ የሚስቧቸው ርዕሰ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተሰኘውን መጽሐፍ ተጠቅመው ጥሩ ውጤት ላገኙ ምናልባትም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላስጀመሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። ከዚያም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ አቀራረብ በመጠቀም መጽሐፉ ከቤት ወደ ቤት በሚደረግ አገልግሎት ላይ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።—የጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 አን. 5ን ተመልከት።
መዝሙር 59 (139) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 21 (46)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሰኔ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በጥር 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 ላይ ከሚገኘው የጥያቄ ሣጥን ውስጥ ዋና ዋና ነጥቦችን አቅርብ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- “መንፈሳዊ ግቦችህ ላይ እንዴት መድረስ ትችላለህ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በጉባኤው ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ለወደፊቱ ጊዜ ያሏቸው መንፈሳዊ ግቦች ምን እንደሆኑና ግባቸው ላይ ለመድረስ ምን የሚያደርጉት ነገር እንዳለ ጠይቃቸው። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት ወጣቶች አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።
መዝሙር 61 (144) እና የመደምደሚያ ጸሎት።