መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“በብዙዎች ዘንድ በሰፊው በሚታወቀው በዚህ ጥቅስ ላይ ያለዎትን አመለካከት ባውቅ ደስ ይለኛል። [ዮሐንስ 3:16ን አንብብ።] ‘የአንድ ሰው ሞት ለሌሎች እንዴት የዘላለም ሕይወት ሊያስገኝ ይችላል?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት፣ ከኢየሱስ ሞት እንዴት ጥቅም ማግኘት እንደምንችል የሚያሳዩ ግልጽና አጥጋቢ ማብራሪያዎችን ይዟል።”
ንቁ! መጋቢት 2008
“ሰዎች ወደ አምላክ መቅረብ እንዲችሉ ለመርዳት ጥረት እያደረግን ነው። ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ አምላክ መቅረብ እንድንችል የሚረዱን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ የአንዳንድ ሰዎችን አምልኮ በተመለከተ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [ማርቆስ 7:7ን አንብብ።] አንድ ሃይማኖት ‘ሰው ሠራሽ ሥርዓትን’ ሳይሆን እውነትን እንደሚያስተምር ማወቅ የሚቻለው እንዴት ነው? እውነትን ማግኘት የሚቻል ይመስልዎታል? ይህ መጽሔት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።”
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“ተስፋን ያዘለ አንድ መልእክት በአጭሩ ብነግርዎት ደስ ይለኛል። በየቀኑ ስለ ሥቃይ፣ ስለ በሽታና ስለ ሞት እንሰማለን። እነዚህን ከመሳሰሉ ችግሮች መገላገል የምንችል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ተስፋ ፈንጥቆላቸዋል። [ዮሐንስ 3:16ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ‘የኢየሱስ ሞት ሊያድንህ የሚችለው እንዴት ነው?’ የሚል ርዕስ አለው።”
ንቁ! መጋቢት 2008
“አጉል እምነቶች ምንም ጉዳት የማያስከትሉ ልማዶች እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ ወይስ አደጋ አላቸው? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ትኩረት የሚስብ ሐሳብ ይዟል። [ኢሳይያስ 65:11ን አንብብ።] ይህ ርዕስ አጉል እምነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማ እንደሆነና እንዳልሆነ ያብራራል።” በገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።