የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ጥር 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 4 (8)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም ጥር 22 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚካሄደው ውይይት ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለውን የቪዲዮ ፊልም ተመልክተው እንዲመጡ አበረታታ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የታኅሣሥ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “ሥራ አለብኝ” ለሚል ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 19-20ን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር ከተባለው ቡክሌት ጥቅም ማግኘት። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2007 በተባለው ቡክሌት መቅድም ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሁላችንም በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎች መድበን የዕለቱን ጥቅስና በዚያ ላይ የተሰጠውን ሐሳብ ማንበባችን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተናገር። የዕለቱን ጥቅስ ስለሚያነቡበት ፕሮግራምና እንዲህ ማድረጋቸው ያስገኘላቸውን ጥቅም የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ። በ2007 የዓመት ጥቅስ ላይ አጠር ያለ ሐሳብ በመስጠት ደምድም።
20 ደቂቃ:- ለእያንዳንዱ ሰው ምሥራቹን ማድረስ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 92 ጀምሮ በገጽ 102 ላይ እስከሚገኘው ንዑስ ርዕስ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 (114)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ወደኋላ እንድትል የሚያደርግህ ነገር ይኖር ይሆን? በሚያዝያ 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13-15 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
25 ደቂቃ:- የሠርጋችሁ ቀን የሚያስደስትና የሚያስከብር እንዲሆን ማድረግ። በጥቅምት 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-31 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። አድማጮች የተወሰነ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
መዝሙር 56 (135) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67 (156)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የታኅሣሥ 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው ለመጽሔት ደንበኛው ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግ የሚያሳይ ይሁን።
10 ደቂቃ:- “አልፈልግም።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ በአገልግሎት ክልላቸው ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የሚያሳስባቸው ነገር ምን እንደሆነ አድማጮችን ጠይቅ። ውይይቱን ለማስቆም “ፍላጎት የለኝም” ለሚል ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 16 ተመልከት።
25 ደቂቃ:- “ከፍተኛ ጥራት ያለው ሕክምና የትኛው ነው?” በሽማግሌ የሚቀርብ። ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል በተባለው የቪዲዮ ፊልም ላይ ለመወያየት የተዘጋጁትን ጥያቄዎች በመጠቀም ውይይቱን ጀምር። የመጨረሻውን አንቀጽ በማንበብ እንዲሁም የተጠቀሱትን የመጠበቂያ ግንብ ርዕሶች በጥንቃቄ እንዲያነቡ በማበረታታት ውይይቱን ደምድም።
መዝሙር 20 (45) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 7 (19)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በየካቲት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። እንዲሁም አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ:- “የተፈጥሮ አደጋ ቢደርስ ዝግጁ ናችሁ?” በሽማግሌ የሚቀርብ። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።
15 ደቂቃ:- ተመልሳችሁ እንደምትመጡ ቃል ከገባችሁ ቃላችሁን መጠበቅ አለባችሁ። በመስከረም 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ቃል በገቡት መሠረት ተመልሰው በመሄዳቸው እንዴት እንደተባረኩ የሚያሳዩ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 1 (3)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- የይሖዋ ምሥክር ነኝ! በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አንዳንድ ወጣቶች እኩዮቻችን ያሾፉብናል ብለው ስለሚፈሩ የይሖዋ ምሥክር መሆናቸውን ከመናገር ይቆጠባሉ። ይሁን እንጂ የይሖዋ ምሥክር መሆናችሁን እንድታሳውቁ የሚገፋፏችሁ ጥሩ ምክንያቶች አሉ። እምነታችሁን የሚያውቁ አስተማሪዎች ብዙውን ጊዜ አቋማችሁን ስለሚያከብሩላችሁ ተገቢ ያልሆነ ነገር እንድትፈጽሙ አይጠይቋችሁም፤ ሥርዓት አልበኛ የሆኑ ወጣቶች ሥነ ምግባር የጎደለው ድርጊት እንድትፈጽሙ ለመገፋፋት አይደፍሩም። ሌሎችም ቢሆኑ ተቃራኒ ጾታ ካለው ሰው ጋር ጓደኝነት የማትመሠርቱት ወይም በትምህርት ቤቱ ስፖርታዊ ውድድሮችም ሆነ ከትምህርት ሰዓት ውጪ በሚዘጋጁ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ የማትካፈሉት ለምን እንደሆነ በቀላሉ ይረዱላችኋል። በትምህርት ቤት ለመስበክ ድፍረት ታገኛላችሁ፤ እንዲሁም በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ በምትሰብኩበት ወቅት የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ያጋጥመኝ ይሆን ብላችሁ እምብዛም አትፈሩም። (ሚያዝያ 2002 ንቁ! ገጽ 16) አስፋፊዎች በትምህርት ቤት የይሖዋ ምሥክር መሆናቸውን ማሳወቃቸው እንዴት እንደጠቀማቸው ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።
20 ደቂቃ:- “ፍቅር—ፍሬያማ የሆነ አገልግሎት ለማከናወን የሚያስችል ቁልፍ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከየካቲት 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23 አንቀጽ 16-17 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦችን አክል።
መዝሙር 59 (139) እና የመደምደሚያ ጸሎት።