የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/08 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 26 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 2 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 5/08 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ግንቦት 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 65 (152)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2008 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን! በሰኔ 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 30-31 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። የደረሰባቸውን ፈተና እንዲቋቋሙ ይሖዋ እንዴት እንደረዳቸው የሚናገሩ አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ።

20 ደቂቃ:- በዓመት እረፍትህ ወይም ትምህርት ቤት ሲዘጋ ረዳት አቅኚ መሆን ትችላለህ? ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ረዳት አቅኚ ለመሆን የሚያስፈልጉትን ብቃቶች በተመለከተ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 112-113 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ከልስ። በዓመት እረፍታቸው ረዳት አቅኚ የሆኑ አስፋፊዎች ስላገኟቸው በረከቶች እንዲናገሩ ጋብዝ። ትምህርት ቤት ሲዘጋ ረዳት አቅኚ ሆነው ያገለገሉ አስፋፊዎች፣ ሌሎች ክርስቲያኖች ማበረታቻም ሆነ ድጋፍ የሰጧቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። ረዳት አቅኚ መሆናቸው በመንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ የረዳቸው እንዴት ነው? ምን በረከቶችንስ አግኝተዋል? ብቃቱን የሚያሟሉ ሁሉ በዓመት እረፍታቸው አሊያም ትምህርት ቤት በሚዘጋበት ወቅት ረዳት አቅኚ ሆነው እንዲያገለግሉ አበረታታ።

መዝሙር 83 (187)

ግንቦት 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 22 (47)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥኑን ከልስ።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ባለጸጋ መሆን ትችላለህ!”* የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ በገጽ 113-114 ላይ የሚገኘውን የዘወትር አቅኚ ለመሆን ስለሚያስፈልጉት ብቃቶች የሚናገረውን ሐሳብ አቅርብ። ከመስከረም 1 ጀምሮ የዘወትር አቅኚ ሆነው ማገልገል የሚፈልጉ ማመልከቻውን በተቻለ ፍጥነት መሙላት ይኖርባቸዋል።

መዝሙር 43 (98)

ግንቦት 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የግንቦት ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2008 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- “ቀንበሬን ተሸከሙ።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- በሰኔ ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። በንግግርና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። በጥር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ከሚገኙት የናሙና አቀራረቦች መካከል አንዳንዶቹን ከልስ። ከዚያም ሁለት ክፍሎች ያሉት ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያው መጽሐፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል በማሳየት ይጀምርና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ በመያዝ እንዴት ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ እንደሚቻል በማሳየት ይደመደማል።

መዝሙር 75 (169)

ሰኔ 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 99 (221)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- ታማኞች በእጅጉ ይባረካሉ። (ምሳሌ 28:20) የጉባኤው ጸሐፊ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። ጉባኤው በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወራት የአገልግሎት እንቅስቃሴውን ከፍ ለማድረግ ያደረገውን ጥረት ይሖዋ እንዴት እንደባረከው ተናገር፤ እንዲሁም አስፋፊዎቹን አመስግናቸው። በእነዚህ ወራት ውስጥ፣ ምን ያህል ረዳት አቅኚዎች እንደነበሩና ስንት አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እንደተመሩ ተናገር፤ በተጨማሪም በአገልግሎት የተከናወኑ ሌሎች መልካም ነገሮችን ጥቀስ። አድማጮች ከመታሰቢያው በዓልና የመጋበዣ ወረቀቱን ለማሰራጨት ከተደረገው ዘመቻ ጋር በተያያዘ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ። በመስክ አገልግሎት የተገኙ አስደሳች ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ መልክ ማቅረብ ትችላለህ። ረዳት አቅኚ ሆነው በማገልገላቸው ያገኟቸውን በረከቶች በተመለከተ ለሁለት ወይም ለሦስት አስፋፊዎች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ።

15 ደቂቃ:- “‘መልካም የሆነውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ’ ሁኑ።”* አድማጮች ከቤት ወደ ቤት ለሚደረገው አገልግሎት መቼ እና እንዴት እንደሚዘጋጁ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 28 (58)

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ