የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ ነሐሴ 27, 2007 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 2 እስከ ነሐሴ 27, 2007 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
የንግግር ባሕርይ
1. በአገልግሎት ላይም ሆነ በጉባኤ ለሌሎች አክብሮት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 192 አን. 2-4]
2. ሐሳባችንን በምናስረዳበት ጊዜ በእርግጠኝነት ስሜት ለመናገር ወሳኝ የሆነው ነገር ምንድን ነው? [be ገጽ 196 አን. 1-3]
3. ለሌሎች ስንመሠክር ዘዴኞች እንድንሆን ለመርዳት ከቀረቡት ሐሳቦች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? [be ገጽ 197 አን. 5 እስከ ገጽ 198 አን. 4]
4. ዘዴኛ መሆን በአገልግሎት ላይ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቆ መናገርን የሚጨምረው እንዴት ነው? (ምሳሌ 25:11) [be ገጽ 199 አን. 1-3]
5. ንግግራችን አዎንታዊ አቀራረብ እንዲኖረው ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 203 አን. 2 እስከ ገጽ 204 አን. 1]
ክፍል ቁጥር 1
6. የሕዝቅኤል መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለ መሆኑ፣ ስለ ትክክለኛነቱና የመጽሐፉ ጸሐፊ ሕዝቅኤል ስለ መሆኑ ምን ለማለት ይቻላል? [bsi07 ገጽ 6 አን. 3]
7. አንድ ሰው የተፈጸመበትን ኢፍትሐዊ ድርጊት እንዲቋቋም የሚረዳው በጣም አስፈላጊ ባሕርይ ምንድን ነው? [w05 6/1 ገጽ 29 አን. 4]
8. ኢየሱስ ትንሣኤን በተመለከተ ሰዱቃውያን ለጠየቁት ጥያቄ መልስ ከሰጠበት መንገድ ምን እንማራለን? (ሉቃስ 20:37, 38) [be ገጽ 66 አን. 4]
9. አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ወይም የእምነት ባልንጀራህ አንድን ጉዳይ በሚመለከት ምን ማድረግ እንዳለበት ቢጠይቅህ መልስህ ምን ሊሆን ይገባል? [be ገጽ 69 አን. 4-5]
10. ‘አእምሮአችንን ለተግባር የሚያነሳሳውን ኃይል ለማደስ’ ምን ያስፈልገናል? (ኤፌ. 4:23) [be ገጽ 74 አን. 4]
ሳምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. በሕዝቅኤል 9:2-4 ላይ የተጠቀሰው ቀጭን በፍታ የለበሰ ሰው ማንን ይወክላል? ‘ግንባር ላይ የሚደረገውስ ምልክት’ ምን ያመለክታል? [w88 9/15 ገጽ 14 አን. 18 (w-AM 18-109 ገጽ 9 አን. 18)]
12. የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖታዊ መሪዎች በሕዝቅኤል 13:3 ላይ እንደተጠቀሱት ‘የራሳቸውን መንፈስ የሚከተሉ ሞኝ ነቢያት’ የሆኑት እንዴት ነው? [w99 10/1 ገጽ 13]
13. በሕዝቅኤል 18:2 ላይ በተገለጸው “ተምሳሌት” መሠረት እስራኤላውያን ምን ለማድረግ ሞክረው ነበር? እዚህ ጥቅስ ላይ ተጠያቂነትን በተመለከተ ጎላ ተደርጎ የተጠቀሰው አስፈላጊ ትምህርት ምንድን ነው? [w88 9/15 ገጽ 18 አን. 10 (w-AM 18-109 ገጽ 14 አን. 10)]
14. ሕዝቅኤል ኢየሩሳሌም በተከበበችበትና በጠፋችበት ወቅት “ድዳ” የሆነው ወይም ‘ዝም ያለው’ በምን መልኩ ነው? (ሕዝ. 24:27፤ 33:22) [w03 12/1 ገጽ 29]
15. ‘በማጎግ ምድር የሚገኘው ጎግ’ ማን ነው? የይሖዋን ሕዝቦች ለማጥፋት የሚነሳውስ መቼ ነው? (ሕዝ. 38:2, 16) [w97 3/1 ከገጽ 14 አን. 1 እስከ ገጽ 15 አን. 3]