መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“ይህ ትንቢት እውን ሲሆን መመልከት አይፈልጉም? [ኢሳይያስ 2:4ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] አምላክ በሰው ልጆች ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ እንደሚገባና ‘አለመግባባትን እንደሚያስወግድ’ ልብ ይበሉ። አምላክ፣ ጦርነቶችን ሁሉ የሚያስቀር አርማጌዶን የሚባል ጦርነት እንደሚያካሂድ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። ይህ መጽሔት አርማጌዶን ምን እንደሆነና በጉጉት ልንጠብቀው የሚገባው ለምን እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ 2008
“የምንኖረው በዚህ ጥቅስ ላይ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ይሰማዎታል? [2 ጢሞቴዎስ 3:1-4ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በመጨረሻው ቀን ውስጥ እንደምንኖር ለሚጠቁሙት ምልክቶች ከፍተኛ ትኩረት መስጠታችን ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ምልክቶች ወደፊት በምድር ላይ የሚፈጸሙ መልካም ነገሮች እንዳሉ ይጠቁማሉ። ይህ መጽሔት ስለዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ይሰጣል።”
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“ምድር ያላት የተፈጥሮ ሀብት አላግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ በመሆኑ ‘ምድር ከጥፋት ትተርፍ ይሆን?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህን የሚያጽናና ተስፋ ይመልከቱ። [መዝሙር 104:5ን አንብብ።] ይህ ርዕስ የምድርን የወደፊት ሁኔታ በማስመልከት መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ማብራሪያ ይዟል።” ገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሚያዝያ 2008
“በርካታ ሰዎች ጊዜያቸው የተጣበበ በመሆኑ አምላክን ለማምለክ ጊዜ መመደብ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። እርስዎስ ይህ ነገር ተፈታታኝ ሆኖብዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኤፌሶን 5:15-17ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን በመጠቀም ረገድ አምላክ ከእኛ የሚፈልገውን ነገር አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ምክንያታዊ ሐሳብ ይዟል።” ገጽ 20 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።