ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 12 (32)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 17-20
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 17:1-17
ቁ. 2፦ የሰው ልጆች ትክክለኛ መስተዳድር ማቋቋም ያልቻሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 152 አን. 2 እስከ ገጽ 153 አን. 6)
ቁ. 3፦ አምላክ ስም አለው (lr ምዕ. 4)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 20 (45)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የመጽሔቶቹን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ አድማጮች በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ሊማርኩ ይችላሉ የሚሏቸውን ርዕሶች እንዲናገሩ ጋብዝ። እንዲህ ያሉበትን ምክንያት እንዲናገሩም ጠይቃቸው። ከተጠቀሱት ርዕሶች ውስጥ አንዳንዶቹን በማንሳት፣ ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄዎችን ለመጠቀም እንዳሰቡና መጽሔቶቹን ከማበርከታቸው በፊት ከርዕሱ ውስጥ የትኛውን ጥቅስ ለማንበብ እንደመረጡ አድማጮችን ጠይቃቸው። ክፍሉን ከመደምደምህ በፊት በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን የናሙና መግቢያዎች ወይም አድማጮች የጠቀሷቸውን ሌሎች አቀራረቦች በመጠቀም እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “ምን አማራጮች እንዳሉህ ታውቃለህ?”* በሽማግሌ የሚቀርብ። በመደምደሚያህ ላይ የመጨረሻውን አንቀጽ አንብብ።
ነመዝሙር 80 (180)
[የግርጌ ማስታወሻ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።