የ2007 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያ
የ2007 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ክፍሎቹ የሚቀርቡባቸው ጽሑፎች፦ መጽሐፍ ቅዱስ [አ.መ.ት]፣ መጠበቂያ ግንብ [w-AM]፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም [be-AM]፣ “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው (ኤርሚያስ—ሚልክያስ) [bsi07-AM] እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rs-AM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ከተከፈተ በኋላ ከዚህ በታች በሰፈረው መመሪያ መሠረት ይከናወናል። እያንዳንዱ ክፍል ሲያበቃ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ቀጣዩን ክፍል ያስተዋውቃል።
የንግግር ባሕርይ፦ 5 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች፣ ረዳት ምክር ሰጪው ወይም ጥሩ ችሎታ ያለው ሌላ ሽማግሌ፣ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከተባለው መማሪያ መጽሐፍ ላይ በተወሰደ አንድ የንግግር ባሕርይ ላይ ተመሥርቶ ክፍል ያቀርባል። (በቂ ሽማግሌዎች በሌሉባቸው ጉባኤዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያላቸው የጉባኤ አገልጋዮች ይህን ክፍል ሊያቀርቡ ይችላሉ።)
ክፍል ቁ. 1፦ 10 ደቂቃ። ይህ ክፍል ብቃት ባለው አንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም በተባለው መጽሐፍ ወይም “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው በተባለው ብሮሹር ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ለአሥር ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ይቀርባል። ዓላማው በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር ለጉባኤው ይበልጥ ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ ማጉላት እንጂ የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ አይደለም። በፕሮግራሙ ላይ የተሰጠውን ጭብጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን ንግግር እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች ክፍላቸውን በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አቅርበው መጨረስ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይችላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 10 ደቂቃ። በመጀመሪያዎቹ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር እያዛመደ ያቀርበዋል። ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርበው ወንድም፣ ለሳምንቱ ከተመደበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ በፈለገው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ሐሳብ መስጠት ይችላል። ክፍሉ ለሳምንቱ የተመደቡትን ምዕራፎች በመከለስ ብቻ መቅረብ አይኖርበትም። ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት እንደሚጠቅም እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ተናጋሪው ለእርሱ የተመደበለትን አምስት ደቂቃ ብቻ በመጠቀም አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አምስት ደቂቃ ላለመንካት መጠንቀቅ ይኖርበታል። ቀጥሎ አድማጮች ከሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ልባቸውን የነካውንና ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን ሐሳብ በአጭሩ (በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ) እንዲናገሩ ይጋብዛል። ከዚያም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በሁለተኛው አዳራሽ ውስጥ ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች መሄድ እንደሚችሉ ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ በ4 ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ የሚቀርብ። ይህን ክፍል አንድ ወንድም በንባብ ያቀርበዋል። ተማሪው መግቢያ እና መደምደሚያ ማዘጋጀት ሳያስፈልገው ክፍሉን በንባብ ብቻ ያቀርበዋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዎቹ ክፍሉን በሚገባ ተረድተው፣ በቅልጥፍና፣ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ በማጥበቅ፣ ድምፅን በመለዋወጥ፣ በተገቢው ቦታ ቆም በማለትና የራሳቸውን ተፈጥሯዊ አነጋገር በመጠቀም እንዲያነብቡ ለመርዳት ጥረት ያደርጋል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። ይህን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡ ተማሪዎች በአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ ከተዘረዘሩት መቼቶች መካከል አንዱ ይመደብላቸዋል አሊያም ራሳቸው እንዲመርጡ ይደረጋል። ተማሪዋ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኘውን ጭብጥ መጠቀምና ክፍሉን ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል በሚስማማ መንገድ ማቅረብ ይኖርባታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪዋ በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ማሰባሰብ ይኖርባታል። አዳዲስ ተማሪዎች ጭብጡ ብቻ የተሰጠባቸውን ክፍሎች ማቅረብ አይኖርባቸውም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ እንዴት እንደምታዳብር እንዲሁም የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉምና የክፍሉን ዋና ዋና ነጥቦች እንድትገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። ተማሪው የተሰጠውን ጭብጥ ማዳበር ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪው በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ያሰባስባል። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ አድማጮቹን ግምት ውስጥ በማስገባት በንግግር መልክ ያቀርበዋል። ሆኖም ክፍሉን አንዲት እህት የምታቀርበው ከሆነ ለክፍል ቁጥር 3 በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተገቢ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ክፍል ቁጥር 4ን ለአንድ ወንድም ሊሰጥ ይችላል። የኮከብ ምልክት ያለባቸው ክፍሎች በንግግር መልክ መቅረብ ያለባቸው ስለሆኑ ለወንድሞች ብቻ መሰጠት ይኖርባቸዋል።
ምክር፦ 1 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪው የሚሠራበትን የንግግር ባሕርይ አስቀድሞ አይናገርም። እያንዳንዱ የተማሪ ክፍል (ቁ. 2፣ ቁ. 3 እና ቁ. 4) ከቀረበ በኋላ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የንግግሩን ገንቢ ጎኖች አንስቶ ተማሪውን ያመሰግናል። ዓላማው “ጥሩ ነው” ብሎ ለማለፍ ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ የተማሪው አቀራረብ ጥሩ የሆነበትን ምክንያት ለይቶ መጥቀስ ያስፈልገዋል። የእያንዳንዱን ተማሪ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከስብሰባው በኋላ ወይም በሌላ ጊዜ ገንቢ የሆነ ተጨማሪ ምክር በግል መስጠት ይችላል።
ጊዜ መጠበቅ፦ ክፍል የሚያቀርቡትም ሆኑ ምክር ሰጪው የተመደበላቸውን ጊዜ ማሳለፍ አይኖርባቸውም። ከቁጥር 2 እስከ 4 ያሉትን ክፍሎች የሚያቀርቡት ወንድሞች የተመደበላቸው ጊዜ ሲሞላ በዘዴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለ ንግግር ባሕርይ የሚናገረውን የመክፈቻ ንግግር፣ ክፍል ቁጥር 1ን ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርቡ ወንድሞች ሰዓት ካሳለፉ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይገባል። ሁሉም ሰዓታቸውን በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ጸሎትንና መዝሙርን ሳይጨምር ጠቅላላው ፕሮግራም 45 ደቂቃ ይፈጃል።
ምክር መስጫ ቅጽ፦ በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
ረዳት ምክር ሰጪ፦ የሽማግሌዎች አካል፣ ከትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተጨማሪ ረዳት ምክር ሰጪ ሆኖ የሚያገለግል ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ሊመርጥ ይችላል። በጉባኤው ውስጥ በርካታ ሽማግሌዎች ካሉ በየዓመቱ ብቃት ያላቸው ሽማግሌዎች እየተቀያየሩ ይህን ኃላፊነት ሊይዙ ይችላሉ። የዚህ ወንድም ኃላፊነት ንግግር ቁጥር 1ን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ለሚያቀርቡ ወንድሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግል ምክር መስጠት ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እነዚህን ክፍሎች የሚያቀርቡ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ንግግራቸውን ባቀረቡ ቁጥር ምክር ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም።
የቃል ክለሳ፦ 30 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በየሁለት ወሩ የሚደረገውን የቃል ክለሳ ይመራል። ክለሳው የሚደረገው የንግግር ባሕርይና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረቡ በኋላ ይሆናል። ክለሳው፣ የክለሳውን ሳምንት ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የቀረቡትን ትምህርቶች ይሸፍናል። የቃል ክለሳው ጉባኤያችሁ የወረዳ ስብሰባ በሚያደርግበት ሳምንት ላይ ከዋለ ክለሳው (እና በሳምንታዊ ፕሮግራሙ ላይ ያሉት ሌሎች ክፍሎች) በቀጣዩ ሳምንት ይቀርባሉ፤ የቀጣዩ ሳምንት ፕሮግራም ደግሞ በወረዳ ስብሰባው ላይ ይቀርባል። የቃል ክለሳውና የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት በሚገጣጠሙበት ጊዜ በፕሮግራሙ ላይ የሰፈረው መዝሙር፣ የንግግር ባሕርይና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች እንዳሉ ይወሰዳሉ። የማስተማሪያ ንግግሩ (ከንግግር ባሕርይ ቀጥሎ ይቀርባል) ለሚቀጥለው ሳምንት ከወጣው ፕሮግራም ላይ ይወሰዳል። በቀጣዩ ሳምንት፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ የወጣው የንግግር ባሕርይ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ የቃል ክለሳው ይቀጥላል።
ፕሮግራም
ጥር 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 24-28 መዝ. 13 (33)
የንግግር ባሕርይ፦ አድማጮችን በሚጠቅም መንገድ ትምህርቱን ማቅረብ (be ገጽ 158 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡህን የተማሪ ክፍሎች መዘጋጀት (be ገጽ 43 አን. 1–ገጽ 44 አን. 3)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 26:1-18
ቁ. 3፦ ፅንስ ማስወረድ የተከለከለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 25-26 አን. 4)
ቁ. 4፦ ‘ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መልበስ’ የምንችለው እንዴት ነው? (ሮሜ 13:14)
ጥር 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 29-33 መዝ. 18 (42)
የንግግር ባሕርይ፦ አድማጮች የትምህርቱን ጠቀሜታ እንዲያስተውሉ መርዳት (be ገጽ 158 አን. 5–ገጽ 159 አን.3)
ቁ. 1፦ ከጭብጡና ከመቼቱ ጋር የሚስማማ ዝግጅት (be ገጽ 44 አን. 4–ገጽ 46 አን. 1)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 30:1-14
ቁ. 3፦ # ‘የራሴን ሰውነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመወሰን መብት አለኝ’ ለሚል ሰው መልስ መስጠት (rs ገጽ 26 አን. 5)
ቁ. 4፦ ይሖዋ ልጆችን እንደሚወድ እንዴት እናውቃለን?
ጥር 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 34-37 መዝ. 100 (222)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ ቃላትን መምረጥ (be ገጽ 160 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ መልካምና ክፉን በሚመለከት የኢየሱስ ዓይነት አመለካከት ማዳበር (w05 1/1 ገጽ 9-10 አን. 11-15)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 34:1-15
ቁ. 3፦ እውነተኛ ፍቅር ማዳበር የሚቻለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ አዳምና ሔዋን በታሪክ ውስጥ የነበሩ እውነተኛ ሰዎች ናቸው? (rs ገጽ 27-28)
ጥር 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 38-42 መዝ. 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ ለመረዳት የማያስቸግር አገላለጽ (be ገጽ 161 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ለተቃውሞ እጅ አትስጡ (w05 1/1 ገጽ 15 አን. 16-18)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 38:9-22
ቁ. 3፦ # ‘አዳም ኃጢአት እንዲሠራ የአምላክ ፈቃድ ነበር’ ለሚል ሰው መልስ መስጠት (rs ገጽ 29 አን. 1-2)
ቁ. 4፦ ሌሎች መጥፎ ዝንባሌ እንዳላቸው ከማሰብ መቆጠብ ያለብን ለምንድን ነው?
ጥር 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 43-46 መዝ. 48 (113)
የንግግር ባሕርይ፦ የተለያዩና ትክክለኛ ቃላት ተጠቀም (be ገጽ 161 አን. 5–ገጽ 162 አን. 4)
ቁ. 1፦ የይሖዋን ፍርድ መጠራጠር የሌለብን ለምንድን ነው? (w05 2/1 ገጽ 23-24 አን. 4-9)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 45:1-14
ቁ. 3፦ የቀድሞ አባቶችን ማምለክ ከንቱ የሆነው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 29 አን. 3–ገጽ 31 አን. 2)
ቁ. 4፦ * ክርስቲያኖች በፉክክር መንፈስ ራሳቸውን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር መቆጠብ ያለባቸው ለምንድን ነው?
የካ. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 47-51 መዝ. 35 (79)
የንግግር ባሕርይ፦ ኃይል ያላቸው፣ ስሜቱን የሚያስተላልፉና ገላጭ የሆኑ ቃላት (be ገጽ 163 አን. 1–ገጽ 164 አን. 1)
ቁ. 1፦ የይሖዋ ቃል ንጹሕና ታማኝ እንድንሆንም ይረዳናል (w05 4/15 ገጽ 11-12 አን. 5-11)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 50:1-11
ቁ. 3፦ የቀድሞ አባቶችን ማምለክ ይሖዋ አምላክን የሚያሳዝነው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 31 አን. 3-8)
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ መስጠትን ያወግዛል?
የካ. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 52-57 መዝ. 59 (139)
የንግግር ባሕርይ፦ የሰዋስውን ሕግ የጠበቀ አነጋገር (be ገጽ 164 አን. 2-6)
ቁ. 1፦ የይሖዋ ቃል ድፍረት ይሰጣል (w05 4/15 ገጽ 13 አን. 12-14)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 55:1-13
ቁ. 3፦ የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ የሚንጸባረቅበት ሕይወት መምራት ጥቅም ያስገኛል
ቁ. 4፦ ፀረ ክርስቶስ የሚባሉት እነማን ናቸው? (rs ገጽ 32-33)
የካ. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 58-62 መዝ. 77 (174)
የንግግር ባሕርይ፦ በአስተዋጽኦ መጠቀም (be ገጽ 166 አን. 1–ገጽ 167 አን. 1)
ቁ. 1፦ ኢሳይያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi06 ገጽ 31-32 አን. 34-39)
ቁ. 2፦ ኢሳይያስ 60:1-14
ቁ. 3፦ የአምላክ ባሪያ መሆን አስደሳች የሆነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ * ከሃዲዎችን ለይቶ ማወቅ (rs ገጽ 34 አን. 1–ገጽ 35 አን. 2)
የካ. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 63-66 መዝ. 25 (53)
የንግግር ባሕርይ፦ መናገር የምትፈልገውን ሐሳብ አቀናብር (be ገጽ 167 አን. 2–ገጽ 168 አን. 1)
የቃል ክለሳ
መጋ. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 1-4 መዝ. 32 (70)
የንግግር ባሕርይ፦ አስተዋጽኦህ ቅልብጭ ያለ ይሁን (be ገጽ 168 አን. 2–ገጽ 169 አን. 6)
ቁ. 1፦ የኤርምያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi07 ገጽ 3 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 3:1-13
ቁ. 3፦ እውነተኛ ደስታ በምን ላይ የተመካ ነው?
ቁ. 4፦ * ለከሃዲዎች ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? (rs ገጽ 35 አን. 3–ገጽ 36 አን. 5)
መጋ. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 5-7 መዝ. 71 (163)
የንግግር ባሕርይ፦ ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ማዋቀር (be ገጽ 170 አን. 1–ገጽ 171 አን. 2)
ቁ. 1፦ ለጉባኤ የሚቀርቡ ንግግሮችን መዘጋጀት (be ገጽ 47 አን. 1–ገጽ 49 አን. 1)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 5:1-14
ቁ. 3፦ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን በጴጥሮስ ላይ አልመሠረታትም (rs ገጽ 36 አን. 6–ገጽ 38 አን. 4)
ቁ. 4፦ ከዘፀአት 14:11 የሚገኘውን ትምህርት በዘመናችን ልንሠራበት የምንችለው እንዴት ነው?
መጋ. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 8-11 መዝ. 95 (213)
የንግግር ባሕርይ፦ ትምህርቱን በሚጨበጥ መንገድ ማቅረብ (be ገጽ 171 አን. 3–ገጽ 172 አን. 5)
ቁ. 1፦ የአገልግሎት ስብሰባ ክፍሎችንና ሌሎች ንግግሮችን መዘጋጀት (be ገጽ 49 አን. 2–ገጽ 51 አን. 1)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 10:1-16
ቁ. 3፦ አብርሃም፣ ኢዮብና ዳንኤል በትንሣኤ ተስፋ ላይ እምነት እንደነበራቸው እንዴት እናውቃለን?
ቁ. 4፦ ጴጥሮስ የተጠቀመባቸው ቁልፎች ምን ነበሩ? (rs ገጽ 38 አን. 5–ገጽ 40 አን. 5)
መጋ. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 12-16 መዝ. 74 (168)
የንግግር ባሕርይ፦ አግባብነት ያላቸውን ነጥቦች ብቻ ምረጥ (be ገጽ 173 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ቤዛው አምላክ ጻድቅ መሆኑን ያጎላል (w05 11/1 ገጽ 13-14)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 12:1-13
ቁ. 3፦ “ሐዋርያዊ ተተኪዎች” እውነተኛ ክርስቲያኖች አይደሉም (rs ገጽ 40 አን. 6–ገጽ 43 አን. 3)
ቁ. 4፦ አንድ ክርስቲያን ሊኮራ የሚገባው በምንድን ነው?
ሚያ. 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 17-21 መዝ. 89 (201)
የንግግር ባሕርይ፦ በራስ አባባል መናገር (be ገጽ 174 አን. 1–ገጽ 175 አን. 5)
ቁ. 1፦ ለሕዝብ የሚቀርብ ንግግር መዘጋጀት (be ገጽ 52 አን. 1–ገጽ 54 አን. 1)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 20:1-13
ቁ. 3፦ የአርማጌዶን ጦርነት የሚካሄደው የት ነው? (rs ገጽ 43 አን. 4–ገጽ 45 አን. 3)
ቁ. 4፦ * ለምክር ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል?
ሚያ. 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 22-24 መዝ. 51 (127)
የንግግር ባሕርይ፦ በራስህ አባባል ስትናገር ልትጠነቀቅባቸው የሚገቡ ጉዳዮች (be ገጽ 175 አን. 6–ገጽ 177 አን. 1)
ቁ. 1፦ ለተናጋሪው የተተዉ ውሳኔዎች (be ገጽ 54 አን. 2-4፤ ገጽ 55 ሣጥን)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 23:1-14
ቁ. 3፦ በአገልግሎት መካፈል ደስታ የሚያስገኝ ተግባር የሆነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ በአርማጌዶን የሚጠፋው ማን እና ምንድን ነው? (rs ገጽ 45 አን. 4–ገጽ 46 አን. 1)
ሚያ. 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 25-28 መዝ. 10 (27)
የንግግር ባሕርይ፦ ለሌሎች ማብራሪያ መስጠት ሲያስፈልግ (be ገጽ 177 አን. 2–ገጽ 178 አን. 2)
ቁ. 1፦ የማስተማር ችሎታህን አዳብር (be ገጽ 56 አን. 1–ገጽ 57 አን. 2)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 26:1-15
ቁ. 3፦ ከአርማጌዶን የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ? (rs ገጽ 46 አን. 2-7)
ቁ. 4፦ ምድር የተረገመችው በምን መንገድ ነበር? (ዘፍ. 3:17)
ሚያ. 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 29-31 መዝ. 63 (148)
የንግግር ባሕርይ፦ በጭውውት መልክ መናገር (be ገጽ 179-180)
ቁ. 1፦ “ለዩ” (be ገጽ 57 አን. 3–ገጽ 58 አን. 2)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 31:1-14
ቁ. 3፦ የይሖዋ ታላቅነት ገደብ የለውም የምንለው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ አርማጌዶን ከአምላክ ፍቅር ጋር አይጋጭም (rs ገጽ 46 አን. 8–ገጽ 47 አን. 2)
ሚያ. 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 32-34 መዝ. 23 (48)
የንግግር ባሕርይ፦ የድምፅ ጥራት (be ገጽ 181 አን. 1-4)
የቃል ክለሳ
ግን. 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 35-38 መዝ. 57 (136)
የንግግር ባሕርይ፦ አተነፋፈስህን መቆጣጠር (be ገጽ 181 አን. 5–ገጽ 184 አን. 1፤ ገጽ 182 ሣጥን)
ቁ. 1፦ አድማጮች በጉዳዩ ላይ እንዲያስቡ ማድረግ (be ገጽ 58 አን. 3–ገጽ 59 አን. 3)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 36:1-13
ቁ. 3፦ በአርማጌዶን ወቅት ገለልተኛ አቋም መያዝ አይቻልም (rs ገጽ 47 አን. 3-6)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች በዓለም ያሉ ሁኔታዎች አስተማማኝ አለመሆናቸው የሚያሳድርባቸውን ጭንቀት መቋቋም የሚችሉት እንዴት ነው?
ግን. 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 39-43 መዝ. 26 (56)
የንግግር ባሕርይ፦ የተወጠሩ ጡንቻዎችን ማዝናናት (be ገጽ 184 አን. 2–ገጽ 185 አን. 2፤ ገጽ 184 ሣጥን)
ቁ. 1፦ ትምህርቱ ተግባራዊ የሚሆንበትን መንገድ ማስረዳትና ጥሩ ምሳሌ መሆን (be ገጽ 60 አን. 1–ገጽ 61 አን. 3)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 39:1-14
ቁ. 3፦ ብሔራትን ወደ አርማጌዶን ወደሚያደርሳቸው ሁኔታ እየነዳቸው ያለው የማን ግፊት ነው? (rs ገጽ 47 አን. 7-8)
ቁ. 4፦ * እውነተኛ ክርስቲያኖች ለጋብቻ በሚጠናኑበት ወቅት ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ የሚጥሩት ለምንድን ነው?
ግን. 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 44-48 መዝ. 16 (37)
የንግግር ባሕርይ፦ ለሰዎች አሳቢነት ማሳየት (be ገጽ 186 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ከሰዎች ጋር የመወያየት ችሎታህን ማሻሻል (be ገጽ 62 አን. 1–ገጽ 64 አን. 1)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 46:1-17
ቁ. 3፦ ራስን ማታለል ሲባል ምን ማለት ነው? በዚህ ወጥመድ እንዳንወድቅ መጠንቀቅ የምንችለውስ እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰችውን ባቢሎን ማንነት ማወቅ (rs ገጽ 48 አን. 1-2)
ግን. 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 49-50 መዝ. 39 (86)
የንግግር ባሕርይ፦ በጥሞና ማዳመጥ (be ገጽ 187 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ውይይቱ እንዲቀጥል ማድረግ (be ገጽ 64 አን. 2–ገጽ 65 አን. 4)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 49:14-27
ቁ. 3፦ የጥንቷ ባቢሎን ምን በማድረግ የታወቀች ነበረች? (rs ገጽ 48 አን. 3–ገጽ 50 አን. 3)
ቁ. 4፦ ወላጆች ለልጆቻቸው ሊያነቡላቸው የሚገባው ለምንድን ነው?
ሰኔ 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 51-52 መዝ. 73 (166)
የንግግር ባሕርይ፦ ሌሎች እድገት እንዲያደርጉ መርዳት (be ገጽ 187 አን. 6–ገጽ 188 አን. 3)
ቁ. 1፦ ኤርምያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 4 አን. 36-39)
ቁ. 2፦ ኤርምያስ 52:1-16
ቁ. 3፦ ከአምላክ ርቆ በራስ ለመመራት መሞከር ሞኝነት ነው
ቁ. 4፦ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሃይማኖቶች የታላቂቱ ባቢሎን ክፍል እንደሆኑ ተደርገው ሊቆጠሩ የሚችሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 50 አን. 4–ገጽ 51 አን. 3)
ሰኔ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ 1-2 መዝ. 52 (129)
የንግግር ባሕርይ፦ እርዳታ መስጠት (be ገጽ 188 አን. 4–ገጽ 189 አን. 4)
ቁ. 1፦ የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi07 ገጽ 4-5 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ 2:1-10
ቁ. 3፦ በአስቸኳይ ከታላቂቱ ባቢሎን መውጣት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 51 አን. 4–ገጽ 52 አን. 3)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ደግነት የድክመት ምልክት አይደለም
ሰኔ 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ 3-5 መዝ. 20 (45)
የንግግር ባሕርይ፦ ሰዎችን ማክበር (be ገጽ 190 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 5-6 አን. 13-15)
ቁ. 2፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:1-13
ቁ. 3፦ ጥምቀት ምንድን ነው? አማኞች መጠመቅ ያለባቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 52 አን. 4–ገጽ 53 አን. 1)
ቁ. 4፦ * እውነተኛ ክርስቲያኖች በፖለቲካ ጉዳዮች የማይካፈሉት ለምንድን ነው?
ሰኔ 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 1-5 መዝ. 94 (212)
የንግግር ባሕርይ፦ አክብሮት የሚገለጽባቸው የተለያዩ መንገዶች (be ገጽ 191 አን. 1–ገጽ 192 አን. 1)
የቃል ክለሳ
ሐምሌ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 6-10 መዝ. 9 (26)
የንግግር ባሕርይ፦ ለአድማጮች አክብሮት እንዳለን የሚያሳይ አነጋገር (be ገጽ 192 አን. 2–ገጽ 193 አን. 2)
ቁ. 1፦ የሕዝቅኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi07 ገጽ 6-7 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 7:1-13
ቁ. 3፦ ወደ ይሖዋ ለመቅረብ ምን ያስፈልጋል? (ያዕ. 4:8)
ቁ. 4፦ የክርስቲያን የውኃ ጥምቀት የሚከናወነው ውኃ በመርጨት አይደለም፤ ሕፃናትም አይጠመቁም (rs ገጽ 53 አን. 2-7)
ሐምሌ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 11-14 መዝ. 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ በእርግጠኝነት መናገር (be ገጽ 194 አን. 1–ገጽ 195 አን. 2)
ቁ. 1፦ በጎ ነገር ከማድረግ አትታክት (w05 6/1 ገጽ 29-30)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 11:1-13
ቁ. 3፦ የውኃ ጥምቀት ከኃጢአት ያነጻል? (rs ገጽ 54 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ ራእይ 17:9-11ን የምንረዳው እንዴት ነው?
ሐምሌ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 15-17 መዝ. 11 (29)
የንግግር ባሕርይ፦ እርግጠኛ መሆናችን የሚንጸባረቅባቸው መንገዶች (be ገጽ 195 አን. 3–ገጽ 196 አን. 4)
ቁ. 1፦ መጥፎ አስተሳሰብን ተዋጉ! (w05 9/15 ገጽ 26-28)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 16:1-13
ቁ. 3፦ አስተዋይ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው? (ምሳሌ 13:16)
ቁ. 4፦ በመንፈስ ቅዱስ የሚጠመቁት እነማን ናቸው? (rs ገጽ 54 አን. 5–ገጽ 55 አን. 7)
ሐምሌ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 18-20 መዝ. 86 (193)
የንግግር ባሕርይ፦ በአነጋገር ዘዴኛ መሆን (be ገጽ 197 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የጠያቂውን አመለካከት ተረዳ (be ገጽ 66 አን. 1–ገጽ 68 አን. 1)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 18:19-29
ቁ. 3፦ በእሳት መጠመቅ በመንፈስ ቅዱስ ከመጠመቅ ጋር አንድ አይደለም (rs ገጽ 56 አን. 1-5)
ቁ. 4፦ የአምላክ መንግሥት እውን መስተዳድር መሆኑን የሚጠቁሙ ማስረጃዎች
ሐምሌ 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 21-23 መዝ. 15 (35)
የንግግር ባሕርይ፦ ስንመሰክር በአነጋገራችን ዘዴኛ መሆን (be ገጽ 197 አን. 4–ገጽ 198 አን. 4)
ቁ. 1፦ እንዴት መልስ መስጠት እንዳለብህ ተማር (be ገጽ 68 አን. 2–ገጽ 70 አን. 3)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 23:1-17
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስን እንድንመረምር የሚያደርጉን ምክንያቶች (rs ገጽ 57 አን. 1–ገጽ 58 አን. 4)
ቁ. 4፦ ታላቅነትን በተመለከተ ተገቢ የሆነው አመለካከት ምንድን ነው?
ነሐሴ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 24-27 መዝ. 16 (37)
የንግግር ባሕርይ፦ በወቅቱ የተነገረ ትክክለኛ ቃል (be ገጽ 199 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ደብዳቤ መጻፍ (be ገጽ 71-73)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 24:1-14
ቁ. 3፦ ሙሴ ለክርስቲያኖች ግሩም ምሳሌ የሚሆነው በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ አነሣሽነት የተጻፈ መሆኑን የሚያሳዩ ከኢሳይያስ እና ከኤርምያስ የተወሰዱ ማስረጃዎች (rs ገጽ 58 አን. 5–ገጽ 59 አን. 4)
ነሐሴ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 28-31 መዝ. 50 (123)
የንግግር ባሕርይ፦ ከቤተሰባችንና ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ዘዴኛ መሆን (be ገጽ 200 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ እድገት አድርግ (be ገጽ 74 አን. 1–ገጽ 75 አን. 3)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 28:1-16
ቁ. 3፦ ስለ ኢየሱስ የተነገሩ ትንቢቶች መፈጸማቸው መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ አነሣሽነት የተጻፈ መሆኑን ያረጋግጣል (rs ገጽ 60 አን. 1-2)
ቁ. 4፦ ‘መጥላት’ የሚለው ቃል በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የተሠራበት በምን መንገድ ነው?
ነሐሴ 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 32-34 መዝ. 96 (215)
የንግግር ባሕርይ፦ አዎንታዊና የምታበረታታ ሁን (be ገጽ 202 አን. 1–ገጽ 203 አን. 1)
ቁ. 1፦ ተሰጥዎህን ተጠቀምበት (be ገጽ 75 አን. 4–ገጽ 77 አን. 2)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 34:1-14
ቁ. 3፦ የአምላክ መንፈስ የሚረዳን እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ ጋር ይስማማል (rs ገጽ 61 አን. 1–ገጽ 62 አን. 4)
ነሐሴ 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 35-38 መዝ. 13 (33)
የንግግር ባሕርይ፦ አዎንታዊ አቀራረብ ይኑርህ (be ገጽ 203 አን. 2–ገጽ 204 አን. 1)
የቃል ክለሳ
መስ. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 39-41 መዝ. 35 (79)
የንግግር ባሕርይ፦ ከክርስቲያን ወንድሞችህ ጋር ስትጨዋወት (be ገጽ 204 አን. 2–ገጽ 205 አን. 4)
ቁ. 1፦ የአምላክን ቃል መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? (w05 4/15 ገጽ 15-16 አን. 3-6)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 40:1-15
ቁ. 3፦ የሰው ልጆች በእርግጥ አምላክን ማስደሰት ይችላሉ?
ቁ. 4፦ # መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ ለሚሰነዘሩ የተቃውሞ ሐሳቦች መልስ መስጠት (rs ገጽ 63 አን. 1–ገጽ 67 አን. 1)
መስ. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 42-45 መዝ. 34 (77)
የንግግር ባሕርይ፦ ነጥቡን ለማጉላት መደጋገም (be ገጽ 206 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ እርጅና “የክብር ዘውድ” ሲሆን (w05 1/15 ገጽ 8-9)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 43:1-12
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች የልደት ቀን የማያከብሩት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 67 አን. 2–ገጽ 69 አን. 2)
ቁ. 4፦ * ‘እንግዳ የሆነውን ድምፅ’ ለይተን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? (ዮሐ. 10:5)
መስ. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 46-48 መዝ. 72 (164)
የንግግር ባሕርይ፦ በአገልግሎት ላይ ስትሆንና ንግግር ስትሰጥ መደጋገም (be ገጽ 207 አን. 1–ገጽ 208 አን. 3)
ቁ. 1፦ ሕዝቅኤል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 7-8 አን. 29-33)
ቁ. 2፦ ሕዝቅኤል 47:1-14
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ከደም የሚርቁት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 69 አን. 3–ገጽ 71 አን. 1)
ቁ. 4፦ * ወላጆች ለልጆቻቸው ሊሰጧቸው የሚችሉት ከሁሉ የላቀ ስጦታ መንፈሳዊ ውርስ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
መስ. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዳንኤል 1-3 መዝ. 69 (160)
የንግግር ባሕርይ፦ ጭብጡን ማዳበር (be ገጽ 209 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የዳንኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi07 ገጽ 8-9 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ ዳንኤል 2:1-16
ቁ. 3፦ የ144,000ዎቹ ቁጥር ቃል በቃል የሚወሰደው ለምንድን ነው? (ራእይ 7:4)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ደም የማይወስዱት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 71 አን. 2–ገጽ 72 አን. 3)
ጥቅ. 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዳንኤል 4-6 መዝ. 8 (21)
የንግግር ባሕርይ፦ ተስማሚ ጭብጥ (be ገጽ 210 አን. 1–ገጽ 211 አን. 1፤ ገጽ 211 ሣጥን)
ቁ. 1፦ መቆጣት ሁልጊዜ ስህተት ሊሆን ይችላል? (w05 8/1 ገጽ 13-15)
ቁ. 2፦ ዳንኤል 4:1-17
ቁ. 3፦ የሜምፊቦስቴን ግሩም ባሕርያት መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ # ደም ስለ መውሰድ ለሚሰነዘሩ ሐሳቦች መልስ መስጠት (rs ገጽ 73 አን. 1–ገጽ 75 አን. 1)
ጥቅ. 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዳንኤል 7-9 መዝ. 14 (34)
የንግግር ባሕርይ፦ ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ (be ገጽ 212 አን. 1–ገጽ 213 አን. 1)
ቁ. 1፦ የይሖዋ “ቃል” ይጠብቅህ (w05 9/1 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ ዳንኤል 7:1-12
ቁ. 3፦ እንደገና መወለድ ሲባል ምን ማለት ነው? (rs ገጽ 75 አን. 2–ገጽ 76 አን. 6)
ቁ. 4፦ አዘውትሮ በመስክ አገልግሎት መካፈል ምን ልዩ ደስታ ያስገኛል?
ጥቅ. 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዳንኤል 10-12 መዝ. 76 (172)
የንግግር ባሕርይ፦ ዋና ዋና ነጥቦችህ አይብዙ (be ገጽ 213 አን. 2–ገጽ 214 አን. 5)
ቁ. 1፦ ዳንኤል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 9-10 አን. 19-23)
ቁ. 2፦ ዳንኤል 11:1-14
ቁ. 3፦ ትሕትና አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚረዳን እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ መዳን እንደገና በመወለድ ላይ የተመካ አይደለም (rs ገጽ 76 አን. 7–ገጽ 77 አን. 5)
ጥቅ. 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሆሴዕ 1-7 መዝ. 15 (35)
የንግግር ባሕርይ፦ በጉጉት ለማዳመጥ የሚጋብዝ መግቢያ (be ገጽ 215 አን. 1–ገጽ 216 አን. 4)
ቁ. 1፦ የሆሴዕ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ እና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 11-12 አን. 1-8, 14-17)
ቁ. 2፦ ሆሴዕ 5:1-15
ቁ. 3፦ # እንደገና ስለመወለድ ለሚሰነዘሩ አስተያየቶች ምላሽ መስጠት (rs ገጽ 78 አን. 1–ገጽ 79 አን. 1)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ትዕግሥት የሚያሳዩባቸው መንገዶች
ጥቅ. 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሆሴዕ 8-14 መዝ. 21 (46)
የንግግር ባሕርይ፦ በአገልግሎት ላይ ሰዎች በትኩረት እንዲያዳምጡን ማድረግ (be ገጽ 217 አን. 1-4)
የቃል ክለሳ
ኅዳር 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢዩኤል 1-3 መዝ. 73 (166)
የንግግር ባሕርይ፦ በመግቢያህ ላይ ርዕሰ ጉዳዩን ግልጽ ማድረግ (be ገጽ 217 አን. 5–ገጽ 219 አን. 1)
ቁ. 1፦ የኢዩኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ እና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 13-14 አን. 1-5, 12-14)
ቁ. 2፦ ኢዩኤል 2:1-14
ቁ. 3፦ “ፍጹም ፍቅር” ሲባል ምን ማለት ነው? (1 ዮሐ. 4:18)
ቁ. 4፦ ለቄስ መናዘዝ ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የለውም የሚባለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 79 አን. 2–ገጽ 80 አን. 8)
ኅዳር 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ አሞጽ 1-9 መዝ. 93 (211)
የንግግር ባሕርይ፦ ግቡን የሚመታ መደምደሚያ (be ገጽ 220 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የአሞጽ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ እና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 14-16 አን. 1-6, 13-17)
ቁ. 2፦ አሞጽ 2:1-16
ቁ. 3፦ ከራስ ተሞክሮ ከመማር የተሻለ ነገር አለ
ቁ. 4፦ በአምላክ ላይ ኃጢአት ስንሠራና ሰዎችን ስንበድል መናዘዝ (rs ገጽ 81 አን. 6–ገጽ 82 አን. 6)
ኅዳር 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ አብድዩ 1–ዮናስ 4 መዝ. 98 (220)
የንግግር ባሕርይ፦ ልታስብባቸው የሚገቡ ነጥቦች (be ገጽ 220 አን. 4–ገጽ 221 አን. 4)
ቁ. 1፦ የአብድዩና የዮናስ መጻሕፍት ማስተዋወቂያ እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 16-17 አን. 1-5, 10-14፤ ገጽ 17-19 አን. 1-4, 9-12)
ቁ. 2፦ ዮናስ 1:1-17
ቁ. 3፦ መንፈሳዊ ገነት በምድር ላይ ከምትቋቋመው ገነት መቅደም ያለበት ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ * ከባድ ኃጢአት የሠራ ሰው ለሽማግሌዎች መናዘዝ ያለበት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 82 አን. 7–ገጽ 83 አን. 2)
ኅዳር 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሚክያስ 1-7 መዝ. 66 (155)
የንግግር ባሕርይ፦ በአገልግሎት (be ገጽ 221 አን. 5–ገጽ 222 አን. 6)
ቁ. 1፦ የሚክያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ እና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 19-21 አን. 1-8, 16-19)
ቁ. 2፦ ሚክያስ 2:1-13
ቁ. 3፦ የዋኅ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?
ቁ. 4፦ በፍጥረት ማመን ምክንያታዊ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 83 አን. 3–ገጽ 85 አን. 1)
ታኅ. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ናሆም 1–ዕንባቆም 3 መዝ. 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ መረጃ ማስተላለፍ (be ገጽ 223 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ የናሆምና የዕንባቆም መጻሕፍት ማስተዋወቂያ እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 21-23 አን. 1-7, 11-12፤ ገጽ 23-24 አን. 1-5, 12-14)
ቁ. 2፦ ዕንባቆም 1:1-17
ቁ. 3፦ ስለ ፍጥረት የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ መረዳት (rs ገጽ 85 አን. 2–ገጽ 87 አን. 2)
ቁ. 4፦ ለዘላለም መኖር አሰልቺ የማይሆነው ለምንድን ነው?
ታኅ. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሶፎንያስ 1–ሐጌ 2 መዝ. 45 (106)
የንግግር ባሕርይ፦ ‘በታመነው ቃል መጽናት’ (be ገጽ 224 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ የሶፎንያስና የሐጌ መጻሕፍት ማስተዋወቂያ እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 25-26 አን. 1-6, 10-12፤ ገጽ 27-28 አን. 1-7, 13-16)
ቁ. 2፦ ሶፎንያስ 3:1-17
ቁ. 3፦ መስቀልን እንደ ቅዱስ ቆጥሮ ማክበር ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የለውም የምንለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 90 አን. 3–ገጽ 91 አን. 5)
ቁ. 4፦ * መንፈሳዊነት በትዳር ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?
ታኅ. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘካርያስ 1-8 መዝ. 92 (209)
የንግግር ባሕርይ፦ ትክክለኛ መረጃ መሆኑን ማረጋገጥ (be ገጽ 225 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የዘካርያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi07 ገጽ 28-29 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ ዘካርያስ 7:1-14
ቁ. 3፦ ኢየሱስ በተአምር ሲለወጥ የታየው ራእይ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ ከጥፋት ውኃ በፊት የነበሩት ሰዎች ዕድሜ የተቆጠረው ዛሬ እኛ በምንጠቀምበት ዓመት ነው? (rs ገጽ 93 አን. 4–ገጽ 94 አን. 1)
ታኅ. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘካርያስ 9-14 መዝ. 6 (13)
የንግግር ባሕርይ፦ በቀላሉ የሚገባ (be ገጽ 226 አን. 1–ገጽ 227 አን. 1)
ቁ. 1፦ ዘካርያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት እንዲሁም የሚልክያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi07 ገጽ 29-30 አን. 23-27፤ ገጽ 31-32 አን. 1-6, 13-17)
ቁ. 2፦ ዘካርያስ 10:1-12
ቁ. 3፦ የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክ መንግሥት የተቋቋመችው በ1914 ነው የሚሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 94 አን. 2–ገጽ 96 አን. 3)
ቁ. 4፦ ለሚያጋጥመን ስደት ራሳችንን ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?
ታኅ. 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሚልክያስ 1-4 መዝ. 4 (8)
የንግግር ባሕርይ፦ እንግዳ የሆኑ ቃላትን ትርጉም ማስረዳት (be ገጽ 227 አን. 2-5)
የቃል ክለሳ
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
* ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
# ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በጉባኤህ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች አመለካከት፣ ለሚሰጡህ ምላሽና ለሚገጥምህ ተቃውሞ ይበልጥ ተስማሚ የሆኑ ሐሳቦችን አቅርብ።