የ2008 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያ
የ2008 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ክፍሎቹ የሚቀርቡባቸው ጽሑፎች፦ መጽሐፍ ቅዱስ [አ.መ.ት]፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም [be-AM]፣ “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው [bsi08-AM] እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rs-AM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ከተከፈተ በኋላ ከዚህ በታች በሰፈረው መመሪያ መሠረት ይከናወናል። እያንዳንዱ ክፍል ሲያበቃ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ቀጣዩን ክፍል ያስተዋውቃል።
የንግግር ባሕርይ፦ 5 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች፣ ረዳት ምክር ሰጪው ወይም ጥሩ ችሎታ ያለው ሌላ ሽማግሌ፣ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከተባለው መማሪያ መጽሐፍ ላይ በተወሰደ አንድ የንግግር ባሕርይ ላይ ተመሥርቶ ክፍል ያቀርባል። (በቂ ሽማግሌዎች በሌሉባቸው ጉባኤዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያላቸው የጉባኤ አገልጋዮች ይህን ክፍል ሊያቀርቡ ይችላሉ።)
ክፍል ቁ. 1፦ 10 ደቂቃ። ይህ ክፍል ብቃት ባለው አንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም በተባለው መጽሐፍ ወይም “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው በተባለው ብሮሹር ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ለአሥር ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ይቀርባል። ዓላማው በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር ለጉባኤው ይበልጥ ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ ማጉላት እንጂ የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ አይደለም። በፕሮግራሙ ላይ የተሰጠውን ጭብጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን ንግግር እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች ክፍላቸውን በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አቅርበው መጨረስ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይችላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 10 ደቂቃ። በመጀመሪያዎቹ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር እያዛመደ ያቀርበዋል። ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርበው ወንድም፣ ለሳምንቱ ከተመደበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ በፈለገው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ሐሳብ መስጠት ይችላል። ክፍሉ ለሳምንቱ የተመደቡትን ምዕራፎች በመከለስ ብቻ መቅረብ አይኖርበትም። ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት እንደሚጠቅም እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ተናጋሪው ለእሱ የተመደበለትን አምስት ደቂቃ ብቻ በመጠቀም አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አምስት ደቂቃ ላለመንካት መጠንቀቅ ይኖርበታል። ቀጥሎ አድማጮች ከሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ልባቸውን የነካውንና ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን ሐሳብ በአጭሩ (በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ) እንዲናገሩ ይጋብዛል። ከዚያም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በሁለተኛው አዳራሽ ውስጥ ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች መሄድ እንደሚችሉ ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ በ4 ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ የሚቀርብ። ይህን ክፍል አንድ ወንድም በንባብ ያቀርበዋል። ተማሪው መግቢያ እና መደምደሚያ ማዘጋጀት ሳያስፈልገው ክፍሉን በንባብ ብቻ ያቀርበዋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዎቹ ክፍሉን በሚገባ ተረድተው፣ በቅልጥፍና፣ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ በማጥበቅ፣ ድምፅን በመለዋወጥ፣ በተገቢው ቦታ ቆም በማለትና የራሳቸውን ተፈጥሯዊ አነጋገር በመጠቀም እንዲያነብቡ ለመርዳት ጥረት ያደርጋል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። ይህን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡ እህቶች በአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ ከተዘረዘሩት መቼቶች መካከል አንዱ ይመደብላቸዋል አሊያም ራሳቸው እንዲመርጡ ይደረጋል። ተማሪዋ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኘውን ጭብጥ መጠቀምና ክፍሉን ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል በሚስማማ መንገድ ማቅረብ ይኖርባታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪዋ በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ማሰባሰብ ይኖርባታል። አዳዲስ ተማሪዎች ጭብጡ ብቻ የተሰጠባቸውን ክፍሎች ማቅረብ አይኖርባቸውም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ እንዴት እንደምታዳብር እንዲሁም የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉምና የክፍሉን ዋና ዋና ነጥቦች እንድትገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። ተማሪው የተሰጠውን ጭብጥ ማዳበር ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪው በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ያሰባስባል። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ አድማጮቹን ግምት ውስጥ በማስገባት በንግግር መልክ ያቀርበዋል። ሆኖም ክፍሉን አንዲት እህት የምታቀርበው ከሆነ ለክፍል ቁጥር 3 በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተገቢ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ክፍል ቁጥር 4ን ለአንድ ወንድም ሊሰጥ ይችላል። የኮከብ ምልክት ያለባቸው ክፍሎች በንግግር መልክ መቅረብ ያለባቸው ስለሆኑ ለወንድሞች ብቻ መሰጠት ይኖርባቸዋል። በጉባኤያችሁ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትና በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚገኙትን የተለያዩ ክፍሎች ማቅረብ የሚችሉ ከበቂ በላይ ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች ካሉ የኮከብ ምልክት ያለባቸውን ክፍሎች የሚቻል ከሆነ አንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ቢያቀርበው ይመረጣል።
ምክር፦ 1 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪው የሚሠራበትን የንግግር ባሕርይ አስቀድሞ አይናገርም። እያንዳንዱ የተማሪ ክፍል ማለትም ቁ. 2፣ ቁ. 3 እና ቁ. 4 ከቀረበ በኋላ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የንግግሩን ገንቢ ጎኖች አንስቶ ተማሪውን ያመሰግናል። ዓላማው “ጥሩ ነው” ብሎ ለማለፍ ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ የተማሪው አቀራረብ ጥሩ የሆነበትን ምክንያት ለይቶ መጥቀስ ያስፈልገዋል። የእያንዳንዱን ተማሪ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከስብሰባው በኋላ ወይም በሌላ ጊዜ ገንቢ የሆነ ተጨማሪ ምክር በግል መስጠት ይችላል።
ጊዜ መጠበቅ፦ ክፍል የሚያቀርቡትም ሆኑ ምክር ሰጪው የተመደበላቸውን ጊዜ ማሳለፍ አይኖርባቸውም። ከቁጥር 2 እስከ 4 ያሉትን ክፍሎች የሚያቀርቡት ወንድሞች የተመደበላቸው ጊዜ ሲሞላ በዘዴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለ ንግግር ባሕርይ የሚናገረውን የመክፈቻ ንግግር፣ ክፍል ቁጥር 1ን ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርቡ ወንድሞች ሰዓት ካሳለፉ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይገባል። ሁሉም ሰዓታቸውን በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ጸሎትንና መዝሙርን ሳይጨምር ጠቅላላው ፕሮግራም 45 ደቂቃ ይፈጃል።
ምክር መስጫ ቅጽ፦ በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
ረዳት ምክር ሰጪ፦ የሽማግሌዎች አካል፣ ከትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተጨማሪ ረዳት ምክር ሰጪ ሆኖ የሚያገለግል ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ሊመርጥ ይችላል። በጉባኤው ውስጥ በርካታ ሽማግሌዎች ካሉ በየዓመቱ ብቃት ያላቸው ሽማግሌዎች እየተቀያየሩ ይህን ኃላፊነት ሊይዙ ይችላሉ። የዚህ ወንድም ኃላፊነት ንግግር ቁጥር 1ን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ለሚያቀርቡ ወንድሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግል ምክር መስጠት ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እነዚህን ክፍሎች የሚያቀርቡ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ንግግራቸውን ባቀረቡ ቁጥር ምክር ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም።
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ፦ 30 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በየሁለት ወሩ የሚደረገውን ክለሳ ይመራል። ክለሳው የሚደረገው የንግግር ባሕርይና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረቡ በኋላ ይሆናል። ክለሳው፣ የክለሳውን ሳምንት ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የቀረቡትን ትምህርቶች ይሸፍናል። የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳው ጉባኤያችሁ የወረዳ ስብሰባ በሚያደርግበት ሳምንት ላይ ከዋለ ክለሳው (እና በሳምንታዊ ፕሮግራሙ ላይ ያሉት ሌሎች ክፍሎች) በቀጣዩ ሳምንት ይቀርባሉ፤ የቀጣዩ ሳምንት ፕሮግራም ደግሞ በወረዳ ስብሰባው ላይ ይቀርባል። ክለሳውና የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት በሚገጣጠሙበት ጊዜ በፕሮግራሙ ላይ የሰፈረው መዝሙር፣ የንግግር ባሕርይና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች እንዳሉ ይወሰዳሉ። የማስተማሪያ ንግግሩ (ከንግግር ባሕርይ ቀጥሎ ይቀርባል) ለሚቀጥለው ሳምንት ከወጣው ፕሮግራም ላይ ይወሰዳል። በቀጣዩ ሳምንት፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ የወጣው የንግግር ባሕርይ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ ክለሳው ይቀጥላል።
ፕሮግራም
ጥር 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 1-6 መዝሙር 29 (62)
የንግግር ባሕርይ፦ በቂ ማብራሪያ መስጠት (be ገጽ 228 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የማቴዎስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 3-5 አን. 1-10)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 5:1-20
ቁ. 3፦ ሰዎች የሚሞቱት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 97 አን. 3–ገጽ 99 አን. 1)
ቁ. 4፦ የአምላክ ቅዱስ መንፈስ የሚረዳን በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ጥር 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 7-11 መዝሙር 67 (156)
የንግግር ባሕርይ፦ የልብ ዝንባሌ ወሳኝ ነው (be ገጽ 228 አን. 3-5)
ቁ. 1፦ የአምላክን ቃል በማንበብ ተደሰት (be ገጽ 9 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 10:1-23
ቁ. 3፦ ሐቀኛ መሆን ይክሳል የምንለው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ሙታን የት ናቸው? የሚገኙትስ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነው? (rs ገጽ 99 አን. 2–ገጽ 101 አን. 2)
ጥር 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 12-15 መዝሙር 55 (133)
የንግግር ባሕርይ፦ ግንዛቤ የሚያሰፋ ንግግር (be ገጽ 230 አን. 1-6)
ቁ. 1፦ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብብ (be ገጽ 10 አን. 1–ገጽ 12 አን. 3)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 14:1-22
ቁ. 3፦ የይሖዋ ምሥክሮች ለሙታን በሚደረገው ባሕላዊ የሐዘን ሥርዓት የማይካፈሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 102 አን. 1-7)
ቁ. 4፦ የክርስቶስ ተቃዋሚ ማን ነው?
ጥር 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 16-21 መዝሙር 13 (33)
የንግግር ባሕርይ፦ ምርምር በማድረግ አንድ ንግግር ግንዛቤ የሚያሰፋ እንዲሆን ማድረግ (be ገጽ 231 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ “እንዴት እንደምታዳምጡ በጥንቃቄ አስቡ” (be ገጽ 13 አን. 1–ገጽ 14 አን. 4)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 17:1-20
ቁ. 3፦ ሞትን አስመልክቶ ለሚነሱ የተሳሳቱ አመለካከቶች መልስ መስጠት (rs ገጽ 103 አን. 1-3)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ቅዱስ አድርገው የሚመለከቷቸው ነገሮች
የካ. 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 22-25 መዝሙር 64 (151)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ማብራራት (be ገጽ 231 አን. 4-5)
ቁ. 1፦ በጉባኤና በትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ማዳመጥ (be ገጽ 15 አን. 1–ገጽ 16 አን. 5)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 23:1-24
ቁ. 3፦ ለዘላለም መኖር አሰልቺ አይደለም
ቁ. 4፦ ከአምላክ የመነጩና ያልመነጩ ሕልሞች (rs ገጽ 104 አን. 1–ገጽ 106 አን. 2)
የካ. 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 26-28 መዝሙር 95 (213)
የንግግር ባሕርይ፦ የቃላትን ፍቺ ማብራራት (be ገጽ 232 አን. 1)
ቁ. 1፦ ማቴዎስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 5 አን. 29-33)
ቁ. 2፦ ማቴዎስ 27:1-22
ቁ. 3፦ አምላክ መኖሩን ማመን ብቻውን በቂ ያልሆነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች አደንዛዥ ዕፆችን የማይወስዱት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 106 አን. 3–ገጽ 108 አን. 2)
የካ. 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 1-4 መዝሙር 94 (212)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሱን ከጉዳዩ ጋር ማገናዘብ (be ገጽ 232 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ የማርቆስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 6-7 አን. 1-11)
ቁ. 2፦ ማርቆስ 2:1-17
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ማሪዋና የማይወስዱት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 108 አን. 3–ገጽ 109 አን. 3)
ቁ. 4፦ ፍቅር ድፍረት የሚጨምረው እንዴት ነው?
የካ. 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 5-8 መዝሙር 33 (72)
የንግግር ባሕርይ፦ አድማጮችን የሚጠቅሙ ሐሳቦችን መምረጥ (be ገጽ 233 አን. 1-5)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
መጋ. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 9-12 መዝሙር 87 (195)
የንግግር ባሕርይ፦ የተመደበልህን ጽሑፍ መጠቀም (be ገጽ 234 አን. 1–ገጽ 235 አን. 3)
ቁ. 1፦ የማስታወስ ችሎታህን ማሻሻል ትችላለህ (be ገጽ 17 አን. 1–ገጽ 18 አን. 5)
ቁ. 2፦ ማርቆስ 11:1-18
ቁ. 3፦ አምላክ መዋሸት የማይችልበት ምክንያት
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ሲጋራ የማያጨሱት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 110 አን. 1–ገጽ 111 አን. 4)
መጋ. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 13-16 መዝሙር 40 (87)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥያቄዎችን በጥሩ ሁኔታ መጠቀም (be ገጽ 236 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ማርቆስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 7-8 አን. 31-33)
ቁ. 2፦ ማርቆስ 14:1-21
ቁ. 3፦ መጥፎ ልማዶችን እንዴት ማሸነፍ ይቻላል? (rs ገጽ 112 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ ‘የሰው ቁጣ የአምላክን ጽድቅ የማያመጣው’ ለምንድን ነው? (ያዕ. 1:20)
መጋ. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 1-3 መዝሙር 6 (13)
የንግግር ባሕርይ፦ ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ጥያቄዎች (be ገጽ 237 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የሉቃስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 8-10 አን. 1-9)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 1:1-23
ቁ. 3፦ ‘እምነት ያለ ሥራ ዋጋ የማይኖረው’ ለምንድን ነው? (ያዕ. 2:20)
ቁ. 4፦ ብሔራት፣ አምላክ ለምድር ያወጣውን ዓላማ ማደናቀፍ አይችሉም (rs ገጽ 113 አን. 1–ገጽ 114 አን. 1)
መጋ. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 4-6 መዝሙር 67 (156)
የንግግር ባሕርይ፦ ስለ ጉዳዩ እንዲያመዛዝኑ ለመርዳት የሚያስችሉ ጥያቄዎች (be ገጽ 237 አን. 3–ገጽ 238 አን. 2)
ቁ. 1፦ የምናውቃቸውን ነገሮች በማስታወስ ረገድ የአምላክ መንፈስ የሚጫወተው ሚና (be ገጽ 19 አን. 1–ገጽ 20 አን. 2)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 4:1-21
ቁ. 3፦ ይሖዋ ምድርን በእሳት ያጠፋት ይሆን? (rs ገጽ 114 አን. 2–ገጽ 115 አን. 3)
ቁ. 4፦ አምላካዊ ፍርሃት ከኃጢአት ይጠብቀናል
መጋ. 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 7-9 መዝሙር 16 (37)
የንግግር ባሕርይ፦ አንድ ሰው ስሜቱን እንዲገልጽ ለማበረታታት የሚረዱ ጥያቄዎች (be ገጽ 238 አን. 3-5)
ቁ. 1፦ ለማንበብ መትጋት ያለብን ለምንድን ነው? (be ገጽ 21 አን. 1–ገጽ 23 አን. 3)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 7:1-17
ቁ. 3፦ አምላክ እንደሚወደንና ደስተኞች እንድንሆን እንደሚፈልግ የሚያሳይ ማስረጃ
ቁ. 4፦ የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም አባላት፣ ክፉዎች ከጠፉ በኋላ ወደ ምድር አይመለሱም (rs ገጽ 115 አን. 4–ገጽ 116 አን. 1)
ሚያ. 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 10-12 መዝሙር 15 (35)
የንግግር ባሕርይ፦ አጽንዖት ለመስጠት የሚረዱ ጥያቄዎች (be ገጽ 239 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ ትጉ አንባቢ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (be ገጽ 23 አን. 4–ገጽ 26 አን. 4)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 11:37-54
ቁ. 3፦ አምላክ ለምድር የነበረው ዓላማ ተለውጧል? (rs ገጽ 116 አን. 2–ገጽ 117 አን. 4)
ቁ. 4፦ በራእይ 17:17 ላይ ያለውን ሐሳብ መረዳት የሚኖርብን እንዴት ነው?
ሚያ. 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 13-17 መዝሙር 39 (86)
የንግግር ባሕርይ፦ የተሳሳተ አመለካከትን ለማጋለጥ የሚያስችሉ ጥያቄዎች (be ገጽ 239 አን. 3-5)
ቁ. 1፦ ማጥናት የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 27 አን. 1–ገጽ 31 አን. 2)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 16:1-15
ቁ. 3፦ አምላክ ቃርሚያን አስመልክቶ ያወጣው ሕግ ምን ያስተምረናል? (ዘሌ. 19:9, 10)
ቁ. 4፦ የታመሙ ሰዎችን እንዴት ማበረታታት እንችላለን? (rs ገጽ 118 አን. 1-4)
ሚያ. 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 18-21 መዝሙር 58 (138)
የንግግር ባሕርይ፦ አነጻጻሪና ተለዋጭ ዘይቤዎች (be ገጽ 240 አን. 1–ገጽ 241 አን. 1)
ቁ. 1፦ ሉቃስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 10-11 አን. 30-35)
ቁ. 2፦ ሉቃስ 18:1-17
ቁ. 3፦ የሚወዱትን ሰው በሞት ያጡ ሰዎችን እንዴት ማበረታታት እንችላለን? (rs ገጽ 118 አን. 5-9)
ቁ. 4፦ ‘አታጉረምርሙ’ ሲባል ምን ማለት ነው? (ፊልጵ. 2:14)
ሚያ. 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 22-24 መዝሙር 2 (4)
የንግግር ባሕርይ፦ ምሳሌዎችን መጠቀም (be ገጽ 241 አን. 2-4)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ግን. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 1-4 መዝሙር 50 (123)
የንግግር ባሕርይ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ምሳሌዎች (be ገጽ 242 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የዮሐንስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 11-13 አን. 1-9)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 3:1-21
ቁ. 3፦ ዳዊት፣ ንጉሥ ሳኦል እንዲገደል አለመስማማቱ ምን ያስተምረናል?
ቁ. 4፦ የአምላክን ፈቃድ በማድረጋቸው ስደት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆን ማበረታቻ (rs ገጽ 119 አን. 1-6)
ግን. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 5-7 መዝሙር 44 (105)
የንግግር ባሕርይ፦ አድማጮች ምሳሌውን በቀላሉ ይረዱታል? (be ገጽ 242 አን. 3–ገጽ 243 አን. 1)
ቁ. 1፦ ጥናት በረከት ያስገኛል (be ገጽ 31 አን. 3–ገጽ 32 አን. 3)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 6:1-21
ቁ. 3፦ ከሐናንያና ሰጲራ ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ቁ. 4፦ በፍትሕ መጓደል ምክንያት የሚተክዙ ሰዎችን እንዴት ማበረታታት ትችላለህ? (rs ገጽ 119 አን. 7–ገጽ 120 አን. 2)
ግን. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 8-11 መዝሙር 83 (187)
የንግግር ባሕርይ፦ የተለመዱ ነገሮችን ምሳሌ አድርጎ መጠቀም (be ገጽ 244 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ምርምር ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 33 አን. 1–ገጽ 35 አን. 2)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 11:38-57
ቁ. 3፦ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት የተጨነቁ ሰዎችን የሚያጽናና ምን ማበረታቻ አለ? (rs ገጽ 120 አን. 3-7)
ቁ. 4፦ አንድ ሰው የአሥርቱን ትእዛዛት የመጨረሻ ሕግ እንዲጠብቅ ማስገደድ የማይቻል ከሆነ ሕጉ መሰጠት ያስፈለገው ለምንድን ነው?
ግን. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 12-16 መዝሙር 1 (3)
የንግግር ባሕርይ፦ ለአድማጮች የሚስማሙ ምሳሌዎች (be ገጽ 244 አን. 3–ገጽ 245 አን. 4)
ቁ. 1፦ ለምርምር የሚረዱ ሌሎች ጽሑፎችን መጠቀም (be ገጽ 35 አን. 3–ገጽ 38 አን. 4)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 12:1-19
ቁ. 3፦ በጉድለቶቻቸው ምክንያት ቅስማቸው ለተሰበረ ሰዎች የሚሆን ማበረታቻ (rs ገጽ 120 አን. 8–ገጽ 121 አን. 2)
ቁ. 4፦ ሸክማችንን በይሖዋ ላይ የምንጥለው እንዴት ነው? (መዝ. 55:22)
ሰኔ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 17-21 መዝሙር 9 (26)
የንግግር ባሕርይ፦ በሚታዩ ነገሮች አስደግፎ ማስተማር (be ገጽ 247 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ ዮሐንስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 13-14 አን. 30-35)
ቁ. 2፦ ዮሐንስ 21:1-14
ቁ. 3፦ በማናየው አምላክ የምናምነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ሳይንሳዊ እንቆቅልሽ የሆነው ዝግመተ ለውጥ (rs ገጽ 121 አን. 3–ገጽ 123 አን. 2)
ሰኔ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 1-4 መዝሙር 42 (92)
የንግግር ባሕርይ፦ ኢየሱስ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ያስተማረው እንዴት ነው? (be ገጽ 247 አን. 3)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 14-15 አን. 1-8)
ቁ. 2፦ ሥራ 1:1-14
ቁ. 3፦ ዝግመተ ለውጥ፣ የቅሪተ አካል መረጃና ምክንያታዊነት (rs ገጽ 123 አን. 3–ገጽ 126 አን. 5)
ቁ. 4፦ ‘በድፍረት’ የመናገር ችሎታ ምን ነገሮችን ይጨምራል? (ዕብ. 3:6 የ1954 ትርጉም)
ሰኔ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 5-7 መዝሙር 76 (172)
የንግግር ባሕርይ፦ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር የሚቻልባቸው መንገዶች (be ገጽ 248 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ አስተዋጽኦ ማዘጋጀት (be ገጽ 39-42)
ቁ. 2፦ ሥራ 5:1-16
ቁ. 3፦ የዝግመተ ለውጥ አማኞች ለሚያነሷቸው ሐሳቦች ምላሽ መስጠት (rs ገጽ 127 አን. 1–ገጽ 129 አን. 2)
ቁ. 4፦ ይሖዋን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (መዝ. 111:10)
ሰኔ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 8-10 መዝሙር 66 (155)
የንግግር ባሕርይ፦ ካርታዎችን፣ የትላልቅ ስብሰባ ፕሮግራሞችንና የቪዲዮ ክሮችን ተጠቅሞ ማስተማር (be ገጽ 248 አን. 4–ገጽ 249 አን. 2)
ቁ. 1፦ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡህን የተማሪ ክፍሎች መዘጋጀት (be ገጽ 43 አን. 1–ገጽ 44 አን. 3)
ቁ. 2፦ ሥራ 8:1-17
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ‘ችግረኛውን የሚታደገው’ እንዴት ነው? (መዝ. 72:12)
ቁ. 4፦ ብዙዎች እምነት የሚያንሳቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 130 አን. 1–ገጽ 131 አን. 2)
ሰኔ 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 11-14 መዝሙር 35 (79)
የንግግር ባሕርይ፦ ለብዙ አድማጮች ማስረዳት (be ገጽ 249 አን. 3–ገጽ 250 አን. 2)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሐምሌ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 15-17 መዝሙር 49 (114)
የንግግር ባሕርይ፦ የምታስረዳበት መንገድ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (be ገጽ 251 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ ከጭብጡና ከመቼቱ ጋር የሚስማማ ዝግጅት (be ገጽ 44 አን. 4–ገጽ 46 አን. 1)
ቁ. 2፦ ሥራ 16:1-15
ቁ. 3፦ ይሖዋን ያለፍርሃት እንድናገለግለው የሚያደርጉ ምን ምክንያቶች አሉ?
ቁ. 4፦ አንድ ሰው እምነት ማዳበር የሚችለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 131 አን. 3–ገጽ 132 አን. 1)
ሐምሌ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 18-21 መዝሙር 12 (32)
የንግግር ባሕርይ፦ ከየት እንጀምር? (be ገጽ 251 አን. 4–ገጽ 252 አን. 3)
ቁ. 1፦ ለጉባኤ የሚቀርቡ ንግግሮችን መዘጋጀት (be ገጽ 47 አን. 1–ገጽ 49 አን. 1)
ቁ. 2፦ ሥራ 20:1-16
ቁ. 3፦ ጽድቅ የሚሰፍንበት አዲስ ሥርዓት እንደሚመጣ ያለንን እምነት በሥራ ማሳየት (rs ገጽ 132 አን. 3–ገጽ 133 አን. 1)
ቁ. 4፦ በዘፀአት 23:19ለ ላይ ከሚገኘው ሕግ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?
ሐምሌ 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 22-25 መዝሙር 88 (200)
የንግግር ባሕርይ፦ ምክንያታዊ መሆን የሚያስፈልግበት ጊዜ (be ገጽ 252 አን. 4–ገጽ 253 አን. 2)
ቁ. 1፦ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡ ክፍሎችንና ሌሎች ንግግሮችን መዘጋጀት (be ገጽ 49 አን. 2–ገጽ 51 አን. 1)
ቁ. 2፦ ሥራ 22:1-16
ቁ. 3፦ የይሖዋ ምሥክሮች በዮሐንስ 13:34, 35 ላይ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ እያደረጉ ያሉት በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ቁ. 4፦ ሐሰተኛ ነቢያት እንዴት ተለይተው ሊታወቁ ይችላሉ? (rs ገጽ 133 አን. 2–ገጽ 134 አን. 7)
ሐምሌ 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሥራ 26-28 መዝሙር 11 (29)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥያቄ መጠየቅና በምክንያት ማስረዳት (be ገጽ 253 አን. 3–ገጽ 254 አን. 2)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 15-17 አን. 32-40)
ቁ. 2፦ ሥራ 26:1-18
ቁ. 3፦ እውነተኛ ነቢያት አንድ ትንቢት መቼና እንዴት እንደሚፈጸም ሁልጊዜ ላያውቁ ይችላሉ (rs ገጽ 135 አን. 1-6)
ቁ. 4፦ ይሖዋ የሚታገሠው ለምንድን ነው?
ነሐሴ 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 1-4 መዝሙር 80 (180)
የንግግር ባሕርይ፦ በአምላክ ቃል ላይ ተመሥርቶ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ (be ገጽ 255 አን. 1–ገጽ 256 አን. 2)
ቁ. 1፦ የሮሜ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 17-18 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ ሮሜ 3:1-20
ቁ. 3፦ መላእክት የአምላክን አገልጋዮች የሚጠብቁትና የሚያበረቱት እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ የይሖዋ ምሥክሮች ለእውነተኛው አምልኮ መጠናከር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ (rs ገጽ 135 አን. 7-8)
ነሐሴ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 5-8 መዝሙር 91 (207)
የንግግር ባሕርይ፦ ተጨማሪ ማስረጃዎች ማቅረብ (be ገጽ 256 አን. 3-5)
ቁ. 1፦ ለሕዝብ የሚቀርብ ንግግር መዘጋጀት (be ገጽ 52 አን. 1–ገጽ 54 አን. 1)
ቁ. 2፦ ሮሜ 6:1-20
ቁ. 3፦ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያፈሩት ፍሬ ተለይተው ይታወቃሉ (rs ገጽ 136 አን. 1–ገጽ 137 አን. 2)
ቁ. 4፦ ጽድቅን ማድረግ ጥበቃ ሊሆንልን የሚችለው እንዴት ነው?
ነሐሴ 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 9-12 መዝሙር 65 (152)
የንግግር ባሕርይ፦ በቂ ማስረጃ ማቅረብ (be ገጽ 257 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ ሮሜ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 18-19 አን. 20-25)
ቁ. 2፦ ሮሜ 9:1-18
ቁ. 3፦ ሐሜት ማሠራጨትና ወሬ ማዛመት ምን አደጋዎች አሉት?
ቁ. 4፦ ሐሰተኛ ነቢያት እንደሆንን ለሚናገሩ ሰዎች ምላሽ መስጠት (rs ገጽ 138 አን. 1-3)
ነሐሴ 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮሜ 13-16 መዝሙር 7 (19)
የንግግር ባሕርይ፦ ልብ ለመንካት መጣር (be ገጽ 258 አን. 1-5)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
መስ. 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ቆሮንቶስ 1-9 መዝሙር 31 (67)
የንግግር ባሕርይ፦ የሰዎችን ሐሳብ ማስተዋል (be ገጽ 259 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የ1 ቆሮንቶስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 20-21 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ 1 ቆሮንቶስ 4:1-17
ቁ. 3፦ አምላክ እያንዳንዱ ሰው የሚሞትበትን ጊዜ አስቀድሞ አልወሰነም (rs ገጽ 138 አን. 4–ገጽ 139 አን. 1)
ቁ. 4፦ ቁሳዊ ሀብት ማግኘት አምላክ እንደባረከን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው?
መስ. 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ቆሮንቶስ 10-16 መዝሙር 15 (35)
የንግግር ባሕርይ፦ የአድማጮችን ስሜት መቀስቀስ (be ገጽ 259 አን. 4–ገጽ 260 አን. 1)
ቁ. 1፦ 1 ቆሮንቶስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 21-22 አን. 23-26)
ቁ. 2፦ 1 ቆሮንቶስ 13:1–14:6
ቁ. 3፦ የአምላክ ቃል የሚናገረውን የሚያደርጉ ሰዎች ደስተኛ የሚሆኑት ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ በሰዎች ላይ የሚደርሰው ነገር ሁሉ የአምላክ ፈቃድ አይደለም (rs ገጽ 139 አን. 2–ገጽ 140 አን. 7)
መስ. 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ቆሮንቶስ 1-7 መዝሙር 28 (58)
የንግግር ባሕርይ፦ ሌሎች አምላካዊ ፍርሃት እንዲያዳብሩ መርዳት (be ገጽ 260 አን. 2-3)
ቁ. 1፦ የ2 ቆሮንቶስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 22 አን. 1-4)
ቁ. 2፦ 2 ቆሮንቶስ 1:1-14
ቁ. 3፦ አምላክ እያንዳንዱን ነገር አስቀድሞ አያውቅም እንዲሁም አይወስንም (rs ገጽ 140 አን. 8–ገጽ 141 አን. 2)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ስደት ሲደርስባቸው የሚደሰቱት ለምንድን ነው?
መስ. 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ቆሮንቶስ 8-13 መዝሙር 24 (50)
የንግግር ባሕርይ፦ አምላክ በምናደርገው ነገር ሊያዝንም ሊደሰትም ይችላል (be ገጽ 260 አን. 4-5)
ቁ. 1፦ 2 ቆሮንቶስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 23 አን. 18-20)
ቁ. 2፦ 2 ቆሮንቶስ 9:1-15
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች የዓለም ክፍል የማይሆኑት ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ አምላክ ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ለማወቅም ሆነ ለመወሰን ያለው ችሎታ (rs ገጽ 141 አን. 3–ገጽ 142 አን. 2)
መስ. 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ገላትያ 1-6 መዝሙር 71 (163)
የንግግር ባሕርይ፦ ራሳቸውን እንዲመረምሩ መርዳት (be ገጽ 261 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የገላትያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 24-25 አን. 1-6, 14-18)
ቁ. 2፦ ገላትያ 1:1-17
ቁ. 3፦ አምላክ፣ ከአዳም ጋር በተያያዘ አስቀድሞ የማወቅ ችሎታውን ያልተጠቀመው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 142 አን. 3–ገጽ 143 አን. 1)
ቁ. 4፦ ፍቅር የሰውን ፍርሃት ማሸነፍ እንድንችል የሚረዳን እንዴት ነው?
ጥቅ. 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤፌሶን 1-6 መዝሙር 87 (195)
የንግግር ባሕርይ፦ ከልብ የመታዘዝን ባሕርይ ማዳበር (be ገጽ 261 አን. 4–ገጽ 262 አን. 2)
ቁ. 1፦ የኤፌሶን መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 26-28 አን. 1-8, 16-19)
ቁ. 2፦ ኤፌሶን 3:1-19
ቁ. 3፦ ይቅርታ መጠየቅ የድክመት ምልክት አይደለም
ቁ. 4፦ አምላክ የያዕቆብን፣ የዔሣውንና የይሁዳን ዕድል አስቀድሞ አልወሰነም (rs ገጽ 143 አን. 2–ገጽ 144 አን. 1)
ጥቅ. 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ፊልጵስዩስ 1–ቈላስይስ 4 መዝሙር 50 (123)
የንግግር ባሕርይ፦ የሰዎችን ልብ ለመንካት ከይሖዋ ጋር መተባበር (be ገጽ 262 አን. 3)
ቁ. 1፦ የፊልጵስዩስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 28-29 አን. 1-7, 12-14)
ቁ. 2፦ ፊልጵስዩስ 3:1-16
ቁ. 3፦ የክርስቲያን ጉባኤ ሁኔታ አስቀድሞ የተወሰነው በምን መንገድ ነበር? (rs ገጽ 144 አን. 2-3)
ቁ. 4፦ * ቈላስይስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 30-31 አን. 12-14)
ጥቅ. 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ተሰሎንቄ 1–2 ተሰሎንቄ 3 መዝሙር 84 (190)
የንግግር ባሕርይ፦ በሰዓቱ መጨረስ (be ገጽ 263 አን. 1–ገጽ 264 አን. 4)
ቁ. 1፦ የ1ኛ እና የ2ኛ ተሰሎንቄ መጻሕፍት ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (bsi ገጽ 3-4 አን. 1-5, 13-15፤ ገጽ 5-6 አን. 1-4, 10-11)
ቁ. 2፦ 1 ተሰሎንቄ 1:1–2:8
ቁ. 3፦ ለኮከብ ቆጠራ ሊኖረን የሚገባው ቅዱስ ጽሑፋዊ አመለካከት ምንድን ነው? (rs ገጽ 145 አን. 1-5)
ቁ. 4፦ * አንደኛ እና ሁለተኛ ጢሞቴዎስ—ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (bsi ገጽ 7-8 አን. 15-19፤ ገጽ 9 አን. 10-12)
ጥቅ. 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ጢሞቴዎስ 1–2 ጢሞቴዎስ 4 መዝሙር 97 (217)
የንግግር ባሕርይ፦ ልብ የሚነካ ምክር (be ገጽ 265 አን. 1-3)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ኅዳር 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ቲቶ 1–ፊልሞና መዝሙር 34 (77)
የንግግር ባሕርይ፦ ከፍቅር የመነጨ ምክር መስጠት (be ገጽ 266 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ የቲቶ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 10-11 አን. 1-4, 8-10)
ቁ. 2፦ ቲቶ 1:1-16
ቁ. 3፦ በአምላክ መኖር ለማመን ከሚያበቁ ጥሩ ምክንያቶች ውስጥ አንዳንዶቹ የትኞቹ ናቸው? (rs ገጽ 146 አን. 1–ገጽ 147 አን. 2)
ቁ. 4፦ * ፊልሞና—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 12-13 አን. 7-10)
ኅዳር 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕብራውያን 1-8 መዝሙር 61 (144)
የንግግር ባሕርይ፦ በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ የተመሠረተ ምክር (be ገጽ 267 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የዕብራውያን መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 13-15 አን. 1-9)
ቁ. 2፦ ዕብራውያን 3:1-19
ቁ. 3፦ ክፋትና መከራ መኖሩ አምላክ እንደሌለ አያረጋግጥም (rs ገጽ 147 አን. 3-5)
ቁ. 4፦ በእውነተኛና ለታይታ በሚደረግ ትሕትና መካከል ያሉት ልዩነቶች
ኅዳር 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕብራውያን 9-13 መዝሙር 51 (127)
የንግግር ባሕርይ፦ በድፍረት መናገር (be ገጽ 267 አን. 3-4)
ቁ. 1፦ ዕብራውያን—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 15-16 አን. 23-27)
ቁ. 2፦ ዕብራውያን 10:1-17
ቁ. 3፦ አምላክ ስሜትም ሆነ የተወሰነ አካል አለው (rs ገጽ 148 አን. 1-7)
ቁ. 4፦ ይቅር ባይ መሆን አንድነትን የሚያጠነክረው እንዴት ነው?
ኅዳር 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ያዕቆብ 1-5 መዝሙር 20 (45)
የንግግር ባሕርይ፦ ንግግራችን የሚያበረታታ መሆን ያለበት ለምንድን ነው? (be ገጽ 268 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የያዕቆብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 16-18 አን. 1-7, 15-17)
ቁ. 2፦ ያዕቆብ 1:1-21
ቁ. 3፦ አምላክ መጀመሪያ የለውም (rs ገጽ 148 አን. 8–ገጽ 149 አን. 2)
ቁ. 4፦ ‘ምሕረት በፍርድ ላይ የሚያይለው’ እንዴት ነው? (ያዕ. 2:13)
ታኅ. 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ጴጥሮስ 1–2 ጴጥሮስ 3 መዝሙር 14 (34)
የንግግር ባሕርይ፦ ይሖዋ ያደረጋቸውን ነገሮች መለስ ብለው እንዲያስቡ ማድረግ (be ገጽ 268 አን. 4–ገጽ 269 አን. 1)
ቁ. 1፦ የ1ኛ ጴጥሮስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 19-20 አን. 1-5, 11-13)
ቁ. 2፦ 1 ጴጥሮስ 2:1-17
ቁ. 3፦ ለመዳን በአምላክ ስም መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው (rs ገጽ 149 አን. 3–ገጽ 150 አን. 1)
ቁ. 4፦ * ሁለተኛ ጴጥሮስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 21-22 አን. 8-10)
ታኅ. 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዮሐንስ 1–ይሁዳ መዝሙር 54 (132)
የንግግር ባሕርይ፦ ይሖዋ ሕዝቦቹን እንዴት እንደረዳ ማስገንዘብ (be ገጽ 269 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ የ1ኛ፣ የ2ኛ እና የ3ኛ ዮሐንስ መጻሕፍት ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (bsi ገጽ 22-24 አን. 1-5, 11-13፤ ገጽ 24-25 አን. 1-3, 5፤ ገጽ 26 አን. 1-3, 5)
ቁ. 2፦ 1 ዮሐንስ 4:1-16
ቁ. 3፦ ሁሉም ሃይማኖቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው? (rs ገጽ 150 አን. 2-5)
ቁ. 4፦ * ይሁዳ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 28 አን. 8-10)
ታኅ. 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 1-6 መዝሙር 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ አምላክ እያደረገልን ባለው ነገር እንደምትደሰት ማሳየት (be ገጽ 269 አን. 5–ገጽ 271 አን. 1)
ቁ. 1፦ የራእይ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (bsi ገጽ 28-30 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ ራእይ 3:1-13
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ምን ዓይነት “አምላክ” ነው? (rs ገጽ 150 አን. 6-7)
ቁ. 4፦ ትዕግሥትም ሆነ ምሕረት ገደብ አላቸው የምንለው ለምንድን ነው?
ታኅ. 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 7-14 መዝሙር 8 (21)
የንግግር ባሕርይ፦ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ሙሉ ጥቅም አግኙ (be ገጽ 5 አን. 1–ገጽ 8 አን. 1)
ቁ. 1፦ ራእይ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (bsi ገጽ 30-31 አን. 28-34)
ቁ. 2፦ ራእይ 8:1-13
ቁ. 3፦ በአምላክ ማመንን አስመልክቶ ለሚነሱ የተቃውሞ ሐሳቦች ምላሽ መስጠት (rs ገጽ 151 አን. 1–ገጽ 152 አን. 1)
ቁ. 4፦ ‘አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው’ የሚለው አባባል ምን ትርጉም አለው? (1 ዮሐ. 3:20)
ታኅ. 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 15-22 መዝሙር 81 (181)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥርት ያለ ንባብ (be ገጽ 83 አን. 1–ገጽ 84 አን. 1)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ፤ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ቢያቀርቡት ይመረጣል።