ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚረዱ ጥያቄዎች
አስተማሪ የተባለውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚያገለግሉ መመሪያዎች
ይህን መጽሐፍ በደንብ ለማጥናት መግቢያውን ጨምሮ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ ላሉት አንቀጾች ቁጥር ስጧቸው። አንድ ላይ የተደረጉት አንቀጾች በሙሉ አንድ ላይ መነበብ አለባቸው። ጥናቱ በሚከናወንበት ወቅት በምዕራፉ መጨረሻ ላይ ያሉት ጥቅሶች እንደ አስፈላጊነቱ ውይይት ሊደረግባቸው ይችላል።
ይህ መጽሐፍ በጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በሚጠናበት ጊዜ በእያንዳንዱ ሳምንት አንድ ምዕራፍ ይጠናል፤ መግቢያው እንደ መጀመሪያ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። መጽሐፉ በ49 የጥናት ሳምንታት ውስጥ ያልቃል።
ምዕራፍ 16 አንቀጽ 1-6
1. በወንድሙ ላይ ያለውን ቅሬታ ለኢየሱስ የተናገረው ሰው ችግሩ ምን ነበር?
2. ኢየሱስ በሰውየው አስተሳሰብ ላይ ያለው ችግር ምን እንደሆነ ለማሳየት የትኛውን ታሪክ ተናገረ? (ሉቃስ 12:16-21ን አንብብ)
አንቀጽ 7-13
3. ብዙ ልጆችና ትልልቅ ሰዎች እንደ ሀብታሙ ሰው የሆኑት እንዴት ነው?
4. ከቁሳዊ ነገሮች የበለጠ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድን ነው? ቢሆንም በዛሬው ጊዜ እንደ ሀብታሙ ሰው ያሉ ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ አስበልጠው የሚመለከቱት ነገር ምንድን ነው?
5. ኢየሱስ በተናገረው ታሪክ ላይ እንደተገለጸው ሀብታም ሰው መሆን የሌለብን ለምንድን ነው?
አንቀጽ 14-17
6. በአምላክ ዘንድ ሀብታም መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?
7. ኢየሱስ ምን ግሩም ምሳሌ ትቶልናል?
8. ኢየሱስ በአምላክ ዘንድ ሀብታም በመሆኑ ምን ጥቅም አግኝቷል?
ምዕራፍ 17 አንቀጽ 1-8
1. ደስተኛ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?
2. ይሖዋ ‘ደስተኛ አምላክ’ የተባለው ለምንድን ነው?
3. ለሌሎች ሰዎች ምን መስጠት እንችላለን?
አንቀጽ 9-12
4. ኢየሱስና ሐዋርያቱ ለሰዎች ምን መስጠት ችለዋል?
5. ጳውሎስና ሉቃስ ለሌሎች ሰዎች ምን ሰጥተዋል? ሊዲያም በበኩሏ መስጠት በመቻሏ የተደሰተችው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 13-16
6. መስጠትን በተመለከተ ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል? ለምንስ?
7. አንዲት ድሃ ሴት ያላትን ሁሉ በመስጠቷ ደስተኛ የሆነችው ለምንድን ነው?
8. ‘ሰጪዎች መሆን’ የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? እንዲህ የምናደርግ ከሆነስ ምን ውጤት ልናገኝ እንችላለን?
ምዕራፍ 18 አንቀጽ 1-5
1. ሌሎች ሰዎች ጥሩ ነገር ሲያደርጉልን ምን ማድረግ ይኖርብናል?
2. የሥጋ ደዌ ምንድን ነው? በኢየሱስ ዘመን የሥጋ ደዌ የያዛቸው ሰዎች ወደ ሌሎች እንዳይቀርቡ ይደረግ የነበረው ለምንድን ነው?
3. ኢየሱስ የሥጋ ደዌ ለያዛቸው ሰዎች ምን አመለካከት ነበረው?
አንቀጽ 6-12
4. ኢየሱስ እንዲፈውሳቸው የጠየቁትን የሥጋ ደዌ በሽተኞች ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው? ይህንንስ ያደረገው ለምንድን ነው?
5. የሥጋ ደዌ በሽተኞቹ ኢየሱስ ሊፈውሳቸው እንደሚችል እምነት እንደነበራቸው የሚያሳየው ምንድን ነው?
6. በሽተኞቹ ወደ ካህናት በመሄድ ላይ ሳሉ ምን ነገር ተፈጸመ?
7. ሳምራዊው ሰው ከሌሎቹ ዘጠኝ ሰዎች የተለየ የነበረው እንዴት ነው?
አንቀጽ 13-18
8. ተመልሶ ኢየሱስን ያመሰገነውን ሰው መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?
9. ጥሩ ነገር ያደረጉልንን ሰዎች ማመስገን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 19 አንቀጽ 1-5
1. ኢየሱስ ሰላም ፈጣሪ መሆንን በተመለከተ ምን ተናግሯል? ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ይህን ማድረግ ከባድ የሚሆነው ለምንድን ነው?
2. ሳምራውያን የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ በቀሩ ጊዜ ያዕቆብና ዮሐንስ ምን ማድረግ ፈልገው ነበር?
አንቀጽ 6-12
3. ምሳሌ 24:29 መበቀልን በተመለከተ ምን ይላል?
4. ኢየሱስ በማቴዎስ 5:39 ላይ የተናገረውን ሐሳብ መረዳት ያለብን እንዴት ነው?
5. አንድ ሰው ነገር ቢፈልገን ምን ማድረጋችን የተሻለ ነው? ለምንስ?
አንቀጽ 13-17
6. ምሳሌ 26:17 ምን ይላል? ይህስ በሌሎች ሰዎች ጸብ ውስጥ ጣልቃ ከመግባት ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?
7. ብዙ ጊዜ ሰዎች ጸብ ሲፈጠር ምን ያደርጋሉ? ሆኖም አንድ ክርስቲያን ምን ማድረግ ይኖርበታል? ለምንስ?
ምዕራፍ 20 አንቀጽ 1-7
1. ኢየሱስ ሁልጊዜ ቅድሚያ ማግኘት ስለሚፈልጉ ሰዎች ምን አመለካከት አለው?
2. ኢየሱስ ምን ታሪክ ተናገረ? ለምንስ?
3. ኢየሱስ የተናገረው ታሪክ ምን መልእክት ያስተላልፋል?
4. አንድ ሰው ቅድሚያ ማግኘት ወይም አንደኛ መሆን በሚፈልግበት ጊዜ በአብዛኛው ምን ሁኔታ ይፈጠራል?
አንቀጽ 8-15
5. የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ቅድሚያ ለማግኘት መፈለጋቸው ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዙ በነበረበት ወቅት በመካከላቸው ችግር እንዲፈጠር ምክንያት የሆነው እንዴት ነው?
6. ኢየሱስ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት ተናግሯል?
7. አንዳችን ሌላውን እንደ ባሪያ ማገልገል የምንችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 21 አንቀጽ 1-10
1. ጉራ መንዛት ማለት ምን ማለት ነው? እንዲህ ስለሚያደርጉ ሰዎችስ ምን ይሰማሃል?
2. ኢየሱስ ስለ አንድ ፈሪሳዊና ስለ አንድ ቀረጥ ሰብሳቢ የሚገልጽ ምን ታሪክ ተናግሯል?
3. ኢየሱስ በዚህ ታሪክ አማካኝነት ሊያስተላልፍ የፈለገው ትምህርት ምንድን ነው?
አንቀጽ 11-19
4. ጴጥሮስ በጉራ የተናገረው መቼ ነው? በዛሬው ጊዜስ ብዙ ሰዎች ጉራ የሚነዙት እንዴት ነው?
5. አንድ ሰው ስለ ራሱ ጉራ የሚነዛበት በቂ ምክንያት የሌለው ለምንድን ነው?
6. በኩራት መናገር ያለብን ስለ ማን ብቻ ነው? ለምንስ?
ምዕራፍ 22 አንቀጽ 1-6
1. ኢየሱስ ማቴዎስ 5:37 ላይ ያለውን ሐሳብ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር?
2. ኢየሱስ ከሞተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምን ነገሮች ተፈጸሙ?
አንቀጽ 7-13
3. ሐናንያና ሰጲራ የሠሩት ስህተት ምን ነበር? ምንስ ደረሰባቸው?
4. የሐናንያና የሰጲራ ታሪክ ምን ያስተምረናል?
አንቀጽ 14-18
5. መዋሸት ስህተት የሆነው ለምንድን ነው?
6. ለመዋሸት ይበልጥ ልንፈተን የምንችለው መቼ ነው?
7. መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ እንዳንዋሽ የሚያስጠነቅቀን እንዴት ነው?
ምዕራፍ 23 አንቀጽ 1-8
1. ሰዎች አንድ ሽባ ሰው ይዘው ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ እሱ የት ነበር?
2. ይህን ሽባ ሰው ኢየሱስ ፊት ማቅረብ ከባድ የነበረው ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የቻሉትስ እንዴት ነው?
3. ኢየሱስ ይህን ሽባ ሰው ለመርዳት ምን አደረገ?
አንቀጽ 9-14
4. ኢየሱስ ሽባውን ሰው በመፈወስ ከፈጸመው ተአምር ምን ትምህርት እናገኛለን?
5. ሁሉም ሰው ኃጢአተኛ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?
አንቀጽ 15-18
6. አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይበልጥ የሚታመሙት ለምንድን ነው?
7. ኃጢአታችን ሊወገድ የሚችልበት ብቸኛ መንገድ ምንድን ነው? ኃጢአታችን ሙሉ በሙሉ ሲወገድ ምን ዓይነት ጤንነት ይኖረናል?
ምዕራፍ 24 አንቀጽ 1-13
1. አንድ ሰው እንዲሰርቅ የሚያደርገው ምን ሊሆን ይችላል?
2. የመጀመሪያው ሌባ ማነው? የሰረቀውስ ምንድን ነው?
3. ሁላችንም ልናስወግደው የሚገባ መጥፎ ምኞት ምንድን ነው?
4. አስቆሮቱ ይሁዳ የነበረው መጥፎ ምኞት የትኞቹን መጥፎ ነገሮች እንዲሠራ ገፋፍቶታል?
አንቀጽ 14-21
5. አካን ሌባ የሆነው እንዴት ነው?
6. ዳዊትም ሆነ ልጁ አቤሴሎም የራሳቸው ያልሆነውን ነገር የሰረቁት እንዴት ነው?
7. አምላክ ማንኛውንም ዓይነት ስርቆት በተመለከተ ምን ይሰማዋል?
8. ሌባ እንዳንሆን የሚረዳን ምንድን ነው?
ምዕራፍ 25 አንቀጽ 1-8
1. ሁላችንም አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ነገር የምንሠራው ለምንድን ነው?
2. ሳኦል ምን መጥፎ ነገር ሠርቷል? ለምንስ?
አንቀጽ 9-15
3. ሳኦል ክርስቲያኖችን ለመያዝ እየሄደ ሳለ ምን አጋጠመው?
4. በኋላ ሳኦል ምን ሆነ? ምን ጥሩ ነገርስ አደረገ?
5. ሰዎች መጥፎ ነገር እንዲሠሩ ለማድረግ እየጣረ ያለው ማነው?
አንቀጽ 16-20
6. ሁላችንም ምን ከባድ ትግል አለብን?
7. ኢየሱስ ቀደም ሲል መጥፎ ነገር ይሠሩ የነበሩ ሰዎችን የወደዳቸው ለምንድን ነው?
8. መጽሐፍ ቅዱስ እየሠራን ያለነው ነገር መጥፎ እንደሆነ የሚገልጽ ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብናል?
ምዕራፍ 26 አንቀጽ 1-9
1. ሳኦል የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ከሆነ በኋላ ምን ደርሶበታል?
2. ሰዎች የተቆጡት ኢየሱስ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሲያስተምር ነው?
3. ሰዎች ኢየሱስን ምን ሊያደርጉት ሞክረው ነበር? ሆኖም ይህ ለእነሱ መስበኩን እንዲያቆም አድርጎታል?
አንቀጽ 10-14
4. ኢየሱስ በሰንበት ቀን ምን ተአምር ፈጸመ?
5. ኢየሱስ በፈጸመው ተአምር የተደሰተው ማነው? ያልተደሰቱትስ እነማን ነበሩ?
6. ሁላችንም ምን ውሳኔ ማድረግ ይኖርብናል?
7. ጥሩ የሆነውን ነገር ማድረግ እንዲከብደን የሚያደርገው ማነው?
አንቀጽ 15-18
8. የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት የሚጠላው ዓለም እነማንን ያጠቃልላል?
9. ጥሩ ነገር ማድረግ በጣም ከባድ የሆነው ለምንድን ነው?
10. አምላክ የሚፈልገውን እንድናደርግ ሊያነሳሳን የሚገባው የትኛው ተስፋ ነው?
ምዕራፍ 27 አንቀጽ 1-5
1. ሰዎች ጳውሎስና በርናባስን ሊያመልኳቸው የፈለጉት ለምንድን ነው? ሆኖም ጳውሎስና በርናባስ ምን አሉ? ምንስ አደረጉ?
2. አብዛኞቹ ሰዎች የሚያመልኩት የትኞቹን አማልክት ነው?
3. የዚህ ዓለም አምላክ ማነው? ሰዎችንስ ምን እንዲያደርጉ ለመገፋፋት ይሞክራል?
አንቀጽ 6-13
4. ንጉሥ ናቡከደነፆር ሁሉም ሰው ምን እንዲያደርግ አዘዘ? ሆኖም ሦስት ዕብራውያን ወጣቶች የታዘዙትን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆኑት ለምንድን ነው?
5. ይሖዋ ምን ተአምር ፈጸመ? ይህስ ንጉሥ ናቡከደነፆርን ምን እንዲያደርግ አነሳሳው?
አንቀጽ 14-15
6. በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሚያመልኳቸውን ምስሎች ወይም ጣዖቶች መጥቀስ ትችላለህ?
7. ሦስቱ ዕብራውያን በአሁኑ ጊዜ ቢኖሩ ኖሮ በዘመናችን ስለሚመለኩት ጣዖቶች ምን አመለካከት የሚኖራቸው ይመስልሃል?
ምዕራፍ 28 አንቀጽ 1-5
1. አንዳንድ ጊዜ ማንን መታዘዝ እንዳለብን ማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው?
2. መጽሐፍ ቅዱስ ለልጆች ምን መመሪያ ይሰጣል?
3. ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ንጉሥ ናቡከደነፆር ለሠራው ምስል ለመስገድ ፈቃደኛ ያልሆኑት ለምንድን ነው?
4. ሐዋርያት ማንን መታዘዝ እንዳለባቸው ለመወሰን የሚያስቸግር ሁኔታ ባጋጠማቸው ጊዜ ምን ውሳኔ አድርገዋል?
አንቀጽ 6-10
5. በኢየሱስ ዘመን ይገዛ የነበረው መንግሥት ማነው? አብዛኛውን ጊዜስ መንግሥታት ምን ጥሩ ነገሮች ያደርጋሉ?
6. ኢየሱስ ግብር ስለመክፈል ምን ብሏል? የሰጠውስ መመሪያ ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 11-18
7. ልጆችም ሆኑ ትልልቅ ሰዎች የመንግሥትን ሕግና መንግሥት የወከላቸውን ሰዎች መታዘዝ ያለባቸው ለምንድን ነው?
8. እውነተኛ ክርስቲያኖች አንዳንድ ሕጎችን የማይታዘዙት ምን ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ ነው? ለምንስ?
ምዕራፍ 29 አንቀጽ 1-10
1. አምላክ ግብዣ ማድረግን እንደማይከለክል የሚያሳየው ምንድን ነው? ሆኖም ምን ዓይነት ግብዣዎች በእሱ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም?
2. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ የትኞቹ ሁለት የልደት ቀን ግብዣዎች ይናገራል?
3. በእነዚህ ግብዣዎች ላይ ምን እንደተፈጸመ ግለጽ።
አንቀጽ 11-15
4. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልደት ቀን ግብዣዎች ምን እያስተማረን ያለ ይመስልሃል?
5. የኢየሱስን ልደት ለማክበር የተመረጠው ቀን የትኛው ነው? ሆኖም ኢየሱስ የተወለደው በዚህ ጊዜ ሊሆን የማይችለው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 16-17
6. ሰዎች የገናን በዓል የሚያከብሩት ለምንድን ነው?
7. የምናዘጋጀው ግብዣ አምላክን የሚያስደስት እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? (ዮሐንስ 17:16፤ 2 ቆሮንቶስ 6:14፤ 1 ጴጥሮስ 4:3)
ምዕራፍ 30 አንቀጽ 1-9
1. ጴጥሮስም ሆነ ሌሎቹ ሐዋርያት የፈሩት ለምን ነበር?
2. ጴጥሮስ ኢየሱስን እንዲክድ ያደረጉት ሁኔታዎች ምን ነበሩ?
አንቀጽ 10-16
3. ጴጥሮስ ኢየሱስን አላውቀውም ብሎ የካደው ስንት ጊዜ ነው? ይህስ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?
4. ጴጥሮስ የደረሰበት ዓይነት ሁኔታ ሊያጋጥመን የሚችለው እንዴት ነው?
5. እንዳንፈራና ጴጥሮስ የደረሰበት ዓይነት ሐዘን እንዳያጋጥመን ምን ሊረዳን ይችላል?
ምዕራፍ 31 አንቀጽ 1-7
1. መጽሐፍ ቅዱስ ላዘኑና የብቸኝነት ስሜት ለሚሰማቸው ምን ማጽናኛ ይሰጣል?
2. ኢየሱስ ሥቃይ ቢደርስበትም እንኳ ምን ያውቅ ነበር?
3. እኛ እንደ በግ የሆንነው እንዴት ነው? ኢየሱስ ስለ ጠፋች በግ የሚገልጽ ምን ታሪክ ተናግሯል?
አንቀጽ 8-12
4. ኢየሱስ በተናገረው ታሪክ ላይ እንዳለው እረኛ የሆነው ማነው? የማይታይ መሆኑስ ለውጥ የማያመጣው ለምንድን ነው?
5. መዝሙር 23 ይሖዋ እንደሚወደን የሚያሳየው እንዴት ነው?
አንቀጽ 13-15
6. የአምላክ በጎች መፍራት የሌለባቸው ለምንድን ነው?
7. ይሖዋ ታማኝ ስለሆኑት ሰዎች ምን ይሰማዋል? ይህስ እኛ ስለ እሱ ምን እንዲሰማን ሊያደርግ ይገባል?