የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/07 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ታኅሣሥ 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 31 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 12/07 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ታኅሣሥ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 21 (46)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- የ2008 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት። በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ከጥቅምት 2007 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ለጉባኤው አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን አቅርብ። ረዳት ምክር ሰጪው ያለውን ኃላፊነት ተናገር። ሁሉም የሚሰጣቸውን ክፍል በትጋት እንዲዘጋጁ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጎላ ያሉ ነጥቦች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ እንዲሁም በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም ከተባለው መጽሐፍ ላይ በየሳምንቱ የሚቀርቡትን ትምህርቶች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትጉዎች እንዲሆኑ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- “ልባቸው የተሰበረውን አጽናኑ።”* በአገልግሎት ክልላችሁ የተገኙ አንድ ወይም ሁለት አጭር ተሞክሮዎችን ተናገር።

መዝሙር 14 (34)

ታኅሣሥ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 88 (200)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ታኅሣሥ 31 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም ጂሆቫስ ዊትነስስ—ኦርጋናይዝድ ቱ ሼር ዘ ጉድ ኒውስ (ምሥራቹን ለመስበክ የተደራጁት የይሖዋ ምሥክሮች) የተሰኘውን ቪዲዮ አይተው እንዲመጡ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- “ለአገልግሎት ያለን ቅንዓት እንዳይቀዘቅዝ እንጠንቀቅ።”* በአገልግሎት በቅንዓት ለሚካፈል አንድ አስፋፊ ቃለ ምልልስ አድርግ። እነዚህን ጥያቄዎች መጠቀም ትችላለህ:- ቅንዓትህ እንዳይቀዘቅዝ ምን ጥረቶችን ታደርጋለህ? በቅንዓት ማገልገልህን እንድትቀጥል የረዳህ ምንድን ነው?

20 ደቂቃ:- “ስለ እውነት የሚመሠክሩ መጽሔቶችን አበርክቱ።”* አድማጮች በኅዳር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። እንዲሁም የኅዳርን (ወይም የታኅሣሥን) መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች እንዲያነቡ አበረታታ። በሚቀጥለው ሳምንት እነዚህን መጽሔቶች ይዘው እንዲመጡ ተናገር።

መዝሙር 59 (139)

ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 94 (212)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በጥር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ ጽሑፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ወቅታዊ መጽሔቶችን ለማበርከት ተዘጋጁ። በኅዳር (ወይም በታኅሣሥ) መጠበቂያ ግንብ አሊያም ንቁ! መጽሔቶች ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የሁለቱን መጽሔቶች ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ተስማሚ የሆነው ርዕስ የትኛው እንደሆነና ተስማሚ የሆነውስ ለምን እንደሆነ አድማጮችን ጠይቅ። አድማጮች በአገልግሎት ላይ ሊጠቀሙባቸው ባሰቧቸው አንዳንድ ርዕሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄ መጠቀም ይቻላል? ከዚያስ በርዕሱ ውስጥ ያለው የትኛው ጥቅስ ቢነበብ ጥሩ ነው? የተነበበው ጥቅስ ከርዕሱ ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው? በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኙትን መግቢያዎች ወይም አድማጮች የሰጧቸውን ሐሳቦች በመጠቀም እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት ግብ አውጣ።”* በቅርቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላስጀመሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። ጥናት ያስጀመሩት እንዴት ነበር? ጥናቱ እድገት እያደረገ ያለው እንዴት ነው?

መዝሙር 8 (21)

ታኅሣሥ 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 41 (89)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የታኅሣሥ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።

20 ደቂቃ:- መንፈሳዊ ነገሮችን መከታተል የሚያስገኘው ጥቅም። በጥቅምት 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 3-7 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ:- “በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የስብከት ዘመቻ!”* አድማጮች ጂሆቫስ ዊትነስስ—ኦርጋናይዝድ ቱ ሼር ዘ ጉድ ኒውስ (ምሥራቹን ለመስበክ የተደራጁት የይሖዋ ምሥክሮች) የተባለውን ቪዲዮ ለዘመዶቻቸው፣ ለሚያውቋቸው ሰዎች፣ ተመላልሶ መጠየቅ ለሚያደርጉላቸውና ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸው ባሳዩበት ወቅት ያገኙትን ጥሩ ምላሽ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 90 (204)

ጥር 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 71 (163)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፤ ወይም “የይሖዋን ልብ ደስ የሚያሰኝ ልግስና” በሚል ርዕስ በኅዳር 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 26-29 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ አቅርቡት።

25 ደቂቃ:- እናንት ወላጆች የልጆቻችሁን ልብ ጥሩ አድርጋችሁ ቅረጹ! በየካቲት 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23-27 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ተስማሚ የክለሳ ጥያቄዎችን አዘጋጅ።

መዝሙር 83 (187)

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ