ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚረዱ ጥያቄዎች
አስተማሪ የተባለውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚያገለግሉ መመሪያዎች
ይህን መጽሐፍ በደንብ ለማጥናት መግቢያውን ጨምሮ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ ላሉት አንቀጾች ቁጥር ስጧቸው። አንድ ላይ የተደረጉት አንቀጾች በሙሉ አንድ ላይ መነበብ አለባቸው። ጥናቱ በሚከናወንበት ወቅት በምዕራፉ መጨረሻ ላይ ያሉት ጥቅሶች እንደ አስፈላጊነቱ ውይይት ሊደረግባቸው ይችላል።
ይህ መጽሐፍ በጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በሚጠናበት ጊዜ በእያንዳንዱ ሳምንት አንድ ምዕራፍ ይጠናል፤ መግቢያው እንደ መጀመሪያ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። መጽሐፉ በ49 የጥናት ሳምንታት ውስጥ ያልቃል።
ምዕራፍ 32 አንቀጽ 1-9
1. ይሖዋ የወፍ ጫጩቶች ጥበቃ እንዲያገኙ የሚያደርገው እንዴት ነው?
2. ኢየሱስ ልዩ ጥበቃ ያስፈለገው መቼ ነው? መጠበቅ ያስፈለገውስ ከማን ነው?
3. ይሖዋ ልጁ እንዳይገደል ጥበቃ ያደረገለት እንዴት ነው?
አንቀጽ 10-13
4. በአሁኑ ጊዜ ኢየሱስ ሕፃን ሳለ ከነበረበት ሁኔታ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ላይ ያሉት እነማን ናቸው? ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውስ ለምንድን ነው?
5. ሰይጣንና አጋንንቱ ልጆችን ለመጉዳት ጥረት እያደረጉ ያሉት እንዴት ነው?
6. አግባብ ባለው መንገድ የጾታ ግንኙነት መፈጸም የሚችሉት እነማን ብቻ ናቸው? አምላክ ምን ዓይነት የጾታ ግንኙነቶችን ያወግዛል?
አንቀጽ 14-17
7. ከልጆች ጋር የጾታ ግንኙነት ለማድረግ የሚሞክሩት እነማን ናቸው? ልጆች እንዲተባበሯቸው ለማድረግ የሚሞክሩትስ እንዴት ነው?
8. ልጆች መጥፎ ነገር ለማድረግ ከሚሞክሩ ሰዎች ራሳቸውን መጠበቅ የሚችሉት እንዴት ነው?
9. ወላጆች ልጆቻቸውን ለመጠበቅ ምን ማድረግ ይችላሉ?
ምዕራፍ 33 አንቀጽ 1-8
1. በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች ኢየሱስን እንዴት አድርገው ያስቡታል? ሆኖም በአሁኑ ጊዜ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?
2. ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ኃይል እንዳለው ያሳየው እንዴት ነው?
3. የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መፍራት ያልነበረባቸው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 9-14
4. በሌላ ወቅት ማዕበል ሲከሰት ምን ሁኔታ ተፈጸመ?
5. ኢየሱስ በዚያ ወቅት እነዚህን አስደናቂ ተአምራት የፈጸመው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 15-16
6. ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ ኃይሉን የሚጠቀምበት እንዴት ነው?
7. ወደፊት ምን ዓይነት ተአምራት ይፈጸማሉ ብለን መጠበቅ እንችላለን?
ምዕራፍ 34 አንቀጽ 1-4
1. አንድ ሰው ሲሞት ምን እንደሚሆን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
2. ኢየሱስ ስለ አልዓዛር የተናገረው ነገር ስለ ሞት ምን ያስገነዝበናል?
አንቀጽ 5-10
3. ኢየሱስ አልዓዛር ወደተቀበረበት ዋሻ በሄደ ጊዜ ምን አደረገ?
4. ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” ብሎ ሲናገር ምን ተፈጸመ?
አንቀጽ 11-16
5. አንድ ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?
6. አልዓዛር ወደ ሰማይ እንዳልሄደ እንዴት እናውቃለን?
7. አንድ ሰው ሞተ ማለት ነፍስ ሞተ ማለት እንደሆነ እንዴት እናውቃለን?
አንቀጽ 17-19
8. በአካባቢህ ያሉ ሰዎች ስለ ሞት ምን ብለው ያምናሉ?
9. የአልዓዛር ታሪክ ሙታንን እንዳንፈራ የሚረዳን እንዴት ነው?
ምዕራፍ 35 አንቀጽ 1-4
1. ይሖዋ ሙታንን ማስነሳት እንደሚፈልግና ኢየሱስም ተመሳሳይ ፍላጎት እንዳለው እንዴት እናውቃለን?
2. ኢየሱስ ከመወለዱ ከረጅም ጊዜ በፊት ሁለት ልጆች ከሞት የተነሡት እንዴት ነው?
3. ብንሞት ይሖዋ እንደሚያስታውሰን እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 5-11
4. የኢያኢሮስ ልጅ ምን ሆና ነበር? ኢየሱስስ ምን አደረገ?
5. ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?
አንቀጽ 12-18
6. የመበለቷ ልጅ ከሞት መነሣቱ ኢየሱስ ሙታንን ማስነሳት እንደሚፈልግ የሚያሳየው እንዴት ነው?
7. ከሞት የተነሳው ልጅ እናት ምን የተሰማት ይመስልሃል? ሌሎች ሰዎችስ ተመሳሳይ ስሜት የሚሰማቸው መቼ ነው?
ምዕራፍ 36 አንቀጽ 1-6
1. ከሞት ስለተነሱ ሰዎች የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ምን ያሳያሉ?
2. ዓመጸኞች ከሞት የሚነሱት ለምንድን ነው? የሚኖሩትስ የት ነው?
3. በምድር ላይ ትንሣኤ የሚከናወነው መቼ ነው? በዚያን ጊዜስ ምን ይከናወናል?
አንቀጽ 7-11
4. ኢየሱስ በገነት ከእሱ ጋር አብሮት እንደሚሆን ለወንጀለኛው ከገባው ቃል ምን ትምህርት እናገኛለን?
5. ኢየሱስ በገነት ከወንጀለኛው ጋር የሚሆነው እንዴት ነው?
6. ኢየሱስ ቀደም ሲል ወንጀለኛ የነበረን ሰው በገነት እንዲኖር የሚፈቅድለት ለምንድን ነው?
አንቀጽ 12-17
7. ትንሣኤ የሚያገኙ ሁሉ በምድር ላይ ይኖራሉ ማለት እንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን?
8. “በመጀመሪያው ትንሣኤ” የሚነሱት ስንት ናቸው? ምን ሥራስ ያከናውናሉ?
9. ገነት በሆነች ምድር ላይ መኖር አስደሳች የሚሆነው ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 37 አንቀጽ 1-7
1. አምላክ ምን ልዩ ስጦታ ሰጥቶናል?
2. ሁላችንም አዲስ አባት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?
3. ኢየሱስ አባታችንና አዳኛችን ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
4. ቤዛው ምንድን ነው? የሚያስፈልገንስ ለምንድን ነው?
አንቀጽ 8-15
5. ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የተገናኘው የትኛውን በዓል ለማክበር ነው?
6. ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በፋሲካ በዓል ምትክ የትኛውን በዓል አቋቋመ?
7. ኢየሱስ በዚህ አዲስ በዓል ላይ ምሳሌ ሆነው የሚያገለግሉ ምን ነገሮችን ተጠቀመ? እነዚህስ ነገሮች ምንን ይወክላሉ?
8. አዲሱ በዓል ምን እንድናስታውስ ይረዳናል?
አንቀጽ 16-18
9. በመታሰቢያው በዓል ላይ ስንገኝ ስለ ምን ነገር ማሰብ ይኖርብናል?
10. ቂጣውን መብላትና ወይኑን መጠጣት ያለባቸው እነማን ናቸው? ለምንስ?
11. ቂጣውን የማይበሉና ወይኑን የማይጠጡ ሰዎችም በበዓሉ ላይ መገኘት ያለባቸው ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 38 አንቀጽ 1-5
1. ኢየሱስ የሚያድነን ከምንድን ነው?
2. ኢየሱስ የሞተው ለማን ነው?
3. አምላክ በምድር ላይ ላሉ ሰዎች ምን ዓይነት ስሜት አለው?
አንቀጽ 6-12
4. ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ምን ሁኔታ አጋጠመው?
5. በቀጣዩ ቀን ምን እንደተከናወነ ግለጽ።
6. ኢየሱስ ከአዳም የተለየ የሆነው እንዴት ነው?
አንቀጽ 13-16
7. ጳውሎስ ክርስቶስ ላሳየው ፍቅር አድናቆት እንዳለው ያሳየው እንዴት ነው?
8. ኢየሱስን እንድንወደው የሚያደርገን ጠንካራ ምክንያት ምንድን ነው?
9. የምንኖረው ክርስቶስን ለማስደሰት እንደሆነ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 39 አንቀጽ 1-4
1. ይሖዋ፣ ኢየሱስ ሲገደል ምን የተሰማው ይመስልሃል?
2. ኢየሱስ ስለ ምን ነገር እርግጠኛ ነበር?
3. ኢየሱስ ከሞት የተነሳው ከየት ነው? ሞቶ የቆየውስ ለምን ያህል ጊዜ ነው?
አንቀጽ 5-13
4. ኢየሱስ በሞተበት ዕለት የተከናወነውን ነገር ግለጽ።
5. ኢየሱስ የተነሳው ምን ዓይነት አካል ይዞ ነው? ከዚያ በኋላ ሰዎች ሊያዩት የቻሉትስ እንዴት ነው?
6. ኢየሱስ ከሞት በተነሳበት ዕለት ምን ነገሮች ተፈጽመዋል?
አንቀጽ 14-17
7. ኢየሱስ ሥጋዊ አካል ለብሶ የታየው ለምን ያህል ጊዜ ነው? ከዚያስ በኋላ ምን ሆነ?
8. በአሁኑ ጊዜ አብዛኞቹ ሰዎች ኢየሱስ ከሞት የተነሳበትን ጊዜ የሚያከብሩት እንዴት ነው? ሆኖም እኛ እንደ ቀድሞዎቹ የኢየሱስ ተከታዮች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 40 አንቀጽ 1-3
1. አምላክ ከእኛ ምን አይፈልግም? ሆኖም ምን ልናደርግለት እንችላለን?
2. ይሖዋ እሱ የሚፈልገውን ነገር ብቻ እንድናደርግ እንደ ማሽን አድርጎ ያልፈጠረን ለምንድን ነው?
አንቀጽ 4-7
3. አምላክ የእሱን ፈቃድ ስናደርግ ምን ይሰማዋል?
4. አምላክን ለማገልገልም ሆነ ላለማገልገል የምናደርገው ምርጫ ለይሖዋም ሆነ ለሰይጣን ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ጉዳይ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 8-15
5. ሰይጣን ኢዮብን ምን አደረገው?
6. ኢዮብ በታማኝነት በመጽናቱ ይሖዋ ምን የተሰማው ይመስልሃል?
7. ኢየሱስ ምን ምሳሌ ትቶልናል? እሱን መኮረጅ የምንችለውስ እንዴት ነው?
ምዕራፍ 41 አንቀጽ 1-7
1. በአንድ ወቅት የኢየሱስ ቤተሰቦች የተጨነቁት ለምን ነበር?
2. ኢየሱስ ልጅ እያለ ወላጆቹንም ሆነ አምላክን የሚያስደስት ምን ነገር ያደርግ ነበር?
አንቀጽ 8-12
3. በአሁኑ ጊዜ አንድ ልጅ አምላክን የሚያስደስት ምን ነገር ሊያደርግ ይችላል?
4. የአምላክ ሕዝቦች እነማን እንደሆኑ ለይተን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
አንቀጽ 13-18
5. የጢሞቴዎስ ምሳሌ ልጆችን ሊረዳቸው የሚችለው እንዴት ነው?
6. ከእስራኤላዊቷ ልጅ ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?
7. ልጆች ምን ዓይነት ግብ ቢያወጡ ጥሩ ነው?
ምዕራፍ 42 አንቀጽ 1-6
1. መዝናናት ስህተት እንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን?
2. መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ምን ሥራ እንደተማረ ይናገራል? በዚህ ሞያ የተዋጣለት ነበር ብለህ እንድታስብ የሚያደርግህስ ምንድን ነው?
3. ኢየሱስ ሥራ መሥራቱ የጠቀመው እንዴት ነው? እኛስ ሥራ መሥራታችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?
አንቀጽ 7-13
4. ኢየሱስ ደስተኛ ሰው የነበረው ለምንድን ነው?
5. ኢየሱስ በምድር ላይ ያከናወነው ልዩ ሥራ ምን ነበር? ይህን ሥራ በመሥራቱስ ምን ተሰምቶት ነበር?
6. በአሁኑ ጊዜ ልጆች ምን ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ? ይህስ ቤተሰባቸውን ሊጠቅም የሚችለው ለምንድን ነው?
አንቀጽ 14-16
7. በትምህርት ቤት የሚሰጡትን ሥራዎች መሥራት ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
8. ሥራ ከመሥራት ወደኋላ ማለት የሌለብን ለምንድን ነው?
9. ሥራን በተመለከተ የትኛውን አስፈላጊ ጥያቄ ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል?
ምዕራፍ 43 አንቀጽ 1-7
1. ስለ ኢየሱስ ሥጋዊ ወንድሞችና እህቶች ምን የምናውቀው ነገር አለ?
2. ኢየሱስ እናቴና ወንድሞቼ ያላቸው እነማንን ነው? እንዲህ ሲልስ ምን ማለቱ ነበር?
3. የኢየሱስ ቤተሰቦች መጀመሪያ ላይ ምን ዓይነት ጠባይ አሳይተውት ሊሆን ይችላል?
አንቀጽ 8-14
4. መጽሐፍ ቅዱስ ወንድሞቻቸውን ይጠሉ የነበሩትን የእነማንን ምሳሌ ይጠቅሳል?
5. ከቃየንና አቤል ታሪክ ልንማረው የሚገባን ትምህርት ምንድን ነው?
አንቀጽ 15-18
6. ፍቅር ምንድን ነው? ፍቅር ማሳየታችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
7. ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እንደምንወድ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 44 አንቀጽ 1-5
1. እንደ አብርሃም የአምላክ ወዳጅ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
2. ኢየሱስ ወዳጆቹ እንዲሆኑ የሚፈልገው ምን ዓይነት ሰዎችን ነበር?
3. ከኢየሱስ የቅርብ ጓደኞች መካከል እነማን ይገኙበታል?
አንቀጽ 6-10
4. ኢየሱስ ሁሉም ዓይነት ሰዎች ቤት ይሄድ የነበረው ለምንድን ነው?
5. ዘኬዎስ ማን ነበር? የኢየሱስ ወዳጅ የሆነውስ እንዴት ነው?
አንቀጽ 11-15
6. ወዳጆቻችን ያልሆኑ ሰዎች ቤት የምንሄደው ለምንድን ነው?
7. የቅርብ ጓደኞቻችን ልናደርጋቸው የሚገባን እነማንን ነው?
8. አንድ ሰው ጥሩ ጓደኛ መሆን እንደሚችልና እንደማይችል ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
9. ጓደኞቻችን በእኛ ሕይወት ላይ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉት እንዴት ነው?
ምዕራፍ 45 አንቀጽ 1-8
1. የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ስለ ገዥውስ ምን የምናውቀው ነገር አለ?
2. በኢየሱስ ዘመን የአምላክ መንግሥት ቀርቧል የተባለው ከምን አንጻር ነው?
3. ኢየሱስ በምድር ላይ እያለ ምን ጠቃሚ ሥራ አከናውኗል? ይህን ሥራ ሲያከናውንስ እነማን ረድተውታል?
አንቀጽ 9-14
4. ኢየሱስ ንጉሣቸው እንዲሆን የፈለጉት እነማን ናቸው? ያልፈለጉትስ እነማን ነበሩ?
5. ኢየሱስን ለመግደል የፈለጉት እነማን ናቸው? ሕዝቡንስ ያነሳሱት እንዴት ነው?
6. በአሁኑ ጊዜ ያሉ ሰዎች ለኢየሱስ ምን አመለካከት አላቸው?
አንቀጽ 15-20
7. አምላክን እንደምንወደው እንዴት ማሳየት እንችላለን?
8. ኢየሱስ መጠመቁ ምን ያሳያል? አምላክ ኢየሱስ በመጠመቁ እንደተደሰተ የገለጸውስ እንዴት ነው?
9. እኛም መጠመቅ ያለብን ለምንድን ነው? ከዚያስ በኋላ የትኛውን አስፈላጊ ሥራ ማከናወናችንን መቀጠል ይኖርብናል?
ምዕራፍ 46 አንቀጽ 1-11
1. መጽሐፍ ቅዱስ ‘ዓለም በማለፍ ላይ ነው’ ሲል ምን ማለቱ ነው?
2. የጥፋት ውኃው ከመምጣቱ በፊት ሰዎች ምን ያደርጉ ነበር? ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ ማወቅ እንዳለብን የተናገረውስ ለምንድን ነው?
3. አምላክ ለኖኅ ምን መመሪያዎች ሰጥቶት ነበር? የጥፋት ውኃው በመጣ ጊዜስ ምን ተከሰተ?
አንቀጽ 12-19
4. የጥፋት ውኃው ከመምጣቱ በፊት የነበሩት ሰዎች ይፈጽሙት ከነበረው ድርጊት ምን ልንማር እንችላለን?
5. አምላክ ክፉ ሰዎችን ለማጥፋት በምን ይጠቀማል? የሚያጠፋቸውስ ለምንድን ነው?
6. አርማጌዶን ምንድን ነው? በአርማጌዶን ግንባር ቀደሙን ሚና የሚጫወተውስ ማን ነው?
ምዕራፍ 47 አንቀጽ 1-11
1. ሰዎች ኢየሱስ እንደተመለሰና በሰማይ መግዛት እንደጀመረ ማወቅ የሚችሉት እንዴት ነው?
2. ኢየሱስ ስለ በለስ ዛፍ የተናገረው ምን ለማስተማር ፈልጎ ነው?
3. ኢየሱስ የጠቀሳቸው በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸሙ ያሉት የምልክቱ ገጽታዎች ምንድን ናቸው?
አንቀጽ 12-16
4. ኢየሱስ የሰጠው ምልክት ምን ትርጉም አለው?
5. ኢየሱስ በክረምት ወቅት ለመሸሽ ስለ መሞከር የተናገረው ምን ለማስተማር ፈልጎ ነው?
ምዕራፍ 48 አንቀጽ 1-8
1. “አዲስ ሰማያት” እና “አዲስ ምድር” ሲባል ምን ማለት ነው?
2. ጥቅሶቹንና ሥዕሎቹን በመጠቀም አምላክ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ ምን ዓይነት ሕይወት እንደሚኖር ግለጽ።
አንቀጽ 9-15
3. የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንድንችል የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት መቅሰማችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
4. አምላክ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር የምንፈልግ ከሆነ ከእውቀት በተጨማሪ ምን ያስፈልገናል?
5. ይህ መጽሐፍ የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?