የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 33—ሚክያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • በ740 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሰማርያን አጥፍተው የሰሜኑን የእስራኤል መንግሥት በግዞት ወስደዋል። (2 ነገ. 17:5, 6) ቆየት ብሎም በአራተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ሰማርያ በታላቁ እስክንድር የተወረረች ሲሆን በሁለተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በቀዳማዊ ጆን ሂርካነስ መሪነት አይሁዳውያን ወርረው አውድመዋታል። ዘ ኒው ዌስትሚኒስተር ዲክሽነሪ ኦቭ ዘ ባይብል፣ 1970 በገጽ 822 ላይ ሰማርያ ለመጨረሻ ጊዜ ስለጠፋችበት ሁኔታ ሲናገር “ድል አድራጊዎቹ በዚያ ኮረብታ ላይ የተመሸገ ከተማ እንደነበረ የሚያሳይ አንዳች ማስረጃ እንዳይቀር በማሰብ አውድመዋታል” ይላል።

      5 በአርኪኦሎጂ የተገኘ ማስረጃ የሚክያስ ትንቢት በትክክል የተፈጸመ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሰጣል። ሰማርያ በአሦራውያን መጥፋትዋ በአሦራውያን ዜና ታሪክ ውስጥ ተመዝግቧል። ለምሳሌ ያህል፣ የአሦራውያን ንጉሥ የነበረው ሳርጎን “ሰማርያን (ሳሚሪና) ከከበብኩ በኋላ ድል አድርጌያታለሁ” በማለት በጉራ ተናግሯል።a ይሁን እንጂ ከከበባው በኋላ የመጨረሻውን ድል የተቀዳጀው ከሳርጎን በፊት የነበረው ንጉሥ ስልምናሶር አምስተኛ ሳይሆን አይቀርም። አንድ የባቢሎናውያን ዜና መዋዕል ስለ ስልምናሶር ሲናገር “ሰማርያን አወደማት” ይላል።b ይሁዳ በሚክያስ ትንቢት መሠረት በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት መወረሯን ሰናክሬብ በሚገባ አስመዝግቦታል። (ሚክ. 1:6, 9፤ 2 ነገ. 18:13) በነነዌ በነበረው ቤተ መንግሥቱ ግድግዳ ላይ ባሠራው ባለ አራት ማዕዘን ትልቅ ቅርጽ ላይ ለኪሶ ስትወረር የሚያሳይ ሥዕላዊ መግለጫ ይገኛል። በተጨማሪም እንደሚከተለው በማለት ጽፏል:- “ከጠንካራ ከተሞቹ መካከል 46ቱን ከበብኩ። . . . ከከተሞቹ ውስጥ 200,150 የሚያክሉ ሰዎችን አስወጣሁ። . . . እርሱንም ንጉሣዊ መኖሪያው በነበረችው በኢየሩሳሌም ውስጥ በጎጆዋ እንዳለች ወፍ እስረኛ ሆኖ እንዲኖር አደረግኩ።” በተጨማሪም ምንም እንኳ መጠኑን አጋንኖ ቢያቀርብም ሕዝቅያስ የሰጠውን ግብር ዘርዝሯል። በራሱ ሠራዊት ላይ የደረሰውን መቅሰፍት ግን አልጠቀሰም።c—2 ነገ. 18:14-16፤ 19:35

      6 በሚክያስ 5:2 ላይ መሲሑ ስለሚወለድበት ቦታ የሚናገረው ጎላ ብሎ የሚታይ ትንቢት የሚክያስ መጽሐፍ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ስለመሆኑ የሚነሳውን ጥርጥር ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል። (ማቴ. 2:4-6) በተጨማሪም በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ከሚክያስ መጽሐፍ ጋር የሚመሳሰሉ ሐሳቦች አሉ።—ሚክ. 7:6, 20፤ ማቴ. 10:35, 36፤ ሉቃስ 1:72, 73

      7 ሚክያስ ከይሁዳ ገጠራማ አካባቢ የመጣ ሰው ቢሆንም ሐሳቡን የመግለጽ ችግር አልነበረበትም። በአምላክ ቃል ውስጥ ከሠፈሩት ግሩም አነጋገሮች መካከል አንዳንዶቹ የሚገኙት በሚክያስ መጽሐፍ ውስጥ ነው። ምዕራፍ 6 የተጻፈው በውይይት መልክ ነው። ሚክያስ ከአንዱ ነጥብ ወደ ሌላው ነጥብ፣ ከበረከት ወደ መርገም እንዲሁም ከመርገም ወደ በረከት በፍጥነት ሲሸጋገር የአንባቢውን ስሜት ይመስጣል። (ሚክ. 2:10, 12፤ 3:1, 12፤ 4:1) ሥዕላዊ የሆኑ መግለጫዎች በብዛት ይገኛሉ:- ይሖዋ ሲመጣ “ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይሰነጠቃሉ፤ በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፣ በገደል ላይ እንደሚወርድ ፈሳሽ ይሆናሉ።”—1:4፤ በተጨማሪም 7:17ን ተመልከት።

      8 መጽሐፉ በሦስት ሊከፈል የሚችል ሲሆን በእያንዳንዱ ክፍል የመጀመሪያ ዓረፍተ ነገር ላይ ሕዝቡ “ስሙ” ተብለዋል። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ተግሣጽ የተሰጠባቸው፣ ጥፋት እንደሚመጣ ማስጠንቀቂያ የተነገረባቸውና በረከት እንደሚያገኙ ተስፋ የተሰጠባቸው ሐሳቦች ይገኛሉ።

      ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት

      16 ከዛሬ 2,700 ዓመታት ገደማ በፊት የሚክያስ ትንቢት ‘ለመገሠጽ የሚጠቅም’ መጽሐፍ መሆኑ ተረጋግጧል፤ የይሁዳ ንጉሥ የነበረው ሕዝቅያስ የሚክያስን መልእክት ሰምቶ መላው ብሔር ንስሐ እንዲገባና ሃይማኖታዊ ተሐድሶ እንዲያደርግ ማነሳሳት ችሏል። (ሚክ. 3:9-12፤ ኤር. 26:18, 19፤ ከ2 ነገሥት 18:1-4 ጋር አወዳድር።) ዛሬም ቢሆን ይህ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ትንቢት የበለጠ ጠቀሜታ አለው። አምላክን እናመልካለን የሚሉ ሁሉ ሚክያስ ስለ ሐሰት ሃይማኖት፣ ስለ ጣዖት አምልኮ፣ ስለ መዋሸትና ስለ ዓመጽ የሰጠውን ግልጽ ማስጠንቀቂያ መስማት ይኖርባቸዋል! (ሚክ. 1:2፤ 3:1፤ 6:1) ጳውሎስ በ1 ቆሮንቶስ 6:9-11 ላይ እውነተኛ ክርስቲያኖች ታጥበው የነጹ በመሆናቸው እንዲህ ያሉትን ድርጊቶች የሚፈጽም ማንኛውም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት እንደማይገባ በመግለጽ የሚክያስን ማስጠንቀቂያ ትክክለኛነት አረጋግጧል። ሚክያስ 6:8 ግልጽና ቀላል በሆነ አነጋገር፣ ይሖዋ ከሰው የሚፈልገው ፍትሕንና ምሕረትን እንዲያደርግ እንዲሁም በትሕትና እንዲመላለስ መሆኑን ይናገራል።

      17 ሚክያስ መልእክቱን ይናገር የነበረው ሕዝቡ በጣም ከመከፋፈሉ የተነሳ “የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰዎቹ” በሆኑበት ማኅበረሰብ ውስጥ ነበር። እውነተኛ ክርስቲያኖችም ብዙውን ጊዜ የሚሰብኩት ከዚህ ጋር በሚመሳሰሉ ሁኔታዎች ውስጥ ነው፤ እንዲያውም አንዳንዶች የገዛ ቤተሰቦቻቸው ይክዷቸዋል እንዲሁም ኃይለኛ ስደት ያደርሱባቸዋል። እነዚህ ክርስቲያኖች ምንጊዜም ‘አዳኛቸው የሆነውን አምላክ’ በትዕግሥት መጠበቅ ይኖርባቸዋል። (ሚክ. 7:6, 7፤ ማቴ. 10:21, 35-39) በድፍረት በይሖዋ የሚታመኑ ሰዎች ስደት ሲገጥማቸው ወይም አስቸጋሪ የሆነ ኃላፊነት ሲሰጣቸው እንደ ሚክያስ ‘በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልን ተሞልተው’ መልእክቱን ይናገራሉ። ሚክያስ በተለይ ‘የያዕቆብ ትሩፍ’ ይህን የመሰለ ድፍረት እንደሚኖረው ተንብዮአል። እነዚህም “በብዙ አሕዛብ መካከል . . . እንዳለ አንበሳ” እንዲሁም ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ። በእርግጥም እነዚህ ባሕርያት በመጀመሪያው መቶ ዘመን የክርስቲያን ጉባኤ አባላት በሆኑት ‘የእስራኤል (የያዕቆብ) ቅሬታዎች’ ላይ በግልጽ ታይተዋል።—ሚክ. 3:8፤ 5:7, 8፤ ሮሜ 9:27፤ 11:5, 26

      18 በሚክያስ ትንቢት መሠረት ኢየሱስ በቤተ ልሔም መወለዱ መጽሐፉ በአምላክ መንፈስ የተጻፈ መሆኑን ከማረጋገጡ በተጨማሪ በዚህ ቁጥር ዙሪያ የተገለጹት ሐሳቦች በክርስቶስ ኢየሱስ በሚተዳደረው የአምላክ መንግሥት ግዛት ሥር የሚኖረውን ሁኔታ የሚተነብዩ መሆናቸውን ያመለክታል። ከቤተ ልሔም (የዳቦ ቤት ማለት ነው) የሚወጣውና በመሥዋዕቱ ለሚያምኑ ሁሉ የዘላለም ሕይወት የሚያስገኘው ኢየሱስ ነው። “በእግዚአብሔር ኀይል . . . መንጋውንም ይጠብቃል” የተባለለትና ዳግመኛ በሚቋቋመውና አንድ በሚሆነው የአምላክ መንጋ መካከል እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ በመሆን ሰላም እንዲመሠረት የሚያደርገው እርሱ ነው።—ሚክ. 5:2, 4፤ 2:12፤ ዮሐ. 6:33-40

      19 ሚክያስ “ብዙ አሕዛብ” የይሖዋን መመሪያ ስለሚፈልጉበት ‘የመጨረሻ ዘመን’ የተናገረው ትንቢት በጣም የሚያጽናና ነው። “ሰይፋቸውን ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጉታል። አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ከእንግዲህም የጦርነት ትምህርት አይማሩም። እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑ ሥር፣ ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፤ የሚያስፈራቸው አይኖርም፤ የእግዚአብሔር ጸባኦት አፍ ተናግሮአልና።” ከማንኛውም የሐሰት አምልኮ ወጥተው ከሚክያስ ጋር በመተባበር “እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም እንሄዳለን” ይላሉ። በእርግጥም የሚክያስ ትንቢት እነዚህ ታላላቅ ክንውኖች የሚፈጸሙበትን ሁኔታ በመተንበዩ እምነት ያጠነክራል። በተጨማሪም ይሖዋ የአጽናፈ ዓለሙ ዘላለማዊ ገዥና ንጉሥ መሆኑን ስለሚገልጽ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መጽሐፍ ነው። “ከዚያች ቀን አንሥቶ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል” የሚሉት ቃላት ምንኛ የሚያስደስቱ ናቸው!—ሚክ. 4:1-7፤ 1 ጢሞ. 1:17

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 34—ናሆም
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 34​—⁠ናሆም

      ጸሐፊው:- ናሆም

      የተጻፈበት ቦታ:- ይሁዳ

      ተጽፎ ያለቀው:- ከክ. ል. በፊት ከ632 ቀደም ብሎ

      የናሆም ትንቢት የሚጀምረው “ስለ ነነዌ ጥፋት የተነገረ ንግር” በሚሉት አስደንጋጭ ቃላት ነው። (ናሆም 1:1) ይሁን እንጂ ናሆም ይህን የጥፋት መልእክት ያወጀው ለምን ነበር? ስለ ጥንቷ ነነዌ ምን የሚታወቅ ነገር አለ? ናሆም ነነዌን ‘የደም ከተማ’ ብሎ በመጥራት ታሪኳን በሁለት ቃላት አጠቃልሎ ገልጾታል። (3:1) የጥንትዋ ነነዌ በነበረችበት ቦታ ላይ ይኸውም በሰሜናዊ ኢራቅ ካለችው ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ ባሻገር በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቃዊ ዳርቻ ላይ ሁለት ጉብታዎች ይታያሉ። ነነዌ ታላቅ ቅጥር የነበራት ከመሆኑም በላይ ከተማዋን ከጥቃት ለመከላከል ሲባል በግንቡ ዙሪያ ተቆፍሮ ውኃ በተሞላ ጥልቅና ሰፊ ጉድጓድ ተከብባ ነበር። ከተማዋ ከመጥፋቷ በፊት በነበሩት ዓመታት ነነዌ የአሦር ግዛት ዋና ከተማ ነበረች። ይሁን እንጂ ከተማይቱ የተቆረቆረችው “በእግዚአብሔር ፊት [“ይሖዋን በመቃወም፣” NW] ብርቱ አዳኝ” እንደሆነ በተነገረለት በናምሩድ ዘመን ሲሆን እርሱም “ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን . . . መሠረተ።” (ዘፍ. 10:9-12) ይህም ነነዌ የተመሠረተችበት መንገድ ጥሩ እንዳልነበረ ያሳያል። ከተማዋ ገናና የሆነችው በአሦር መንግሥት የመጨረሻ ዘመናት በተለይም በሳርጎን፣ በሰናክሬብ፣ በአስራዶንና በአሹርባኒጳል ዘመነ መንግሥት ነበር። ነነዌ ከጦርነትና ከወረራ በተሰበሰቡ ምርኮዎች ከመበልጸጓም በላይ ገዥዎቿ ሥፍር ቁጥር በሌላቸው ምርኮኞቻቸው ላይ በሚፈጽሙት ሰብዓዊነት የጎደለው የጭካኔ ድርጊት በጣም የታወቀች ሆነች።a ከርት ዊሊ ማሬክ ጎድስ፣ ግሬቭስ ኤንድ ስኮላርስ (1954) በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ 266 ላይ እንዲህ ብለዋል:- “ነነዌ በሰው ዘሮች ዘንድ የምትታወሰው በግድያ፣ በዘረፋ፣ በጭቆና፣ በደካሞች ላይ ግፍ በመፈጸም፣ በጦርነትና በተለያዩ የዓመጽ ድርጊቶች እንዲሁም ሕዝቡን በማስፈራራት አስጨንቆ የሚገዛው ደም አፍሳሽ ሥርወ መንግሥት በሚፈጽማቸው ተግባሮች ብቻ ነው። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ገዥዎች ከእነርሱ ይበልጥ ጨካኝ በሆኑ ተፎካካሪዎቻቸው ይገለበጡ ነበር።”

      2 ስለ ነነዌ ሃይማኖትስ ምን ሊባል ይችላል? በርካታ አማልክት ይመለኩባት የነበረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ብዙዎቹ ከባቢሎን የተወሰዱ ነበሩ። ገዥዎቿ ለማጥፋትና ለማውደም በሚዘምቱበት ጊዜ ወደ እነዚህ አማልክት ይጸልዩ ነበር፤ ስግብግብ የሆኑት ካህናቶችዋም ከምርኮ የሚያገኙትን ሀብት በመናፈቅ ከተማዋን ለዘመቻና ለጦርነት ያነሳሱ ነበር። ደብልዩ ቢ ራይት ኤንሸንት ሲቲስ (1886 ገጽ 25) በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንደሚከተለው ብለዋል:- “[የነነዌ ሰዎች] የሚያመልኩት ጥንካሬን ሲሆን የሚጸልዩትም በጣም ግዙፍ ለሆኑ የድንጋይ ጣዖቶች ብቻ ነበር። በአንበሳና በኮርማ ቅርጽ የተሠሩት እነዚህ ጣዖቶች፣ የፈረጠሙ እጆችና እግሮች፣ የንሥር ክንፎች እንዲሁም የሰው ጭንቅላት ያላቸው ሲሆን ይህም የጥንካሬ፣ የድፍረትና የድል ምሳሌ ነበር። የአገሪቱ ዋነኛ ሥራ ውጊያ ሲሆን ካህናቶቹም ያለማቋረጥ ለጦርነት ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር። ዘራፊ የሆኑት የዚህች አገር ሰዎች በጣም ሃይማኖተኞች በመሆናቸው ምንጊዜም ቢሆን በምርኮ የተገኘው ሀብት ለሌሎች ከመከፋፈሉ በፊት የተወሰነው ክፍል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ