ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት:- መጽሔቶች እና ትራክት ቁጥር 26 (ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?)፤ ኅዳር:- ነቅተህ ጠብቅ!፤ ታኅሣሥ:- ታላቅ ሰው ወይም ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?፤ ጥር:- እውቀት ወይም ነቅተህ ጠብቅ!
◼ የታኅሣሥ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ለመሆን አመቺ ነው።
◼ በጥር ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ትራንስፊውዥን ኦልተርኔቲቭ ሄልዝ ኬር—ሚቲንግ ፔሸንት ኒድስ ኤንድ ራይትስ (በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና—የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር) የተሰኘውን ፊልም እንከልሳለን። ፊልሙን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ “የ2008 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” አባሪ ሆኖ የወጣ ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።
◼ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የመጨረሻውን ክፍል የሚያቀርበው ወንድም የመደምደሚያውን መዝሙር ማስተዋወቅ እንደሚኖርበት አስታውሱ። ከዚያም እሱ ወይም አስቀድሞ የተመደበ ብቃት ያለው ሌላ ወንድም የመደምደሚያውን ጸሎት ያቀርባል።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- እንግሊዝኛ፦ የ2006 የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ፣ የ2006 የመጠበቂያ ግንብና የንቁ! መጽሔት ጥራዞች።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፦ ለቤተሰብ ደስታ፤ ቀለል ባለ ቻይንኛ፦ ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ፤ እንግሊዝኛ፦ ለቤተሰብ ደስታ፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ የውዳሴ መዝሙር (ስምንት ካሴቶች)፤ ፈረንሳይኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ የዳንኤል ትንቢት፣ ታላቅ ሰው፣ ሥላሴ፤ ኦሮምኛ፦ የአምላክ ወዳጅ፤ ስዋሂሊ፦ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም።