የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ ታኅሣሥ 31, 2007 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከኅዳር 5 እስከ ታኅሣሥ 31, 2007 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
የንግግር ባሕርይ
1. መደምደሚያችን ግቡን እንዲመታ ለማድረግ ልናስብባቸው የሚገቡ ነጥቦች የትኞቹ ናቸው? [be ገጽ 220 አን. 4 እስከ ገጽ 221 አን. 3]
2. በአገልግሎት ላይ የምንናገረው ሐሳብ ትክክለኛ እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርብናል? [be ገጽ 223 አን. 2-4]
3. በስብሰባዎች ላይ ክፍል በምናቀርብበት ጊዜ ጉባኤው “የእውነት ዐምድና መሠረት” መሆኑን እንደተገነዘብን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (1 ጢሞ. 3:15) [be ገጽ 224 አን. 1-4]
4. የምናስተላልፈው መረጃ ተአማኒነት ያለው መሆኑን ማረጋገጣችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንንስ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 225 አን. 1-2]
5. በምናስተምርበት ወቅት ሌሎች ትምህርቱን በቀላሉ እንዲረዱት አድርገን ማቅረብ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 226 አን. 3 እስከ ገጽ 227 አን. 1]
ክፍል ቁ. 1
6. የዮናስ መጽሐፍ እውነተኛ ታሪክ መሆኑን የሚያረጋግጠው ምንድን ነው? [bsi07 ገጽ 18 አን. 3]
7. ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ በመሆን ከሚጫወተው ሚና ጋር ግንኙነት ያለው የሚክያስ ትንቢት የትኛው ነው? [bsi07 ገጽ 20-21 አን. 18]
8. የዕንባቆም መጽሐፍ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መሆኑን የሚያረጋግጠው ምንድን ነው? [bsi07 ገጽ 23 አን. 4]
9. አይሁዳውያን እስከ 520 ከክርስቶስ ልደት በፊት ድረስ ከግዞት የተመለሱበትን ዓላማ አልፈጸሙም ነበር ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው? (ሐጌ 1:4) [bsi07 ገጽ 27 አን. 3]
10. ዘካርያስ በተደጋጋሚ የጠቀሰው ስለ የትኛው ክብራማ ቀን ነው? [bsi07 ገጽ 30 አን. 26]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ኢዩኤል አንድ የነፍሳት ሠራዊት ያደረገውን ወረራ አስመልክቶ የተናገረው ትንቢት በመጀመሪያው መቶ ዘመን ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነበር? በዛሬው ጊዜስ ፍጻሜውን እያገኘ ያለው እንዴት ነው? (ኢዩ. 2:1-10, 28) [w07 10/1 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የኢዩኤል እና የአሞጽ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
12. “የጎመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት” ምን ያመለክታል? (አሞጽ 8:1, 2) [w07 10/1 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የኢዩኤል እና የአሞጽ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
13. ይሖዋ በነነዌ ሕዝብ ላይ ‘እንደሚያደርግባቸው በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቷል’ ሲባል ምን ማለት ነው? ይህስ በእኛ ላይ ምን ስሜት ሊያሳድርብን ይገባል? (ዮናስ 3:10 የ1954 ትርጉም) [w03 7/15 ገጽ 17-18]
14. በይሖዋ ስም መሄድ ሲባል ምን ማለት ነው? (ሚክ. 4:5) [w03 8/15 ገጽ 17 አን. 19]
15. በዘመናችን ይሖዋ ለፍርድ “ወደ ቤተ መቅደሱ” የመጣው መቼና እንዴት ነው? (ሚል. 3:1-3) [re ገጽ 32 ሣጥኑ፤ jd ገጽ 179 አን. 3 እስከ ገጽ 181 አን. 6]