መጋቢት 23 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 34 (77)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 47-50
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 48:1-16
ቁ. 2፦ ዲያብሎስን ልንፈራው ይገባል?
ቁ. 3፦ ከአምላክ መላእክት የሚገኝ እርዳታ (lr ምዕ. 11)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 4 (8)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የመጽሔቶቹን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ አድማጮች በክልላቸው ውስጥ የሚያገኟቸውን ሰዎች በየትኞቹ ርዕሶች ተጠቅመው ሊያነጋግሩ እንዳሰቡ እንዲናገሩ ጋብዝ። እንዲህ ያሉበትን ምክንያት እንዲናገሩም ጠይቃቸው። ርዕሶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄዎች ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ ይቻላል? እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ የምታነጋግረውን ሰው በትኩረት በማዳመጥና አመለካከቱን ግምት ውስጥ በማስገባት አክብሮት እንዳለህ አሳይ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 186-187 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። እዚህ ላይ ያለውን ምክር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ቀጥሎም የአስፋፊው አቀራረብ ውጤታማ የሆነበትን ምክንያት እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 41 (89)