የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ ጥቅምት 29, 2007 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመስከረም 3 እስከ ጥቅምት 29, 2007 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
የንግግር ባሕርይ
1. መደጋገም ጠቃሚ የማስተማሪያ ዘዴ ነው የምንለው ለምንድን ነው? [be ገጽ 206 አን. 1-2፣ ሣጥኑ]
2. የአንድን ንግግር ጭብጥ ማጉላት የምንችልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው? [be ገጽ 210፣ ሣጥኑ]
3. የአንድ ንግግር ዋና ዋና ነጥቦች የሚባሉት የትኞቹ ናቸው? እነዚህን ነጥቦች ለመምረጥ ምን ሊረዳን ይችላል? [be ገጽ 212 አን. 1-3]
4. በአንድ ንግግር ውስጥ ዋና ዋና ነጥቦችን ማብዛት የማይኖርብን ለምንድን ነው? [be ገጽ 213 አን. 2-4]
5. መግቢያችን በጉጉት ለማዳመጥ የሚጋብዝ መሆኑ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 215 አን. 1, 5 እስከ ገጽ 216 አን. 2፣ ሣጥኑ]
ክፍል ቁ. 1
6. መዝሙር 119:89, 90 በአምላክ ቃል ላይ እምነት ማሳደር እንደምንችል የሚያሳየው እንዴት ነው? [w05 4/15 ገጽ 15, 16 አን. 3]
7. የሕዝቅኤል መጽሐፍ ጠበቅ አድርጎ የሚገልጸው ስለ ምን ጉዳይ ነው? በአሁኑ ጊዜ በአኗኗራቸው ይሖዋን እየቀደሱ ያሉ ሰዎች ምን በረከቶች ያገኛሉ? [bsi07 ገጽ 8 አን. 33]
8. የይሖዋ “ቃል” ልባችንን የሚጠብቅልን እንዴት ነው? (መዝ. 18:30) [w05 9/1 ገጽ 30 አን. 2]
9. የመንግሥቱ ተስፋ በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ጎላ ተደርጎ የተገለጸው እንዴት ነው? [bsi07 ገጽ 10 አን. 23]
10. የሆሴዕ መጽሐፍ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት ባስነገራቸው ትንቢቶች ላይ ያለንን እምነት የሚያጠነክርልን እንዴት ነው? [bsi07 ገጽ 12 አን. 14]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ሕዝቅኤል በተመለከተው ራእይ ውስጥ የቤተ መቅደሱ መለካት ምን ትርጉም አለው? ይህስ በዛሬው ጊዜ ለምንገኘው ምን ዋስትና ይሰጠናል? (ሕዝ. 40:2-5) [w99 3/1 ገጽ 9 አን. 6፤ ገጽ 14 አን. 7]
12. ሕዝቅኤል በተመለከተው ራእይ የመጨረሻ ፍጻሜ መሠረት ‘ገዢው’ ወይም አለቃው ማን ነው? (ሕዝ. 48:21) [w99 3/1 ገጽ 16 አን. 13-15፤ ገጽ 22-23 አን. 19-20]
13. የዳንኤል 2:21 ትርጉም ምንድን ነው? [w98 9/15 ገጽ 12 አን. 9]
14. ዳንኤልን በይሖዋ ፊት ‘እጅግ የተወደደ’ እንዲሆን ያደረገው ምንድን ነው? (ዳን. 9:23) [dp ገጽ 185 አን. 12፤ w04 8/1 ገጽ 12 አን. 17]
15. ‘አምላክን ማወቅ በእስራኤል ምድር የለም’ የተባለው ከምን አንጻር ነው? እኛስ በግለሰብ ደረጃ እነዚህን ቃላት እንዴት አድርገን ልንመለከታቸው ይገባል? (ሆሴዕ 4:1, 2, 6) [w05 11/15 ገጽ 21 አን. 21፤ jd ገጽ 57-58 አን. 5፤ ገጽ 61 አን. 10]